Postlar filtri


ምንድነው የተፈጠረው?

የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሳ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ከሰጠው ምላሽ በፋስት መረጃ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።
ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።

ቦሌ አራብሳ ከአመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።

ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።

ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።


ታዋቂው ሙዚቀኛ አቶ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋጭነታቸው የሚታወቁት ሙዚቀኛው አለማየሁ ፋንታ ስራቸውን የጀመሩት ሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት በመቀጠር ነው፤ እዚያም ለ10 ዓመታት ሰርተዋል፡፡

ለ40 ዓመታት ያህል በ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሙዚቀኛው፤ በዕድሜአቸው መጨረሻ ጡረታ ከውጡ በኋላ በዚሁ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ማገልገላቸውን የሙዚቀኛው የቅርብ ሰው ሆኑት ታዋቂው የበገና መምህር መጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ነግረውናል፡፡

ባህላዊዎቹን የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያዎች በገናን በመደርደር፣ ክራርና መሰንቆን አሳምረው በመጫወት ይታወቁ እንደነበር ከመጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ሰምተናል፡፡

አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ የቀለም ትምህርትን የተማሩ እንዲሁም የድቁና ትምህርትም የነበራቸው ነበሩ፡፡

ሙዚቀኛው ከ6 ወራት በፊት በድንገት ወድቀው እግራቸው በመሰበሩ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትናንትናው እለት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት ይፈፀማል።

አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ባለ ትዳርና 6 ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ነፍስ ይማር

ለፈጣን መረጃ ቴሌግራም 👇
https://t.me/MuktarovichOusmanova


የሚያሳዝን ልብ ሰባሪ ዜና ከወደ ሰመራ 😪

የሰመራ ዮኒቨርስቲ ተጨዋቾችን የጫነ ሰርቪስ ከአዋሽ አርባ ወደ ሰመራ በሚወስደው መንገድ ላይ ዛሬ ማለዳ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶበታል።

ከሟቾች መካከል 👇

የዳጉ ስፖርት መስራች የሆነው እና ትኩረት ያላገኙ የታችኛው የሀገራችን ሊጎችን በሚገርም ትጋት ሽፋን በመስጠት የሚታወቀው ኑሩ ሁሴን ህይወቱ ማለፉን ተሰምቷል። ነፍስ ይማር ወንድማለም 😭

ለፈጣን መረጃ ቴሌግራም

https://t.me/MuktarovichOusmanova


የተወዳጁ ድምፃዊ አንዷለም ጎሳ ባለቤት ቀነኒ አዱኛ በድንገት ሕይወቷ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ የቀነኒን አሟሟት ፖሊስ እያጣራ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ነፍስ ይማር 😢
ለፈጣን መረጃ ቴሌግራም 👇
https://t.me/MuktarovichOusmanova


“የጊዜያዊ አስተዳደሩ በሶስት ጄነራሎች ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ተቋማዊ አሰራርን እና ህግን ያልተከተለ ነው” - የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ በተለያዩ ግንባሮች አዛዦች መሆናቸው የተገለጸ ሶስት ጄነራሎችን፤ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሀይለ በግዜያዊነት ማገዳቸውን አስታወቁ።

በፕሬዝዳንቱ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ጄነራሎቹ በግዜያዊነት የታገዱት “ከመንግስት ውሳኔ ውጭ መላ የክልሉን ህዝብ እና ወጣቱን ወደ ግርግር፣ የጸጥታ ሀይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገባ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ በመሆኑ ነው” ብሏል፤ የጀነራሎቹ እንቅስቃሴ “ህዝቡ ወደማይወጣው አዘቅት የሚከት ነው” ሲል አስታውቋል።

የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ “የወንጀለኞች ጠበቃ መሆን ይብቃ” በሚል ርዕስ ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን እንደማይቀበለው አስታውቋል፤ “ያልሾመውን ያወረደ ነው” ሲል ገልጿል።

በተመሳሳይ በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የጉዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ውሳኔን ህገወጥ ሲል ኮንኗል፤ “የትግራይ ሰራዊትን ለማፍረስ ሲያደርግ የነበረው ሴራ ወደ ከፍተኛ እና አደገኛ ደረጃ አሸጋግሮታል” ሲል ገልጿል።

ለወቅታዊ ፈጣን መረጃ ከታች ያለውን ቴሌግራም ይከታተሉ 👇

https://t.me/MuktarovichOusmanova


መቀሌ ውጥረት ነግሷል‼️
ዛሬ ለሊቱን ጀምሮ ብዛት ያለው ሰራዊትና መትረየስ የጫኑ ፓትሮል መኪኖች በመቀሌ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ እያደሩጉ እንደሚገኙ ታውቋል‼️
በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ህዝባዊ ሰራዊታችን በከሃዲ ቡድን ሴራ አይፈርስም ብሏል።
ህወሓት በመግለጫው የግዚአዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ብሄራዊ ክህደት የፈጸሙ እና እየሰሩ ያሉ አመራሮችን በማባረር በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ውክልና አንስቻለሁ ያለ ሲሆን ነገር ግን ጊዚያዊ ፕሬዝዳንቱ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከህግና ስርዓት ውጪ ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።

የህዝባችንን አንድነት በማደፍረስ የትግራይን ሁለንተናዊ አቅም በማዳከም ብሄራዊ ክህደት እየፈፀመ ያለው የቀድሞ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ለመፋለም የተደራጀውን የትግራይ ሰራዊት ለመበተን ድርጊቱን አጠናክሮ ቀጥሏል"ብሏል።
የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከስልጣናቸው እና ከኃላፊነታቸው ውጪ የትግራይ ጦር ግንባር አመራሮችን እና ጄኔራሎችን አግደዋል ያለው ህወሃት፣ይህ ማዕቀብ መሠረተ ቢስ እና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ቢሆንም ህዝባዊ ትግሉን ከህግ እና ከስርዓት ውጭ ለማድረግ ቡድኑ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን ያሳያል ማለቱን አዩዘሀበሻ ከመግለጫው ተመልክቷል።
አዩዘሀበሻ


ሰበር
ሰበር ዜና

ዙሩ ከሮአል የትግራይ ክልል ጊዚያዊ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሶስት የጦር አዛዦች ማምሻውን ከስራ አገዱ። ምንጭ የትግራይ ቴሌቪዥን
በትግራይ ፍጥጫው በርትቶ ወደየለየለት የርስበርስ ጦርነተ እንዳያመራ ከፍተኛ ስጋት አለ።


ለሕወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ

አንዳንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ረገብ እያለ የቀጠለው የሕወሓት አመራሮች ሽኩቻ መነሻው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተሳተፈው የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ምን መፈጸምና አለመፈጸም እንዳለበት በተገቢው ሁኔታ ሳይደራደር ትዕዛዝ ተቀብሎ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን፣ የሕወሓት አንደኛው ክንፍ ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ዘ ኒው ሂዩማኒታሪያን ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት አሁን በትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን መካከል ለሚታየው መቆራቆስ ዋነኛ ምክንያት ነው፤›› በማለት ስምምነቱን ‹‹የክፍፍሉ መነሻ›› ብለውታል።
አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይዘውት የተጓዙት ተደራዳሪ ቡድን በጦርነት ለደቀቀችው ትግራይ፣ ‹‹ጦርነቱን ብቻ እንዲያስቆምና ከዚያ ያለፈም ያነሰም ነገር እንዳይፈጽም ነበር ተልዕኮ የተሰጠው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የክልሉን መንግሥት የሚያፈርስ ትዕዛዝ ጭምር ይዘው መጥተዋል...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.proworksmedia.com/139049/


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፀደቁ ሁለት አዳዲስ አዋጆች ዙርያ ቅሬታ ያቀረቡ ፖለቲከኛ ዛሬ ጠዋት ታሰሩ

(መሠረት ሚድያ)- ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በነበረ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቀርቦ የፀደቀውን የየእርከኑ የምክር ቤት ተወካዮች ብዛት ለመወሰን የወጣ አዋጅ እንዲሁም የክልሉ ህገ መንግስትን እንደገና ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ተቃውመው ቅሬታ ያስገቡት ፖለቲከኛ ዛሬ ጠዋት ለእስር ተዳርገዋል።

መሠረት ሚድያ እንዳረጋገጠው የቦሮ ዲሞክራያዊ ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና የክልሉ የምክር ቤት ተመራጭ የሆኑን አቶ ዮሐንስ ተሰማ በፀጥታ ሀይሎች ተወስደዋል።

የቦሮ ዲሞክራያዊ ፓርቲ በውሳኔዎቹ ላይ ቅሬታ የነበረው ሲሆን ሶስቱ የምክር ቤቱ አባላት በወቅቱ ተቃውሞ አቅርበው ውሳኔውንም 'የህገ መንግስት አተረጓጎም ላይ የቀረበ ቅሬታ' በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ከተጨማሪ ጥያቄዎች ጋር አቅርበው ነበር።

"በዚህ ሁኔታ ያቀረቡትን ጥያቄ የተለያዩ አንድምታ እየሰጡ ይባስ ብለው ዛሬ አቶ ዮሀንስን አስረውታል" ብለው የክልሉ የመረጃ ምንጫችን ለሚድያችን ተናግረዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ከየካቲት 10 እስከ 11 2017 ዓ/ም በአሶሳ ከተማ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ በስራ ላይ የሚገኘውን የክልሉን የምክር ቤት የመቀመጫ ቁጥር ከ99 ወደ 165 አሻሽሏል፡፡

የቦሮ ዲሞክራያዊ ፓርቲ ግን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሳይደረግ 165ቱ የመቀመጫ ብዛት አሁን በስራ ላይ ለሚገኙ የምርጫ ክልሎች የተከፋፈለበት መንገድ የህዝብ ብዛትን ያማከለ አለመሆኑን እና ነባር የምርጫ ክልሎች የፈረሱበትና አዳዲስ ምርጫ ክልሎች የተቋቋሙበት ሂደት ህገ መንግስቱን የጣሰ በመሆኑን እንዲሁም በቂ ውይይትና ክርክር ያልተደረገበት መሆኑን በመግለፅ ቅሬታውን ገልፆ ነበር።
ምንጭ መሠረት ሚዲያ


አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ 72ኛው አባ ገዳ ሆነው ተሰየሙ

አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ስልጣናቸውን ለተከታያቸው አስረክበዋል።

ተከታዩ አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮ 72ኛው አባ ገዳ በመሆን ለቀጣይ ስምንት ዓመታት ስልጣናቸውን ተረክበዋል።

አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ 71ኛው አባ ገዳ ሆነው ላለፉት ስምንት ዓመታት ሥርዓቱን በመምራት አገልግለዋል።

72ኛው አባ ገዳ ሆነው የተመረጡት አባ ገዳ ጉዮ ቦሩ ጉዮም ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት የገዳውን ሥርዓት በበላይነት የሚመሩ ይሆናል።


ከጅቡቲ የተነሱ አራት ጀልባዎች ተገልብጠው 181 ኢትዮጵያዊያን መጥፋታቸው ተሰማ፡፡ የአለም የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀው ጀልባዎቹ ከጅቡቲ ተነስተው ወደየመን እየተጓዙ ነበር፡፡ አራቱም ጀልባዎች ጉዞ የጀመሩት ትላንት ሀሙስ ምሽት ላይ ሲሆን በወቅቱ የነሳው ሀይለኛ ንፋስ ጀልባዎቹን እንደገለበጣቸው አስረድቷል፡፡ ከአራቱ ጀልባዎች ሁለቱ የተገለበጡት ጅቡቲ አቅራቢያ መሆኑን የገለፀው አይኦኤም በዚህኛው አደጋ ሁለት ስደተኞች ሞተው አስከሬናቸው መገኘቱን አስታውቋል፡፡

ቀሪዎቹ በጀልባው ላይ ተሳፍረው የነበሩት ስደተኞች በሙሉ በህይወት መትረፍ መቻላቸውንም ገልጿል፡፡ ሶስተኛው ጀልባ ከጅቡቲ ተነስቶ ጉዞ ከጀመረ በኋላ በደቡባዊ ምእራብ የመን ታኢዝ ግዛት ክልል ውስጥ ሲደርስ መገልበጡን ያስታወቀው ድርጅቱ በዚህኛው ጀልባ 31 ኢትዮጵያዊያንና ሁለት የመናዊያን የጀልባው አሽከርካሪዎች እንደነበሩ አስረድቷል፡፡ አራተኛው ጀልባም የተገለበጠው በዚሁ አካባቢ ሲሆን 150 ኢትዮጵያዊያንንና አራት የመናዊያን የጀልባውን አሽከርካሪዎች አሳፍሮ እንደነበር ጨምሮ ገልጿል፡፡

በመሆኑም በሶስተኛውና አራተኛው ጀልባ ተሳፍረው የነበሩት 181 ኢትዮጵያዊያንና አምስት የመናዊያን የጀልባው አሽከርካሪዎች እስካሁን እንዳልተገኙ ጠቅሷል፡፡ እነዚህን የጠፉትን ሰዎች ፍለጋው እየተከናወነ ሲሆን አንደኛው የመናዊ መገኘቱንም አስረድቷል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ አገራት ዜጎች ወደመካከለኛው ምስራቅ ለሚያደርጉት ፍልሰት ዋነኛ መተላለፊያቸው የመን ስትሆን በጅቡቲ በኩል በሚደረገው በዚህ ጉዞ በየአመቱ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች ሙከራ እንደሚያደርጉ ይገመታል፡፡

Zehabesha


(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ ሰራዊት(ቲዲኤፍ) አመራሮች ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ የህወሀት ዋና ፅህፈት ቤት በሚገኝበት ሰማእታት ሀውልት አዳራሽ በተደረገው በዚህ ውይይት ላይ ከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ የሰራዊቱን አዛዦች በመወከል መድረኩን የመሩት ጄኔራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊው ወይንም መዲድ ናቸው፡፡

በስብሰባው ላይ ከሁሉም መቀሌ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን የሚሰማቸውን ጥያቄዎች አቅርበው መልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የዛሬው ውይይት ሊካሄድ የነበረው ሮብ እለት ቢሆንም የሰራዊቱ አዛዦች ባለመገኘታቸው ለዛሬ መቀጠሩ ይታወቃል፡፡ የዛሬውን ውይይት ለየት የሚያደርገው የሰራዊቱ አዛዦች መገኘታቸው ብቻም ሳይሆን በስብሰባው መክፈቻ ላይ የተገኙት የክልሉ ሚዲያዎች ልክ ስብሰባው ሲጀመር እንዲወጡ መደረጋቸው ነው፡፡

በመክፈቻው ወቅት ፎቶ ግራፍ ማንሳት የተፈቀደላቸው ጋዜጠኞቹ ሙሉ ውይይቱን እንዳያዳምጡ ከአዳራሹ መባረራቸውን ከስፍራው የተሰራጩ መረጃዎች አስረድተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት የከተማውን ወጣቶች ማነጋገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

🔴 በስብሰው ላይ ጄነራሉ ስላነሷቸውና ሌሎችም ተጨማሪ ጉዳዮች አሁን የተለቀቀው መረጃችንን ከዩቱብ ገጻችን ይመልከቱ።


አዲስ አበባ ቤሌር አካባቢ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እያሉ በደረሰባቸው አደጋ አፈር ተጭኗቸው የነበሩ ሁለት ሰራተኞችን በህይወት ማውጣት መቻሉ ተሰምቷል።


#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1 መኝታ 66ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 71ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177


ወቅታዊ እና እውነተኛ የመረጃ እጦት ለጋጠማችሁ፣ የቱን ልመን? ብላችሁ ለተወዛገባችሁ፣ እነሆ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ መረጃዎችን ካሉበት አጣርቶና ፈልፍሎ ልምድ ባላቸው ጋዜጠኞች የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ።

መረጃዎቹ ለየት ያሉ ፈጣን እና እውነተኛ ናቸው።👌""በዚህ ሊንክ ግቡ
👇👇👇
https://t.me/+MGwLfqRVgDsyNGM0
https://t.me/+MGwLfqRVgDsyNGM0
https://t.me/+MGwLfqRVgDsyNGM0


ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የቀድሞ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ተናገሩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት (ጆቤ)፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መጀመሪያውንም ያልተቀደሰ ግንኙነት እንደነበር ጠቁመው፣ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ ፍንጮች እንዳሉ ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያ የወደብ ተጠቃሚ መሆን የምትችልባቸውን ሁኔታዎች በተመለከተ ከሦስት ዓመታት በፊት የሠሩትን ጥናታዊ ጽሑፍ አስታውሰው፣ ጥያቄው ግን በጉልበት መመለስ የለበትም ብለዋል፡፡ በአገሮቹ መካከል ጦርነት ቢቀሰቀስ አቅጣጫው ምን ይሆናል የሚለው ጉዳይ የሚታወቀው የጦርነቱ ዓላማ ሲታወቅ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ‹‹ጦርነቱ አንድም አሰብን መያዝ፣ ሁለተኛው ደግሞ ሻዕቢያን ማስወገድ ሊሆን ይችላል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የጦርነቱ ዓላማ አሰብን መያዝ ከሆነ የሁለቱን አገሮች የመሣሪያና የቴክኖሎጂ አቅም መገምገም እንደሚገባ ጠቅሰው፣ የሻዕቢያን መንግሥት የመጣል ዓላማ ካለ ደግሞ፣ የኤርትራ ዕጣ ፈንታ የሚያሳስባቸው እንደ አሜሪካ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.proworksmedia.com/138930/


የደቡብ ሱዳን ጦር የሀገሪቱን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪካ ማቻርን መኖሪያ ቤት ከቧል፣ ሚንስትሮችም ታስረዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሚመሩት መንግስት ጦር ማምሻውን በምክትላቸው ሪክ ማቻር መኖሪያ ቤት ከበባ በማድረግ የቁም እስረኛ እንዳደረጋቸው ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

እስካሁን ለማቻር ቅርበት አላቸው የተባሉ ሶስት ሚንስትሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። መንግስት እርምጃውን የወሰደው ለማቻር ታማኝ ነው የተባለ ታጣቂ ቡድን በላይኛው ናይል ግዛት በሚገኝ የመንግስት የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሶ ከተቆጣጠረ በኋላ ነው። በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንትና በምክትላቸው መካከል ከአስራ ሁለት አመት በላይ የዘለቀ ተደጋጋሚ ውጊያ ያደረጉና ለሚሊዮኖች ሞትና መፈናቀል ሰበብ ናቸው።

Image: Pope Francis literally begs for peace at retreat for South Sudan leaders, April 11, 2019, CNS photo/Vatican Media via Reuters


(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት (ጆቤ)፣ "ከ28 ዓመታት በፊት በተካሄደው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ሻዕቢያን የመደምሰስ አቅም የነበረ ቢሆንም ይህ አለመደረጉ ትልቅ ስህተት ነበር" አሉ።

የቀድሞው የአየር ኃይል ዋና አዛዥ፣ ከዚያ በኋላ በነበሩት 18 ዓመታት የተሠራው ጠላትን በዝምታ የማቆየት ትልቅ ስህተት ከባድ ዋጋ ማስከፈሉን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የትግራይ ሕዝብ ዋጋ እንዲከፍል ምክንያት ሆኗል ብለው፣ አሁንም ጦርነት ከተቀሰቀሰ የትግራይ ክልል የጦርነት ዓውድማ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መጀመሪያውንም ያልተቀደሰ ግንኙነት እንደነበር ጠቁመው፣ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ ፍንጮች እንዳሉ ገልጸዋል።


ከደብረ ታቦር ወረታ መሀከል ባለችው ወጂ አቅራቢያ ከ30 በላይ ሹፌሮች ታፍነው ተወስደዋል መንገዱም በመኪኖች ሙሉ ለሙሉ በመዘጋቱ ቁመናል ታፍነው የተወሰዱ ሹፌሮች ረዳቶች ብዛታቸውን አጣርተን እናሳውቃለን ::

የሹፌሮች አንደበት የፌስቡክ ገፅ


🌾 ለሶፋ እድሳት ሁነኛ ምርጫዎ ነን🌴

ከውጭ የገቡ ሶፋዎችን ፈረንጆቹ በሰሩበት ማሽኖች እና ሙያዊ ብቃት እንደነበሩ አድርገን መልሰን እናድሳለን 👌

🌻 በውድ የገዙት ሶፋዎት በከፍተኛ ጥራት በማደስ ወደ ቀድሞ አዲስነቱ በመመለስ እናስደንቆታለን

🌻 የ11 አመታት የሶፋ እድሳት የስራ ልምዳችን ጥንቅቅ ያለ ስራ እንድንሰራ አስችሎናል

🌻 የሀገር ውስጥ ሶፋዎችንም ከተለመደው ከፍ ባለ ጥራት ማሳደስ ለምትፈልጉም በራችን ክፍት ነው

🌻 በሀገራችን አሉ የተባሉ ስማቸው ገናና የሆኑ ፈርኒቸር ወይ ሶፋ አምራቾች የሚጠቀሙባቸውን ማሽኖች ይዘን የእድሳት ስራ እንደምንሰራ የሚያውቁ ደንበኞች የዘውትር ምርጫቸው ነን

🌻 ዋጋችን ተመጣጣኝ የስራ ጥራታች ከፍተኛ ነው።

🌻 በአቅራቢያችን ላሉ ሰዎች እንደ ሶፋው የቤት ለቤት እድሳት አገልግሎት ልንሰጥ እንችላለን።

🌻አዳዲስ ሶፋ በፈለጉት ዲዛይን እና በቤትዎ ልክ እንሰራልዎታለን።

🌻የተንጣለለ ወርክሾፖችንን እና ለእድሳት ስራ የምንጠቀማቸውን ማሽኖች መጥተው ይጎብኙ።
አድራሻችን ጃክሮስ ሜታ አካባቢ ለበለጠ መረጃ
0921317125
0938300946
ላይ ይደውሉልን
ድረገፃችንን ይጎብኙ 👇

https://smartsofasolution.com

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.