ዛሬ የሸዕባን ወር የመጀመሪያ ቀን ነው። በተለያዩ ምክንያቶች የባለፈው አመት ረመዿን ጾም አልፏችሁ ቀዷውን ያላወጣችሁ ካላችሁ፤ የዚህ አመት ረመዿን ሳይገባባችሁ ባላችሁ ክፍት ቀናት አጠናቁ።
ይህ የሸዕባን ወር ከተከበሩት አራት ወራት መካከል አንዱ በሆነው በወርሃ ረጀብ እና በውዱ የረመዿን ወር መካከል የሚገኝ ስለሆነ፤ ብዙ ሰው እንደሚዘናጋበት ውዱ ነቢይ ﷺ ነግረውናል።
ሰዎች በተዘናጉ ጊዜ በዒባዳህ መበርታት ደግሞ ልዩ ምንዳ አለውና በተለይም ጾም ላይ እንበራታ፤ ራሳችንንም ለወርሃ ረመዿን ነፍሳችንን እናዘጋጃት።
ገና ከአሁኑ ከወንጀል መራቅንና በመልካም ነገር ላይ መበራታትን ያልተለማመደች ነፍስ፤ ኋላ ቀጥታ ረመዿን እንደጀመረ በቅፅበት ከመጥፎ ነገር ርቀሽ በጥሩ ነገር ተጠመጂ ብለን ስንይዛት ያልለመደችው ሆኖባት በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ ላትሆን ትችላለች። በረመዿን ውስጥ እያንዳንዷ ሰከንድ ልዩ ቦታ ስላላት በመለማመጃ የምታልፍ ሳትሆን ውጤታማ በሆነ ነገር ማለፍ የሚገባት ናት። ስለሆነም ከወዲሁ እንስተካከል። ሌሎችንም እናስታውስ። አላህ ያግራልን!
||
t.me/MuradTadesse