Natnael Mekonnen


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Siyosat


በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Siyosat
Statistika
Postlar filtri


እያመመው እያመመው መጣ ‼️ሶማሊያ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለጎረቤቷ ኢትዮጵያ የወደብ መዳረሻ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር እየተነጋገረች መኾኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ሞሐመድ ኦማር መናገራቸው ተገለጸ።

እንደ ሃገር እንደ ጥሩ ጎረቤት ኢትዮጵያ የሌላትና ከሶማሊያ የምትፈልግው ሶማሊያ የሌላትና ከኢትዮጵያ የምትፈልገው ብዙ ነገሮች አሉ:: በሰጥቶ መቀበል መርህ አብሮ ማደግ መበልጸግ ነው የኢትዮጵያ መርህ!

ሶማሊያ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለጎረቤቷ ኢትዮጵያ የወደብ መዳረሻ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር እየተነጋገረች መኾኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ሞሐመድ ኦማር መናገራቸው ተገለጸ።

ሁለቱ ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ አየመከሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒሰተር ዴኤታው እስከ መጪው ሰኔ ወር የስምምነቱን ማዕቀፍ ለማጠናቀቅ እየተነጋገሩ ነው ማለታቸውን ከብሉንበርግ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

“ማዕቀፉ ምን አይነት ወደብ እንደሚሰጥ ውሳኔ ይሰጣል፣ በትክክል የትኛው የህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ እንደሚሻል ምክረ ሀሳብ ያቀርባል እንዲሁም ለወደቡ ግንባታ አጠቃላይ ስለሚያስፈልገው የገንዘብ ወጭ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል” ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሞቃዲሹ ማቅናታቸው ይታወቃል፤ የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ሶማሊያ ያመሩት ጠ/ሚ አብይ በሞቃዲሾ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ጋር የፀጥታ ትብብርን በማጠናከር፣ የንግድ አጋርነት በማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የአንካራውን ስምምነት ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን በወቅቱ ከ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ውይይት በማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመመለስ መስማማታቸውን ይታወሳል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መልካም የአድዋ ድል በዓል!!!💚💛❤


ዜለንስኪ ከቡጤ መዳኑ ተአምር ነው -ማርያ ዛካሮቫ

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሮቫ የዋሽንግተኑ ክስተት እንዳበቃ ይህን መልዕክት አሰፈረች።

በዜለንስኪ ውርደት አንጀቷ የራሰው ማርያ 👇

" ትራምኘ እና ጄድ ቫንስ በዚህ ከሃዲ ላይ (ዜለንስኪን ማለቷ ነው) ቡጢ ከማሳረፍ የታቀቡት ራሱ በተአምር ነው " ስትል ፅፋለች።

ዜለንስኪ ከትራምኘ ጋር ባደረገው ንግግር ላይ እኳን ብዙ ውሸቶችን ተናግሯል ያለችው ዛካሮቫ ፥ ለዚህም ቁጣ እና የቃል ዘለፋ ብቻ ሳይሆን ቡጢም ይገባው ነበር ብላለች።

ክሬምሊን በኋይት ሃውስ ተግባር እንደዛሬው ጮቤ የረገጠበት ዕለት በታሪክ ቢፈለግ ከቶም አይገኝም።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ትራምፕ ዘለንስኪን “አሜሪካን አላከበርክም" ሲሉ፤ ዘለንስኪ ዋይት ኃውስን ጥለው ወጥተዋል

የአሜሪካው ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በዋይት ኃውስ ያደረጉት ውይይት ያለ ምንም ስምምነት ተጠናቋል።

ዘለንስኪ ወደ ዋይት ኃውስ ያቀኑት በውድ ማእድናት ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር ስምምት ለመፈራረም ቢሆን፤ ሁለቱ ወደ ክርክር እና የቃላት ግጭት አምርቶ ያለ ምንም ሰምምት ተጠናቋል።

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር የጦፈ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው ውይይታው የተቋረጠው።

በዋየት ኃውስ በኦቫል ፅህፈት ቤት በነበራው ቆይታ ዶናድ ትራምፕ ቮሊድሚር ዜልኒስኪን “አክብሮት የጎደለው ባህሪ” ከሰዋል።

በንግግራው ወቅትም ትራምፕ ዘሌንስኪን “በሚሊየኖች ህይወትና በ3ኛ የዓለም ጦርት ቁማር እየተጫወትክ ነው” ብለዋል።

ዘለንስኪ የሰለም ስምምነት ለመፈረም ዋስትና ያስፈልገናል ማለታችውን ተከትሎም፤ ትራም ዘለንስኪን ያለህ አማራጭ ስምምነቱን መፈረም ነው ካልሆነ አሜሪካ ከዚህ ትወጣለች ሲሉም ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ዘለንስኪ በሰላም ውይይቱ ዙሪያ ካለመግባባታቸውም ባሻገር "ለሰላም ስትዘጋጅ ተመለሰህ ና" ብለዋል።

ይህንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ዋይት ሀውስን ጥለው የወጡ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ሊያደርጉት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰርዟል፡፡


የኢትዮጵያ መርህ....ሠላም ነው!

ሰሞኑን ሚዲያው ሁሉ ቅኝቱ የጦርነት ሆኗል። አንዳንድ ተስፈኞች ደግሞ ኢትዮጵያ ካሁን አሁን ወደጦርነት ገባችልን ብለው በተስፋ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ባለፈው "ከሶማሊያ ጎን ነን" ይሉ የነበሩት ዛሬ ጎን ቀይረው "ከኤርትራ ጎን ነን" ሲሉ ሰማን። ገዢ ይኑር እንጂ ራሳቸውን ለመሸጥ ታጥበውና ታጥነው እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ቁርጠኛ የኢትዮጵያ ልጆች ግን ጉዳዩን በጥሞና እየተከታተሉ ነው።

ለጠላትም ለወዳጅም ግልፅ ማድረግ የምንፈልገው ነገር....ኢትዮጵያ የጦርነት ፍላጎት የላትም። ጦርነትን ለማስቀረትም ትሰራለች።
ጦርነት ተገደህ የምትገባበት እንጂ "ለምን አየኸኝ" ብለህ የምትጀምረው የሰፈር ጠብ አይደለም። ጦርነትን አይተነዋል። እናውቀዋለን። በፍፁም የመጀመሪያ ምርጫችን ሊሆን አይችልም። በተለይ ድንበር፥ ታሪክ፥ ቋንቋ፥ ባህል፥ ከምትጋራው ጎረቤትህ ጋር የምትገባው ጦርነት ብታሸንፍም የማታሸንፍበት እንደሆነ እንረዳለን። የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊስ ግልፅ ነው። እሱም "በጋራ ተጠቃሚነት ላይ አብሮ መስራትና በጋራ ማደግ" ይባላል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውም ሐገር ላይ ወረራ ፈፅማ አታውቅም። ወረራ ሊፈፅም ያሰበን ቀጥተን መመለስ እንደምናውቅበት ሁሉ የሌላውን ድንበርና ሉአላዊነት ማክበርም እናውቅበታለን።
ኢትዮጵያ የትኛዋም ሐገር ልታነሳው የምትችለውን የባህር በርም ሆነ ተዛማጅ ጥያቄ ጠይቃለች። ይሄን ለማሳካትም ቀን ከሌት ትሰራለች። ነገር ግን ይሄን የምታደርገው የሌሎችን ሉአላዊነትና ጥቅም ረግጣ አይደለም። የምንኖረው በሰለጠነ ዘመን ነው። ውይይት፥ ድርድር፥ ሰጥቶ መቀበል፥ የማይፈታው ቋጠሮ የለም። ሐገር እየመራህ በደበረህ ቁጥር ህዝብን አፋፍሰህ ወደጦርነት የምትማግድበት ግዜ አልፏል። የፖለቲካ ችግር የሚፈታው በፖለቲካዊ መፍትሄ እንጂ በአፈሙዝ አይደለም።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን የሚባል ጦር የገነባችው በየአመቱ ጂኦግራፊ ያጣመረንን ጎረቤቶቻችንን ለመውጋት አይደለም። የኛ ጥያቄ የሚመነጨው ከህግ፥ ከታሪክና ሐገራችን ካለችበት አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም ከህዝባችን ዘላቂ ጥቅም አንፃር ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ባለፉት ስድስት ወይም ሰባት አመታት ለሰላም ስንል የሄድንባቸው ርቀቶች ምስክሮቻችን ናቸው።

አለም እስኪደነቅ ድረስ ከኤርትራ ጋር የነበረን የዘመናት ግጭት በሰላም ፈትተን አሳይተናል። ለአመታት የዘለቀ ጦርነትን በእርቅ ፈትተን አሳይተናል። በተለያየ ግዜ ሐገር ውስጥ ካሉ ታጣቂዎች ጋር ያለብንን ችግር በእርቅ ፈትተን አሳይተናል። ነገም ለሰላም ሲባል ብዙ ርቀት ለመጓዝ ዝግጁ ነን።

እኛ በሰበብ አስባቡ እየሳቅን ወደእሳት የምንማግደው ትርፍ ትውልድ የለንም። ለፖለቲካ ትርፍ ብለን ጦርነት ውስጥ የምንጨምረው ወጣት የለንም። የየአንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነፍስ የከበረ ዋጋ አላት። አጥራችን ሲታለፍ። መስመራችን ሲረገጥ የማንታገሰውን ያህል ለሰላም ስንል የመጨረሻዋን እድል ሁሉ እንደማናባክን አለም ያውቃል።

ስለዚህ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ኢትዮጵያ የምትዋጋውም ለመዋጋት ያቀደችው ጦርነት የለም። ይልቁኑ ጦርነትን የመጨረሻ መፍትሄ ያደረጉ ሀይሎች ካሉ "ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ" ይላልና ቃሉ በእብሪት ያበጠ ደረታቸውን መልሰው ለሰላምና ለዘላቂ ጥቅማችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመወያየት ቢዘጋጁ ለሁላችንም ይበጃል ባይ ነኝ።

የበሬ ቆ*ጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል እንደዋለችው ቀበሮ፥ ኢትዮጵያ ካሁን አሁን ወደጦርነት ገባች ብላችሁ ተስፋን ለሰነቃችሁ የቀበሮ ባህታውያንም ተስፋ ቆርጣችሁ ወደቀድሞ አሰልቺ ትንታኔያችሁ እንድትመለሱ እንመክራለን።

ሰላም ለሐገራችን!
ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር!


እያመመው መጣ!


በዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል። በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊቲ ሐኪም፣ ተመራማሪ፣ መምህር እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ባልታወቁ ኃይሎች መገደላቸው ይታወሳል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው በሰጡት መግለጫ ፖሊስ ባደረገው ክትትል አንደኛውን ተጠርጣሪ ገዳይ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ብለዋል። እሱባለው ነበረ የሚባል ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ነው ያሉት። ወንጀል ፈጻሚው ድርጊቱን መፈጸሙን ማመኑንም ተናግረዋል። ግድያው ጥቅም ፍለጋ መኾኑን ተናግረዋል።

ፖሊስ የዶክተር አንዱዓለም ዳኘን ገዳዮች ለፍርድ እንደሚያቀርብ ቃል በገባው መሠረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ነው የገለጹት። በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ተመሳሳይ ወንጀሎችን ይፈጽም እንደነበርም አንስተዋል።በግድያ ወንጀሉ ከተሳተፉት ውስጥ የተያዘው ተጠርጣሪ ዋናው መኾኑን የተናገሩት ኀላፊው እርሱን ያገዙ እና ግብረ አበሮቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ፖሊስ እየሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሶማሊያ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል::


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሶማሊያ ገብተዋል።


ኢ-ፓስፖርቱ ለዜጎች ጥራት እና ግልፅነት የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት ያግዛል፡- ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተው እና ዛሬ ይፋ የተደረገው ኢ-ፓስፖርት ለዜጎች ጥራት እና ግልፅነት የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።

አዲሱ ኢ-ፓስፖርት ይፋ በተደረገበት ወቅት ፕሬዚደንት ታየ እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ፓስፖርቶች እና የጉዞ ሰነዶች ዘመኑን የዋጁ እና የተራቀቁ የደህንነት ባህሪያት እንዲኖራቸው መደረጉ ትልቅ እመርታ ነው።

የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ተግባራዊ መደረጉ የሀገርን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ለዜጎች የተሰጠውን ዋጋ የሚገልፅ ነው ብለዋል።

ፓስፖርቱ ማንኛውንም አይነት ማጭበርበር ለመግታት የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ዘመናዊ ሰነዶች የሰዎችን እንቅስቃሴ ከማፋጠን ባሻገር ንግድን ለማሳለጥና ህጋዊ የስራ ዕድል ለማግኘት አስፈላጊ መሆናቸውንም አክለዋል።

ኢ-ፖስፖርቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በቶፓን ሴኪዩሪቲ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር አማካኝነት በሀገር ውስጥ መመረቱ በመድረኩ ላይ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምሕረት፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ፣የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


Ethiopiaዬ ሰላምሽ ይብዛ! ከጫካ ወደ ሰላማዊ ትግል የመጡት የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ሹመት ተሰጠ::

Good News : የኦሮሚያ ክልል የመንግስትን የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-

1. አቶ ያደሳ ነጋሳ
በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ

2. አቶ ኦሮሚያ ረቡማ
የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ ምክትል ሃላፊ

3. አቶ ቶሌራ ረጋሳ
የኦሮሚያ ክልል ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ

ሁሉም ቢተሳሰብ፥
ሁሉም ቀና ቢያስብ፥
. . .
መተሳሰብ ቢኖር፥
ሁሉም ቢተባበር፥
የት ይደረስ ነበር?


አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርትን ይፋ ተደረገ

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርትን ይፋ አደረገ ፡፡

አዲሱ ፓስፖርት ደህንነቱ የተጠበቀ እና በሀገር ዉስጥ የሚመረት ነዉ ተብሏል፡፡

ፓስፖርቱ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘዉ የለሚ ኢንደስትሪያል ፓርክ የሚመረት ሲሆን ጥራቱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡

በፓስፖርቱ ገፆች ላይ የሀገር ገፅታ የሚያስተዋዉቁ የኢትዮጵያ መለያዎች እንደተካተቱበትም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Alert News ‼️

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ የትግራይ ጸጥታ ኃይል አባላት በደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ ዓለም በተባለ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በነዋሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን አውግዟል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የተወሰኑ የክልሉ ጸጥታ ኃይል አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩን መዋቅሮች ለማፍረስ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው በማለት ከሷል። ጸጥታ ኃይሉ የአንድ ቡድን የሥልጣን መወጣጫ መሳሪያ ሊኾን እንደማይችል የገለጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ኹኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ክልሉ ከባድ ቀውስ ሊገባ ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ ትናንት የተወሰኑ የጸጥታ ኃይል አባላት የቀበሌ አስተዳደሩ ማኅተሙን እንዲያስረክቡ ባስገደዱበትና፣ በዚሁ ወቅት ድርጊቱን በተቃወሙ ነዋሪዎች ላይ የኃይል ርምጃ በወሰዱበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል ።


“ዘለንስኪ ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው” ትራንፕ 😂

“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነው” ብለዋል ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው” ሲሉ ወርፈዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው” ብለዋል።

ትራምፕ “ትሁቱና ውጤታማ ኮሜዲያን ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል” ብለዋል።

“ዩክሬን ጦርነቱን ያለ አሜሪካ እና ትራምፕ በፍፁም መቋቋም አትችልም” ሲሉም ገልጸዋል።

ዜለንስኪ ከላክንለት ገንዘብ ግማሹ “የጠፋ” መሆኑን አምኗል ያሉት ትራምፕ “ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም፣ በዩክሬን የሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት በጣም ዝቅተኛ ነው” ብለዋል።

“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።

“ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም” ብለዋል ትራምፕ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አክውም “ዩክሬንን እወዳለሁ፣ ነገር ግን ዘለንስኪ አስከፊ ስራ ሰርቷል፣ ሚሊዮኖችም ያለምክንያት ሞተዋል እየሞቱም ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ “ዶናልድ ትራምፕ የሀሰት መረጃ ውስጥ እየኖሩ ወይንም በሀሰት መረጃ እየተነዱ ነው” ብለዋል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የመሳይ መኮንን (ቦምብነሽ) ቦምቦች 😄

መሳይ መኮንን (ቦምብነሽ) አዲስ አበባ ላይ “አራት ቦምብ ፈነዳ” ብሎ ዘግቧል።😄 እንደዘገባው ከሆነ የነመሳይ ምናባዊ ቦምቦች የፈነዱት አንዱ አራት ኪሎ አካባቢ ነው። ሌላው ደግሞ ፒያሳ የከንቲባዋ office አካባቢ ነው 😄 አንዱ ደግሞ ፌደራል ፖሊስ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ቦሌ ኤርፖርት መግቢያ በሩ ጋር ነው 😄 (የነመሳይ ቦምቦች የፈነዱት የኮሪደር ልማቱን ተከትለው ይመስላል 😄)

የነመሳይ ቦምቦች ከአለም ለየት የሚያደርጋቸው አራቱንም ቦምብ መሀል ከተማ ውስጥ ሲያፈነዱ የአዲስ አበባ ሠው ምንም አለመስማቱ ነው 😄 በርግጥ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሰማነው ቦምቡን ያፈነዱት በሳቅ ነው ተብሏል 😄

ቦምቡ ፍቅርሽ ሲፈነዳ
ላንቺ ብዬ ገባሁ ዕዳ 😂

አይ ቦምብነሽ


ወይዘሮ ኬሪያ ኤብራሂም ‹‹የታክሲ ሰልፍ ጠብቄ እየሄድኩ ነው›› በማለት ተናገሩ፡፡ የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ በአሁኑ ወቅት ከቤተሰባቸው ጋር በአዲስ አበባ እንደሚኖሩ ገልፀው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከቪኦኤ ትግርኛ ቋንቋ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ‹‹እኔ ስልጣን ላይ በነበርኩበት ጊዜ አጃቢና ሹፌሮች ነበሩኝ፡፡ አሁን ግን የታክሲ ሰልፍ ጠብቄ እየሄድኩ እገኛለሁ፡፡ ምንም ችግር የለውም፡፡ ህይወት ይቀጥላል›› ብለዋል፡፡

ስልጣን መልቀቅ የህይወት መጨረሻና ሞት ማለት እንዳልሆነም አስረድተዋል፡፡ ‹‹በረሀ ወርደን መስዋእትነት የከፈልነው ለስልጣን ነበር ወይ?›› የሚል ጥያቄ ያነሱት ወይዘሮ ኬርያ ስልጣን መያዝ የመጨረሻ ግብ መሆን እንደሌለበት አሳስበው እሳቸው ግን እንደማንኛውም ሰው በህዝብ ጋር እየኖሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወይዘሮ ኬርያ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነታቸው በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ በጦርነቱ ወቅት ታስረው የነበረ ሲሆን ከእስር ከተፈቱ በኋላ ከህወሀት መባረራቸው ይታወሳል፡፡


Good Morning #Ethiopiaዬ : ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ አንካራ ውስጥ ያካሄዱትን የመጀመሪያ ዙር የቴክኒክ ድርድር ትናንት አጠናቀዋል።

ኹለቱ ወገኖች፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በአንካራው ስምምነት ያስቀመጡትን ራዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ መኾናቸውንና ኹለቱን አገራት ተጠቃሚ ለሚያደርግ ዘላቂ ልማት መሠረት መጣላቸውን በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

ኹለቱ ወገኖች ለኹለተኛው ዙር የቴክኒክ ድርድር በመጋቢት ወር ለመገናኘት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቅሰዋል።

በቴክኒክ ድርድሩ የኢትዮጵያን ልዑካን ቡድን የመሩት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሲኾኑ፣ የሱማሊያን ልዑካን ቡድን የመሩት ደሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ኦማር ናቸው።


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ዘመን ለአንድ አመት ተራዘመ።

ኮሚሽኑ ዛሬ የሦስት አመታት ሪፓርቱን ለፓርላማ ያቀረበ ሲሆን፣ የፓርላማ አባላት በሪፓርቱ ላይ የተለዩዩ ጥያቄዎችንና አስተየቶችን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ሦስት አመቱን የካቲት 14 ቀን በመድፈን የሥራ ዘመኑ ይጠናቀቅ የነበረው ኮሚሽኑ፣ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ የአንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶታል።

በቋሚ ኮሚቴው የተሰጠው የአንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ ውሳኔው የቀረበበት ሦስት የተቃውሞ ድምፅ ብቻ ነው።

በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ስላለው ሁኔታ የፓርላማ አባላት ያነሷቸውን ነጥቦችና የተሰጡ ምላሾችን በተመለከተ ተጨማሪ ይኖረናል።

18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.