ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb
+ ግሩፕ ለመቀላቀል +
https://t.me/NablisNablis
+ facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
TikTok
https://www.tiktok.com/@zdfitsumkebede1?_t=8pguEgtdsVq&_r=1

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 43ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የተሰማ ሪፖርት መካከል

1)ምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአንድ ዓመት ብቻ 271 ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በግፍ ተገድለዋል።

2)431 አብያተክርስቲያናት በአንድ ዓመት ብቻ ተቃጥለዋል።

ፈጣሪዬ ሆይ 😭

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


የፍቅር አይነቶች.pdf
5.5Mb
+ የተሳሳቱ የፍቅር ዓይነቶች + PDF.

ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው "መጽሔተ ወራዙት" በሚል እርዕስ ካዘጋቸው መንፈሳዊ መጽሐፍ የተወሰደ ።


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ ምልጃ ለምን ያስፈልጋል +

#የእግዚአብሔርን_ብዙኅ_ምሕረት_ብዛት_ እንድናውቅ ፦

እግዚአብሔር ከበደል በኋላ የሚጸጸት ሰው አለ የማይጸጸትም አለ እንደ በደለ አያውቅምና ። እንደ በደለም እያወቀ ልቡናውን የሚያገዝፍ አለ ። ሰው እንደበደለ በተሰማው በደሉም በቆረቆረው ጊዜ እግዚአብሔርን ይለመናልና ። ሲለምን ግን እግዚአብሔር እንዲሞረው የሚያሳስቡ ከእርሱ የተሻሉትን የሚበልጡትን እግዚአብሔር ደስ የሚያሰኛቸውን ሰዎች በማሳሰብ ነው ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሕረት ተሰፍራ የምትለካ ስላልሆነች ደጋጎቹን ባሰበ ጊዜ ብዙኅ ምሕረቱ ስለሚፈስስ ኃጥአንም ይቅር ይባላሉና ።

#እነ ሙሴ እነዳዊት ስለ እስራኤል ሲለምኑ በደጋጎቹ በኩል አድርገው ነበር ፤ ቅዱሳኑ በአካለ ስጋ ባይኖሩም እንኳን ስለ እነርሱ የሚያደርገው ምሕረቱ በዘመን የማይገታ በመኾኑ ።

"....ዘራቹሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ ይኽችንም የተናገርኳትን ምድር ኹሉ ለዘራቹሁ እሰጣለሁ ለዘለዓለም ይወርሷታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪዎችሆን አብርሃምንና ይሰሐቅን እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ላያደርግ ስላሰበው ክፍት ራራ። " ዘጸ.32፥13-14  ተብሎ እንደ ተጻፈው በዘመን የማይገታ የእግዚአብሔር ምሕረት በእስራኤል በደል ሳይገደብ በዝቶ የተደረገው ሙሴ አብርሃምን እና ይስሐቅን እስራኤል የተባለ ያዕቆብን አንስቶ ስለ ማለደው ነው ።

ሙሴ የእግዚአብሔር ብዝኅ ምሕረትን በቅዱሳን ስም የሚማለድ መኾኑን ስለ አወቀ አደረገው እንጂ እኔ በቃለሁ አላለም ስለዚህ እግዚአብሔር ምልጃን የፈቀደው በዘመን የማይገታ ምሕረት ያለው መኾኑን አውቀን እንድንጠቀም ነው ። "ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ ለአብርሃም ለዘሩ የዘላለም ምሕረቱን አስቦ እስራኤልን ብላቴናውን ረድቷል ።" ሉቃ 1፥55 እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር በቅዱሳኑ በኩል ዘለዓለማዊ ምሕረትን አድርጓል ። ክብሩ ፣ ገናንነቱ ፣ ጌትነቱ የሚታወቀው በእነርሱ ስም በማለድነው ጊዜ ነው ።


#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ


+ ተለቀቀ +

🩸 አዲስ ድንቅ ዝማሬ 🩸

በ5ቱ ዘማርያን🔊

👇👇 👇👇
OPEN   OPEN OPEN 
OPEN   OPEN OPEN 
OPEN   OPEN OPEN


+ የእመቤታችን ምስጋና ትርጓሜ +

የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈስ ቅዱስ ያደረባትን የኤልሳቤጥን ምስክርነት ከሰማች በኋላ "ነብሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ በመድኅኒቴ ሐሤት ታደርጋለች" በማለት ክብር የባሕርይ ገንዘቡ የኾነ በማሕፀኗ በፈቃዱ ያድር ዘንድ ለወደደ ለአምላኳ ያላትን ክብር ገልጻለች ነብዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ በመንፈስ እግዚአብሔር ተቃኝቶ በምዕ ፳፩-፲ ላይ ፦ "አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ በጌጥ ሽልማቷም እንዳጌጠች ሙሽራ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና የጽድቅንም መጎናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች " በማለት ትንቢት እንደተናገረ ቅድስት ድንግል ማርያምም የንጽሕናን የቅድሰት ጸጋና ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ ለመሸከም ያበቃትን ርሱን ደስታን በተመላ በዚኽ ቃል አመሰግናለች።


ሐሴት" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሳ ዘጠኝ ግዜ በላይ ሲጠቀስ ክቡር ዳዊት በመዝ ፷፯-፫ ላይ " ጻድቃንም ደስ ይበላቸው በእግዚአብሔርም ፈት ሐሤት ያድርጉ በደስታም ደስ ይበላቸው" ሲል ነቢዩ ዕንባቆምም በምዕ ፫፥፲፰ ላይ "እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኅኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለኁ " በማለት ፈጣሪውን እንዳመሰገናት "ደስተኛዩቱ ደስ ይበልሽ " የተባለች የባሕርይ አምላክን በማሕፀኗ የተሸከመች ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇን "መንፈሴም በአምላኬ በመድኅኒቴ ሐሤት ታደርጋለች " በማለት በደስታ ኾና አመሰገነችበት ። ( "ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን" በመጋቢ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ገጽ 205-206)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


ነገ አይቀርም

+ የመጽሐፉ ምረቃ +

ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም
ከቀኑ 7:30
አሐቲ ድንግል አዲስ መጽሐፍ!
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
    
የመርሐ ግብሩ መሪ መምህር ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ

የመጽሐፍ ዳሰሳ በቀሲስ ግርማ ባቱ እና በዶ/ር አባ ሃይለ ገብርኤል ይቀርባል። ትምህርተ ወንጌል በየኔታ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ይሰጣል!! ቦታ ቦሌ መድኃኔዓለም  ቤተክርስቲያን።
 
  በዕለቱ ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ!!
  የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ ማህበረ ጽዮን!!!


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ ዕረፍታ ለቅድስት አርሴማ +

ሴቶች እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ
(ዕብ 1፥35)

ቅድሰት አርሴማ ሰማዕቷ ። በአርመንያ ታኅሣሥ 6 ቀን ሐሙስ ዕለት ተወለደች ። አባቷ ቴዎድሮስ አትናስያ ይባላሉ ። የነበረችበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት በመባል ይተወቃል ። ዲዮቅልጥያኖስ ቆንጆ ሴት ፈልጋችሁ አምጡልኝ ብሎ ሠራዊቱን በየሀገሩ ላከ አምጡልኝ ሲላቸው አርሴማ በተራራ ተቀምጣ ነበር ፤ እርሷም የእግዚአብሔር መንፈስ ተገልጦላት ወደ አርመንያ ሄደች ። ይህንን ሰምቶ ለንጉሡ ለድርጣድስ አሰፈልገህ ላክልኝ ብሎ ላከበት አስፈልጎ አገኛት እርሷም መልከ መልካም ሴት መሆኗን አይቶ ይህችንስ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም ብሎ ዶርታንን ለምኚልኝ አላት ለመንግሥተ ሰማያት የታጨሽ ነሽና ይህ አላዊ እንዳያረክስሽ አለቻት መልኳን አይቶ በስሜት ተሸንፎ ዘሎ ያዛት ከእግዚአብሔር ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷልና ጎትታ ከመሬት ጣለችው ። በሰይፍ መስከረም 29 ቀን አሰቆረጣት በ27 ዓመቷ በሰማዕትነት በዚህ ዕለት አረፈች ። ( ፍኖተ ስብከት ሊቀ ስዮማን አዲሱ ላቀው ገጽ_37 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ የበረከት ጥሪ +

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማን ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረከሰ ዝክር ለመዘከር የሚሆን የ1እንጀራ ዋጋ 25 ብር ነው ። ይሄን ስናደርግ 250 እንጀራ ያክል ያስፈልገናል በቦታው ላሉ አገልጋዮች እንዲሁም ለምዕመናን ለነዳያን የሚሆን ።
ስለ ሰማዕቷ ከበረከቱ ተሳተፍ ። 🙏

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
1000441182345
ማህበረ ኤዶምያስ
ስልክ ቁጥር ተጨመሪ መረጃውችን መጠየቅ ይችላሉ ።
0967722490
ሲገባ ስክሪን ሹት እና ክርስትና ስም ይላኩልን @Joseph2716 👈። 🙏🙏


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


#አዲስ_ዝማሬ

ታላቆቻችን በትልቅ ስራ ሲገለጡ ማየት ያስደስታል ።

ዘላለም ከአፌ ማይለይ ስም ማርያም ይህ በተጨማሪ ዝማሬዎች ለመረስረስ መንገድ ነው ። ❤🙏

ዘ/ዲ ሙሴ ሚኒልክ ፀጋውን ያብዛልህ ። !!


https://youtu.be/JNH8WKCLhC4?si=SALX3vz-1hx-8aSb


#ወተትና ማር

ከዚህም ማወቅ ያለብን ነገር ወተት በድመት ከተወደደው በላይ በሰው ልጅ ዘንድ ቃለ እግዚአብሔር ሊወደድ ይገባል የሚለው ነው ። ምክንያቱም በመጽሐፍት ወተት ተብሎ ከተገኘ ቃለ እግዚአብሔር ማለት ነው ። እግዚአብሔር ለአብርሃም ከነዓንን ሊያወርሰው ወተት እና ማርን የምታፈስ ሀገር ብሎታል ። በእውኑ ወተት እና ማር ከሰማይ የሚፈስባት ሀገር ማለቱ ይሆንን ? ብለን ብንጠንቅ ይህ እንዳልሆነ በኋላ የአብርሃም ልጆች እነ ያዕቆብ በረሃብ ምክንያት ከነዓንን ለቅቀው ሲሰደዱ እናያለን ። ወተት እና ማር የምታፈስ ከሆነ ለምን ራባቸው ? እንዳንል በቁሙ ወተት እና ማር እንዳይደሉ እንረዳለን ። ወተት እና ማር ካልሆኑ ምንድን ናቸው ። ካልን ማር የተባለች ብሉይ ኪዳን ፣ ወተት የተባለች የተባለች ሐዲስ ኪዳን መሆኑን መተርጉማን ያሰረዳሉ ።

ለምን ብሉይ ኪዳን በማር ፣ ሐዲስ ኪዳን በወተት ተመሰሉ ብለንም ማሰባችን ስለማይቀር ማር በእጅ ሲነኩት እጅን ጭምድድ አድርጎ ይይዝና ምንም የሚለቅ አይመስልም ፣ ግን ትንሽ ውኃ ሲታጠቡት በፍጥነት ይለቃል ወተት ግን በተለይ ቅቤው እንደነኩት ወዲያው የሚለቅ ይመስልና ውኃ ሲያስነኩት ግን የበለጠ የማይለቅ እየሆነ ይመጣል ። በመሆኑም ዘመን ባመጣው ሳሙና ካልሆነ እንዲሁ በውኃ ብቻ ይለቃል ተብሎ የማይታሰብ ነው ። ኦሪትም በስድስት መቶ ሺህ እስራኤላውያን መካከል ስትሠራ የማታልፍ ትመስል ነበር ግን ለጥቂት ጊዜ አገልግሎት ሰጥታ አለፈች ወንጌል ግን በመቶ ሃያ ቤተ ሰብእ ላይ ተመስርታ ትጠፍለች ስትባል እንደ መንጠር እሳት እየተቀጣጠች ዓለም እስከ ዘለዓለም የማታልፍ ሕግ ሆና ቀርታለች ። ( ምዕላደ ጥበብ ፪ መምህር በጽሐ ዓለሙ ገጽ 307-308)


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ ዘመነ ጽጌ +

ዘመነ ጽጌ ሰው ዘመኑ እንደ አበባ በቶሎ የሚረግፍ መሆኑን በማሰብ ይህ ዘመን ሳያልፍ መልካም ሥራ ለመሥራት ትንሣኤ ኅሊና የሚነሣበት ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለዘመነ ጽጌ የሠራው ድጓም ይህንኑ የሰውን ዘመን አጭርነት የሕይወቱን ኢምንትነት በዚህ ሕላዌ የተፈጠረ ሰው በዚህ ዓለም ክፉ ሥራ መሥራት እንደሌለበት ሁልጊዜ በተዘክሮተ ሞት እንዲኖር የሚያስረዳ ነው፡፡ በዘመነ ጽጌ ቅዱስ ያሬድ ከደረሰው ድጓ በተጨማሪ ከላይ እንደተጠቀሰው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሣ አባ ጽጌ ድንግል ከዚሁ ዘመን ጋር የተያያዘ ድርሰት ደርሷል፡፡

ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ በአብዛኛው አምስት ስንኞች ያሉት ሲሆን ብዛቱም 15ዐ ያክል ነው፡፡ ይህም ድርሰት «ማኅሌተ ጽጌ» በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘው ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚያስረዳ ድርሰት ነው፡፡ እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ደግሞ ልጇን በአበባ እየመሰለ ይናገራል።

ነቢዩ ኢሳይያስ «ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓርግ ጽጌ እምጉንዱ፤ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል» /ኢሳ.11፡1/ ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል፡፡ እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን ማኅሌተ ጽጌን እንዲደርስ አድርጋዋለች፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ማኅሌተ ጽጌ በመልክዕ አደራረስ ሥርዓት የተደረሰ ሲሆን ይህንንም ለመመልከት እንዲያመች በሚከተሉት ክፍሎች ከፋፍሎ ማቅረብ ይቻላል፡፡

( ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


🩸የዕለተ ሰንበት እንግዳ 🩸

በዕለተ ሰንበት (ዕሁድ) በዐውደ💭 ወንጌል ኦርቶዶክሳውያን የቴሌግራም ገጽ በቀጥታ ሥርጭት (Live)  ላይ ይገኛሉ !

     🔔 ቀሲስ ዘማሪ አሸናፊ ገ/ማርያም🔔

✅ኑ በአካል ብንራራቅ በመንፈስ✅ አንድ ላይ ሆነን በዝማሬ እንረስርስ 👇👇


Awude_wengel
Awude_wengel
Awude_wengel


ይህቺ ልጅ ሜሮን ካፒታ ትባላለች የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ ስትሆን የሶስተኛ አመት የፋርማሲ ተማሪ ነበረች አሁን ላይ ግን የኩላሊት ታማሚ ሆና በአልጋ ላይ ትገኛለች። በአዲስአበባ ታዝማ የዉስጥ ደዌ የህክምና ማእከል ዉስጥ የምትገኝ ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቶቿ መስራት ስላቆሙ በእጥበት ላይ ትገኛለች። እናም ይህ እጥበት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ወደ ህንድ ሀገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንድታደርግ ተብላለች። ቤተሰቦቿም የተጠየቁትን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻላቸው ለእርዳታ እጃቸዉን ዘርግተዋል እናንተም የተቻላችሁን እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን እህታችን ሜሮንን እናድናት።
ሰዉን ለመርዳት ሰዉ መሆን በቂ ነዉ።
1000021582046
KAPITA WALCHA MENGESHA


+ በወለደች ትሞታለች +

የእፍኝት (አርዌ ገሞራዊት )ልጆች በእናታቸው ማሕፀን ሲፀነሱ በእናታቸው ምክንያት አባታቸው ተገድሎ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ሲወለዱ የእናታቸውን ሆዷን ቀድደው በመብላት ነው ከእናታቸው ማሕጸን የሚወለዱት ። ለዚህም ምክንያታቸው የእናታቸው አፈ ማሕጸኗ ጠባብ በመሆኑ የሚፈጠር ክስተት መሆኑን ሊቃውንት ያስረዳሉ (ምዕላደ ጥበብ ቅጽ ፩) ። በመሆኑም እፍኝትን ልጆቿ የሚበሏት ከውስጥ ከሆዷ ጀምረው ወደ ውጪ ነው ። እንዲህ አድርገው በልተው ሆዷ ሲቀደድላቸው ይወለዳሉ ። የሸረሪት ደግሞ ሲጀመር የሚፀነሱት እንደ ዕንቁላል ባለ ነገር ውስጥ ነው። እንዳንድ ጊዜ በመጨረሻ አካሏ ይዛው ትንቀሳቀሳለች ፣ አንዳንድ ጊዜም አስቀምጣው ስትንቀሳቀስ ትታያለች ።

በመጨረሻም በሚወለዱበት ጊዜ ገስግሰው ሒደው እናታቸውን ይወሩና ይበሏታል ሸረሪት በተፈጥሮ አጥንት የሌላት በመሆኑዋ ምንም ቅሬታ አካል ሳይኖራት ተበልታ ታልቃለች ። ስለዚህ የሸረሪት ልጆች እናታቸውን ሲበሉ ከውጭ ጀምረው ወደ ውስጥ ነው ። እስኪ አሁን ተመልሰን ኢትዮጵያን እናስባትና እንደ እፍኝት ከውስጥ ወደ ውጭ እንደ ሸረሪት ደግሞ ከውጭ ወደ ውስጥ በሁለቱም የአበላል መንገድ አይደለምን ? እየተበላች ያለችው እንዲህም ስተበላ ይህ ዘመን የመጀመሪያዋ አለመሆኑ ከአለፈ ታሪክም መረዳት ይቻላል ። ( ምዕላደ ጥበብ ቁጥር ፪ በመምህር መምህራን በጽሐ ዓለሙ ገጽ 121-122 )


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


የመጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብር ላይ ይሳተፉ።

-የአባ ገብረ ኪዳን ግርማ "አሐቲ ድንግል" የተሰኘ መጽሐፍ ቅዳሜ ጥቅምት 2 በቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ይመረቃል። ስለዚህ የመጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብር ላይ ይሳተፉ።

-ሰዓት 7:30

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


#ሚካኤል ማለት መሓሪ ወመስተሣህል ዕፁብ ማለት ነው። ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ገብር ወአግዓዚ ማለት ነው። ማርያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው ። ዳዊት ማለት ፍቁር ልበ አምላክ ማለት ነው። #ሰሎሞን ማለት መስተሣልም ማለት ነው። #ሳሙኤል ማለት ሰምአኒ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ የጌታን መታጠቂያ ከታጠቀ በኋላ ፍትወት እንስሳዊት ከባሕርይው ጠፍታለች። የሙሴ የቀድሞ ስሙ ምልክአም ነው ። ምልክአም ማለት መልአከ እግዚአብሔር ማለት ነው። #አሮን ማለት ደብር ማለት ነው። #ዘካርያስ ማለት ዝክረ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል መጋቤ ሐዲስ ነው ። ቅዱስ ሚካኤል መጋቤ ብሉይ ነው። የእግዚአብሔር መዓቱም ምሕረቱም በእውነት ይደረጋል። በአፀደ ቤተክርስቲያን በመዓልት 600፣ በሌሊት 600 መላእክት ይኖራሉ። ቤተክርስቲያንን ይጠብቃሉ። የእግዚአብሔር ባሕርዩ በዚህ ጊዜ ተገኘ አይባልም። በባሕርይው አስገኝ ምክንያት የለውም። ክርስቶስ ራሱን በመስቀል ሠውቶ አስታርቆናልና ሊቀ ካህናት ይባላል። የእግዚአብሔር ሥልጣኑ የባሕርዩ ነው። ጌታ በተወለደ ጊዜ መላእክትና ኖሎት በአንድ ላይ አመስግነዋል። ቄሱ ከሕዝቡ ኃጢአት ንጹሕ ነኝ ሲል እጁን ይታጠባል።

(መምህር በትረ ማርያም አበባው)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


ሰንበት ተማሪነት!
......
ከላይም ከታችም ልትሰደብ ትችላለህ ... መሳሳት በፍጹም አይፈቀድልህም ... ምናልባት ከታናሽ እህትህ ጋር ሊሆን ይችላል ከጉባኤ አምሽተህ ወደቤት እየገባህ ያለኸው ... ነገር ግን የሚያየው ሁሉ ሰው ስም ያወጣልሃል ... ባለጌዎች ናቸው ልትባል ትችላለህ ፡፡፡ ሕጉን ስርአቱን የሚያውቀውም ... ዛሬ ቤተክርስቲያን የመጣውም ሊቆጣህ ሊያዝህ ይችላል፡፡፡ አንተ ግን ምንም አትልም ... በፍጹም ትህትና አገልግሎትህን ታገለግላለህ ... ምክንያቱም.............
ሙሉውን ለማንበብ ከታች ባለው ሊንክ አሁኑኑ ይቀላቀላሉ። 😍


+ ተአምራትን እንዴት እናያቸዋለን? +

መጽሐፍ ቅዱስ ‘የሐዋርያት ሥራ’ን የመሰሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ኃይል የሠሩትን ሥራ የሚተርኩ መጻሕፍት ያለበት መጽሐፍ ነው፡፡ ‘የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው’ በማለት ሕያዋን መጽሐፍት ወይም ተንቀሳቃሽ መጽሐፍ ቅዱስ /Living bible or
moving bible/ ተብለው የሚጠሩትን የቅዱሳንን ሕይወት እንድናጠና እና በኑሮአቸው እንድንመስላቸው ያሳስበናል፡፡
(ዕብ. 13፡7) ቅዱስ ጳውሎስ ‘እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ’ ብሎ እንደነገረን ክርስቶስን ለመምሰል የጳውሎስን የሕይወት ታሪክ ማጥናት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ (1ቆሮ. 11፡1) ራሱ ጳውሎስም

ከእርሱ የቀደሙ የእምነት አርበኞችን አስደናቂ ታሪክ ከዘረዘረ በኋላ ‘ሁሉን እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል’ ብሏል፡፡
(ዕብ. 11፡32) ጳውሎስ የቅዱሳኑን ታሪክ ለመተረክ ያጠረው ጊዜ እንጂ ፍቅር አልነበረም፡፡እግዚአብሔር በቅዱሳኑ አድሮ ያደረገውን መስማትም የቅዱሳን ታሪክ አካል ነው፡፡ ‘በሐዋርያት እጅ ብዙ ድንቅና ምልክት ተደረገ’ ‘እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር’ እንደሚል እግዚአብሔር
በባሪያዎቹ እጅ ታላላቅ ተአምራት ያደርጋል፡፡ (ሐዋ. 2፡42 ፣ 19፡11) የእስራኤል ንጉሥ ‘ኤልሳዕ ያደረገውን ተአምር እስቲ ንገረኝ’ እያለ ግያዝን እየጠየቀ በደስታ ይሰማ እንደነበረ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ያደረጉትን ተአምር መስማት ለምናምን ሰዎች እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ (2ነገሥ. 8፡4)

( ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


🙏 እህታችንን እንታደጋት🙏

የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት ጎበዝ ተማሪ የነበረችው ሊዲያ ሥዩም፣ ተመርቃ ለቤተሰቦቿ መከታ የመሆን ሕልሟ ላይ brainsteam cavernoma የተሰኘ የጭንቅላት ሕመም ጋሬጣ ሆኖባት፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ትገኛለች።

ይህች ምስኪን ልጅ በውስጠኛው የአእምሮ ክፍል ውስጥ የደም ሥር መወሳሰብ በፈጠረው መድማት ሳቢያ እንደ ስትሮክ እየሆነባት ትገኛለች።

ሕመሙ በሀገር ውስጥ ሕክምና ሊገታ ስላልተቻለ በሀገረ ሕንድ ሄዳ እንድትታከም የጥቁር አንበሳ ቦርድ ወስኗል። ለአጠቃላይ ወጪም እስከ ሁለት ነጥብ ሦስት ሚልየን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን በጸሎታችሁ እንድታስቡ እንዲሁም ከታች በተጠቀሰው አካውንት የአቅማችሁን በማበርከት ከጎናችን እንድትሆኑ ሲሉ ቤተሰቦቿ በእግዚአብሔር ስም ይማጸናሉ።

ከዚህ በኋላ የውስጠኛው የአእምሮ ክፍል ውስጥ የሚደማ ከሆነ፣ እጅግ ለከፋ ችግር ስለምትጋለጥ፣ እርዳታችሁን በአፋጣኝ እንሻለን።

1000027428162 = CBE
Seyoum Zewdie (አባቷ)

01336511809500 Abenezer Seyoum(ወንድም ) Awash

44516721 = Abysinia
Abenezer Seyoum (ወንድም )

ስልክ: 0932588260 (Abenezer Seyoum )

የጎ ፈንድ ሚ : https://gofund.me/063f71fb

እናመሰግናለን 🙏🙏🙏


+ መስቀልም ምስጋና ይገባዋል ማለት...

ሠሞኑን ከምንሰማቸው ትችቶች አንዱ "መስቀል መከበሩንስ ይከበር፤ ግን እንዴት እንደሚሰማ አካል ምስጋና ይቀርብለታል?" የሚል ይገኝበታል። ይህም "ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምሥጋና ይገባል፤" የሚለውን እና ተመሳሳይ የቤተ ክርስቲያን ጸሎቶችን በመተቸት ነው።
ይህ ትችት መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የንግግር ዘይቤ ያለማወቅ (ወይም ሆን ብሎ ማሳሳት) የሚያመጣው ችግር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መስማት የማይችሉ ነገሮችን እንደሚችሉ ቆጥሮ ቅኔያዊ በሆነ መንገድ (personification) ይናገራል። ለምሳሌ ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ፤" ይላል። (ዘዳግም 32÷1) ክቡር ዳዊትም ጌታችን የተጠመቀባትን ዮርዳኖስን በትንቢት ቃል ያወራታል፦ "አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ፥ምን ሆናችኋል?" (መዝሙር 114/115÷5) ሰሎሞንም በምሳሌው ጥበብን እየዞረች የምትናገር ሴት አድርጎ ያቀርባታል፦ "ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፤ በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤" (ምሳሌ 1÷20)

መስቀልም ምስጋና ይገባዋል ስንል የሚሰማ እና ነፍስ ያለው (personal) አድርገነው ሳይሆን እግዚአብሔር ትልቅ ሥራ የሠራበት ክቡር ነገር መሆኑን ጠለቅ ባለ ቅኔያዊ ቋንቋ የተገለጸበት መንገድ ነው። ሥርዓተ አምልኮ እግዚአብሔርን እና የከበሩ ሥራዎቹን የምንናገርበት እና ምሥጋና የምናቀርብበት ልባዊ ግብር በመሆኑ ጥልቅ እና ቅኔያዊ አገላለጾች አስፈላጊ ናቸው። በሥርዓተ አምልኮ ቀጥተኛ (plain) ቋንቋ ብቻ መጠቀም ለግብሩ ታላቅነት አይመጥንምና።

(በረከት አዝመራው)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.