Orthodox Mezmur Channel


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


✞✞✞ Orthodox Mezmur Channel ✞✞✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቆየት ያሉ እና አዳዲስ መዝሙሮችን ያገኛሉ።
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

ለማንኛውም ሀሳብ ፣ ጥቆማ ፣ አስተያየት
👇👇👇
@Orthodox_Mezmurs
@Orthodox_Mezmurs

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


❤️ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤️

ጥር 23 ቀን

ሐዋርያው ጢሞቲዎስ (እረፍቱ)

እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ (በመንፈስ ልጁ) ለሆነው ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ለዕረፍት በዓል ፣  ለጻድቁ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ለመታሰቢያ በዓሉና ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።


ኡራኤል ብርሃና ለኢትዮጵያ | ዘማሪ ዲያቆን ሳይዛና ጌታቸው

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


መልአኩ ዑራኤል | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ዑራኤል | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ቅዱስ ኡራኤል መልአከ ሰላምነ | ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤

ጥር 22 ቀን

ቅዱስ ኡራኤል
/ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሾመበት ቀን/


🌹በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሰረት ከሰባቱሊቃነ መላእክት አንዱ ነው

🌹ዑራኤል: ማለት ትርጉሙ የብርሃን ጌታ የአምላክ ብርሀን ማለት ነው ከፍጥረተ አለም ጀምሮም በመብረቅ እና በነጎድጓድ ላይየተሾመ ሀያል መላእክ ነው ምስጢረ ሰማይንም ለሔኖክ ገልጿል

🌹ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል በሠረገላ ብርሃንም ጭኖ አስቀድሞ ገነትን በመቀጠልም ሲኦልን አስጎብኝቷታል

🌹በስደቷም ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ መምጥቷታል በክንፍ ተሸክሞም በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል

🌹ጌታችን በተሰቀለም ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጎ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል

🌹እውቀትን ጥበብን በመግለፅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘ ጋሰጫ ድንቅ አድርጓል

🌹በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ አብዛኞቹ ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው

🌹ጥር 21 ቅዱስ ዑራኤል የተሾሙበት ነው በረከቱ ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ከሕዝቦቿ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን 🌹














❤️ ለጥር አስተርዮ ማርያም የሚዘመሩ መዝሙሮች 👇


❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤

            ጥር ፳፩ 21 ቀን

የእመቤታችን በዓለ እረፍት

/አስተርእዮ ማርያም/

❤ እንኳን አምላክን ለወለደች ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለዕረፍቷ በዓል (ለአስተርእዮ ማርያም) በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።




ሙሽሮች በጌታ ደስ ይበላችሁ | ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ

ሙሽሮች በጌታ ደስ ይበላችሁ
ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ
/2/
የበረከት አምላክ ይግባ ከቤታችሁ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፍቅርን ያላብሳችሁ
/2/

ለሰው ኹሉ ይታወቅ ይገለጥ ሥራችሁ
ለአምላክ ክብር ይኹን ይባረክ ሰርጋችሁ
በጸሎት በምልጃ ከምስጋና ጋራ
ለእግዚአብሔር አስታውቁ ኹሉን ያውቃልና
      አዝ =======
የእግዚአብሔር ሰላም እንዲበዛላቸው
በእውነት ይታነፅ የትዳር ኑሮዋቸው
ጽድቅ ይሞላበታል ፍጹም ንጽህና
የፍቅር ባለቤት ክርስቶስ ነውና
      አዝ =======
መልካም ዜና ኾኖ በዓለም ይነገራል
በደስታ በሐሤት በመንፈስ ይፀራል
ሀሌ ሉያ ለእርሱ ዘላለም ምስጋና
የአርያም ዝማሬ ይገበዋልና
አዝ =======
እምነት ተስፋ ፍቅር ሦስቱም ይኖራሉ
ከኹሉ በሚበልጥ በፍቅር ይጸናሉ
አንድነት የሰጠን አንድ አምላክ ነውና
ጌታን እንልበሰው ፍቅር እርሱ ነውና

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


"ሙሽሮቹ ዛሬ አምረን ተውበናል"

የቤታችን ራስ የኑሮአችን ውበት
አንተ ነህ ለዚህ ቀን ያደረስከን በእውነት
ሙሽሮቹ ዛሬ አምረን ተውበናል
ፍቅራችንን አጽና አንድ ለአንድ ሆነናል

አዝ =======

አብርሃም ቢታዘዝ ለአንተ በቅንነት
ይስሐቅን ሰጠኸው የምድርን በረከት
ግባ ከቤታችን ተገለጥ በፍቅር
ማን ያፍራል ያመነህ ሳይጠራጠር /2/ 

አዝ =======

የተማማልንበት ቃል ኪዳኑ ይጽና
በልጅ በበረከት ጎብኘን በጸጋህ ና
ሥጋና ደምህ አድርጎናል አዲስ
በቤትህ በቅጥርህ አጽናን በመንፈስ /2/ 

አዝ =======

በፍቅር በምግባር ዙሪያችን ይታጠር
ከእኛ ሕይወት ዓለም በጎ እንዲማር
እጅግ አትራፊ ነው አንተ ያለኸው
በምስጋና ይጽና ደጁን ጠብቀው /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ሙሽራውን ያከበረው ሙሽሪትን ያከበረው | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እንደ እርሱ ማነው? /4/
ሙሽራውን ያከበረው ሙሽሪትን ያከበረው
እንደ እግዚአብሔር ያለ እንደ እርሱ ማነው? /2/

የባሪያዪቱ ልጅ እስማኤል አይወርስም
በክብር የሚመጣው ይስሐቅን አይቀድምም
የአጋር አይደለም ሣራ ሆይ ትዳርሽ
በሳቅ ይሞላሻል ጌታ ስለ እምነትሽ
      አዝ =======
በቤርሳቤህ በዚያ ምድረ በዳ
ይስሐቅ የለበትም የሚከፍለው ዕዳ
ከተቀደሰው ዘር ኾኗል እና ግንዱ
መልአኩን ሰዶለት ይቀናል መንገዱ
      አዝ =======
የአጥንቱ ፍላጭ አትቀርም ርብቃ
ጸንታ ትኖራለች ለእርሱ ተጠብቃ
የእግዚአብሔር መልአከ ከሎሌው ቀደመ
አክሊልና ርስቱን ይስሐቅ ተሸለመ
      አዝ =======
ታርፋለህ በርብቃ ይስሐቅ ትረካለህ
አትደንግጥ ከእንግዲህ ብቻህን አይደለህ
የቅዱሳን ትዳር የእናትና አባትህ
ዛሬም ከአንተ ጋር ነው ዘላለም አይጥልህ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.