✅✅✅✅
"#ምስክሮችህ #ድንቆች #ናቸው፤#ስለዚህ #ነፍሴ #ፈለገቻቸው።"(መዝሙረ ዳዊት 119፥129)
#ሰማዕት ማለት በአጭሩ #ምስክር ማለት ነው፤ስለእግዚአብሔር መንግስት ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ የሰጠ ማለት ነው።#እስጢፋኖስ ማለት ደግሞ ወደብ ጸጥታ ማለት ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ነው።"ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ለምን ቀዳሚ ሰማዕት ተባለ ከሱ በፊት ሰማዕታት የሉም ነበርን?"ቢሉ መኖርስ አሉ እርሱ ግን ቀዳሚ ሰማእት መባሉ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኃላ ስለ ጌታችን መውረድ መወለድ መሰቀል መነሳት... መስክሮ ሰማእትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ሰማእት እርሱ ስለሆነ ነው።
👏😇👏ቅዱስ እስጢፋኖስ ለምን ሊቀ ዲያቆናት ተባለ ቢሉ በሐዋርያት እጅ ከተሾሙት ሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የሁሉም አለቃ እርሱ ስለሆነ ነው።
👏😇👏 (የሐዋ ሥራ 6 ፥5)
መጽሐፍ ቅዱስ ስለእስጢፋኖስ እንዲህ ሲል በእውነት መሰከረ "እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበረ...ፊቱም የመልአክ ፊት ይመስል ነበር ፤ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም።
👏😇👏(የሐዋ ሥራ 6፥8) አይሀድ አማጽያን መልስ መስጠት ቢያቅታቸው ድንጋይ አነሱ ልቡን አናቱን ጭንቅላቱን... እያሉ ወገሩት፤ ቀና ብሎ ቢመለከት ቅድስት ሥላሴን አየ፤ "አቤቱ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው ይቅር በላቸው" እያለ ነፍሱን ሰጠ።
👏😇(የሐዋ ሥራ 7፥60)👏😇
👏😇👏ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወለደው በኢየሩሳሌም በምትገኝ ሐኖስ በተባለች ቦታ ነው:: አባቱ ስምዖን ሲባል እናቱ ደግሞ ሐና ትባላለች ነገዱ ከነገደ ብንያም ነው።የኦሪትን ሕግና ሥርዓት ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ተምሯል::በሐዋርያት ሥራ ምዕ. 6 እንደምናነበው ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋ፤ ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ( ሊቀ ዲያቆን) ሆኖ ተሾሟል ይህም የሆነው በጥቅምት 17 ነው።
👏😇👏ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር፤ ተአምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር ።
✅በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል። በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን (እግዚአብሔርን በአንድነቱ በሦስትነቱ ) ተመለከተ።
🙏💒🙏💒ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ "ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው "በመጨረሻም "ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል" ብሎ ነፍሱን ሰጠ ።(የሐዋርያት ሥራ ምዕ 7) በተወለደ በ 30 ዓመቱ በ35 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ።
🙏💒🙏⛪ጌታ እኛንም መከራውን ፈተናውን አስችሎን የዘመኑን ሰማእትነት አልፈን እውነተኛ ምስክሮቹ ለመሆን ያብቃን!
ከሰማዕቱ ከቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት ያሳትፈን አሜን! ከእኔ የበረታችሁ አስቡኝ በፀሎታችሁ ገብረመስቀል
👏😇ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
👏😇ወለ ወላዲቱ ድንግል👏😇
👏😇ወለ መስቀሉ ክቡር👏😇
🙏አሜን🙏አሜን🙏አሜን🙏
@ortodox_27