📘#ተአምር አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ🌹
📕☞ወር በገባ በ12 የአባታችን የበርሃው መናኝ የአባ ሳሙኤል (ዘዋልድባ)ወራሒው መታሰቢያው ነው፡፡☞ህግን የሚጠብቅ ትእዛዝን የሚፈጽም የነብያትና የሐዋርያት ወገን በሽተኞችን የሚፈውስ የነፍሳት መድኃኒት የእግዚአብሔር ሰው የማር አባ ሳሙኤል ታምር ይህ ነው፡፡
☞የከበራችሁ አሕዛብ ሆይ አባታችን ብጹአዊ ማር አባ ሳሙኤል ከተማሪዎቹ ጋር አርብ ቀን በገዳም ውስጥ ሲመላለስ እግዚአብሔር ያደረገውን እነግራችሁ ዘንድ በማስተዋልና በጥበብ ስሙ፡፡
☞ምሽት በሆነ ጊዜ በአለት መካከል አደሩ፤ የሚመገቡትም አጡ፡፡ አባታችን
ብቻውን ራቅ አለ፡፡ ☞እጆቹን ዘርግቶ አይናቹን አንጋጦ ወደ አምላኩ፤ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እንዲህም ብሎ አቤቱ ሰውን የምትወድ የምሕረት አምላክ ፍጥረትን የምትወድ የምህረት አምላክ ፍጥረትን ሁሉ የምትመግብ በበረሃ አረባ ዘመን ሳይዘሩ ሳይሰበስብ እስራኤል የመገብካቸው አሁንም ለተቸገሩት ለእነዚህ አገልጋዮች ምግባቸውን ስጣቸው፡፡
☞እንደዚህ ከጸለደ በኀላ ተማሪዎቹ ወደ አሉበት የእግዚአብሔር ስልጣን ይዞ
ተመለሰ በአደሩበት በዚያች እለት ላይ ሦስት ጊዜ ባረከ ከትልልቅ አሳዎች ጋር
በእርሱ ውኃ ፈለቀ፡፡
☞ብጹአዊው ከእስራኤል ልጆች ወገን የሆኑ ልጆቹን ይህች ዉኃ ከዚህ ዓሣ ጋር
ተሰጠኝ በይቅርታው ብዛት ይህን ስለሰጠን እግዚአብሔር እያመሰገናችሁ
ለቀዳሚት ሰንበትና ለእሁድ የሚያበቃንን ያዙ አላቸው፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ነውና፡፡
☞ከእርሱ ይህንን ነገር በሰሙ ጊዜ አባታችን ብጹአዊ ማር ሳሙኤል ያደረገውን
ተአምር አይተው ፈጽመው ተደሰቱ፡፡ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡
☞እንደ አዘዛቸው አደረጉ፡፡ ለሁለት ቀኖች ያህል ከሰበሰቡት እየተመገቡ
ተቀመጡ፡፡
☞ሁለተኛ ቀን ሰኞ በነጋ ጊዜ የተረፈውን ምግባቸውን ይሰበስቡ ዘንድ
ተማሪዎቹን ዳግመኛ አዘዛቸው በዚያምች ውሃና ተይዘው በተበሉት በእነዚያም
አሣዎች ላይ ባረከ እንደ መጀመሪያውም ሕያው ሆኑ ወደ ዚያች ዐለትም ገቡ፡፡
ተዘጋጅ እንደ ቀድሞም ሆነች፡፡
☞ስም አጠራርህ መልካም የሆነ የእስራኤል ወገን ምሁር የስድሳ ነገስታት ወገን
ለልጆችህ ምግብ ከዓሣ ጋር ከደረቅ ዐለት ውሃን ያፈለቅህ ብጹአዊ አባት አባ
ሳሙኤል (ዘዋልድባ) ጸሎትህ ሀጥያታችንን በደላችንን የሚያስተሰርይልን
ይኹነን፡፡ ለዘላለሙ አሜን
☞(ገድለ አቡኑ ሳሙኤል ዘዋልድባ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc