𝗣𝗛𝗔𝗥𝗠𝗔 𝗜𝗡𝗙𝗢 𝗣𝗥𝗢


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Tibbiyot


Promote on PHARMA INFO!!!!! ምርትና አገልግሎትዎን ለማስተዋወቅ የሚከተሉትን መገናኛዎች ይጠቀሙ!!!
👉Telephone- +251911919998
👉Telegram- @Endalepharma
👉Email- endale47@hotmail.com
👉Telegram group: https://t.me/ETHIOPHARMAINFO
👉Telegram Channel: @PHARMA39INFO

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን dan repost
የመድኃኒት ደህንነትና ውጤታማነት ለማስጠበቅ በስራ ላይ ካሉ ስልቶች በተጨማሪ የመድኃኒት ምርት ስርጭት ክትትል ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ እንዲውል ባሉ ነባራው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሜዲካል ቫሊዩ ቼን (MVC) ከተሰኘ የባህሬ የመድኃኒት ስርጭት ክትትል ቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅት ጋር የቁጥጥር ስራውን ለመጀመር የድርጅቱ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በአደረጉት ውይይት እንደተናገሩት ይህ ፕሮጀክት መንግስት ከግሉ ሴክተር ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመው በባለስልጣኑ በኩል ምንም አይነት ወጪ እንደማይኖርና ወጪውም የቴክኖሎጂ አቅራቢው ከመድኃኒት አምራች ድርጅቶች ጋር በሚያደርገው ስምምነት የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በወቅቱም ከድርጅቱ ኃላፊ ጋር ሌሎች ዝርዝር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡
የሜዲካል ቫሊዩ ቼን ድርጅት ኃላፊ ሼካ ዲያ ቢንት ኢብራሂም አል ካሊፋ በበኩላቸው ድርጅታቸው የሚያቀርበው ቴክኖሎጂ ባህሬን ውስጥ ለውጥ ማምጣቱን ገልፀው የምንስራው ለአንድ ግብ ነው ይህም የታካሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ከደረጃ በታች የሆኑና ሀሰተኛ መድኃኒቶች መከላከል ዋነኛ ተግባራችን ነው ካሉ በኃላ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ድርጅታቸው አብሮ እንዲሰራ በመፍቀዱ አመስግነዋል፡፡
የቫሊዩ ቼን ልዑካን ቡድን አባላት በአገር ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ የአገር ውስጥ የመድኃኒት ፋብሪካዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ከድርጅቱ ጋር በጋራ ለመስራት ከወራቶች በፊት የመግባቢያ ስምምነት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ወኪሉ በኩል መፈራረሙ ይታወሳል፡፡


𝐏𝐇𝐀𝐑𝐌𝐀 𝐈𝐍𝐅𝐎™ የፋርማ መረጃ™ dan repost
🌹🌹🌹 VACANCY ANNOUNCEMENT 🌺🌺🌺
👉👉👉👉👉👉👉👉

🧿 FEMALE Senior Pharmacist with License

🧿 Partime Worker - Pharmacist

🧿 Dermatologist Doctor

Location: Kera

Anyone interested can call me ☎️☎️☎️ 0974409620


EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን dan repost
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀፅ 4/8  በተሰጠው ስልጣን መሠረት ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ ያዘጋጃል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ይከልሳል፡፡ በዚህም መሠረት የ3ኛዉ እትም ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከመንግስትና ከግል ዘርፍ የተወጣጡ የሕክምና የመድኃኒትን ባለሙያዎች የቴክኒካል የስራ ቡድን ተቋቁሞ ለአንድ ዓመት ያህል ሲሰራ የቆየ ሲሆን  በጤና እና ፋርማሲዩቲካል ሳይንስ አዳዲስ ለውጦችን መሰረት በማድረግ እንዲሻሻል በማደርግ ተዘጋጅቷል፡፡
የተከለሰው ፎርሙላሪ በቅርቡ ስራ ላይ የዋለውን 7ኛውን እትም ብሔራዊ መሠረታዊ የመድኃኒት መዘርዝርን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ፎርሙላሪው በተለያዩ ዙሮች ከተለያዩ ዩኒቨርስቲ እና ሆስፒታሎች በተወጣጡ የመስኩ ባለሙያዎች በምክክር እንዲዳብር ተደርጓል፡፡
ከህዳር 20-21/ 2017 ዓ.ም በአደማ  ከተማ በ3ኛው እትም ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ ዙርያ የክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት፣ የክልል ጤና ቢሮ የፋርማሲ አገልግሎት ባለሙያዎች እና ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተወጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የምክክር አውደ ጥናት ሲካሄድ የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የሕክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ኃላፊ አቶ ተሽታ ሹቴ እንደተናገሩት ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ በየአምስት ዓመቱ መዘጋጀት ያለበት ሲሆን በዚሁ መሠረት የመጀመሪያው እና የሁለተኛው በ2000 እና በ2006 ዓ.ም ተዘጋጅቷል፡፡ ይሁንና 3ኛውም ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ በ2011 ዓ.ም መዘጋጀት የነበረበት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን መቆየቱን አስታውቀው በተለያዩ ባለድርሻ አካላት የዳበረው 3ኛው ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪው በቅርቡ በባለስልጣኑ ማኔጅመንት ፅድቆ ታትሞ ስራ ላይ  እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡


Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት dan repost
በሀገራችን እየተከሰተ ስላለው ጉንፋን መሰል በሽታ የተሰጠ ማብራሪያ
---------------------------
የጉንፋን በሽታ በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጉሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ። በርካታ ቫይረሶች ለጉንፋን መከሰት ምክንያት ቢሆኑም በጣም የተለመዱት ግን ሪኖ ቫይረስ ፣ኮሮና ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ሲሆኑ ሪኖ ቫይረስ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል። ደረቅና ነፋሻማ የአየር ፀባይ (ወቅት) ቫይረሶች በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራጭ ስለሚያግዝ እና የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን (ሙከስ መምብሬን) ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍተኛ ድካም፣ ብርድ ብርድ ማለት፣የትንፋሽ ማጠር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸዉ።
ይህ የጉንፋን መሰል በሽታ ሁሉንም ሰው የሚያጠቃ እና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚያስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከሚወጡ ጠብታዎች (droplets) ጋር በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ፣ እንዲሁም ቫይረሱ ያረፈበትን ቁሳቁስ ወይም እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ሊተላለፍ ይችላል። ስለሆነም የእጅ ንጽህናን በመጠበቅ፣ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) በማድረግ፣ የምንጠቀምባቸውን ቁሳቁሶችን ንጽሕና በመጠበቅ፣ የቤት እና የብዙሃን መጓጓዣ ትራንስፖርት መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታውን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡ ህጻናት፣ አረጋውያን፣ ተጓዳኝ የጤና ዕክል (አስም፣ የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ የልብ ህመም፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ) በሽታዎች ያሉባቸው እና ነፍሰጡሮች ይበልጥ ተጠቂ ስለሚሆኑ በበሽታው ከተያዙ አስፈላጊው ክትትልና የህክምና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባል፡፡
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመተንፈሻ አካላት ቫይረስ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ክፍል በክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የጤና ተቋማት የቅኝት ስራውን በመደበኛነት ላለፉት 15 አመታት እየሰራ ይገኛል። ከአሁን በፊት በተሰራው የቅኝት መረጃ መሰረት ይህ ጉንፋን (ጉንፋን መሰል) በሽታ በሀገራችን አመቱን ሙሉ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ከመስከረም እስከ ታህሳስ ድረስ የስርጭት መጠኑ ከፍ ይላል፡፡በዚህም መሰረት ባለፉት ሁለት ወራት (መስከረምና ጥቅምት 2017ዓ/ም) ከሁሉም የቅኝት ጣቢያዎች የተሰበሰቡ ናሙናዎች መካከል 35% አር ኤስ ቪ፣ 6.2% ኢንፍሉዌንዛ፣ እንዲሁም 2% የኮረና ቫይረስ ተጠቂ መሆናቸው ተረጋግጧል። የአር ኤስ ቪ (RSV) ቫይረስ ተጠቂዎች ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ወቅት ከሚከሰተው መጠን ከፍ ያለ ሲሆን ቫይረሱ ከተገኘባቸው ህሙማን መካከል 88.5% የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡ ለሚቀጥሉት 2 ወራት የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡
በቂ እረፍት ማድረግ፣ ፈሳሽ መውሰድ፣ በልጆች የአፍንጫ መታፈን ከገጠመ ለብ ባለ ውሀ ላይ ትንሽ ጨው በመጨመር በአፍንጫ ጠብ ማድረግ፣ በእንፋሎት(ስቲም) መታጠን እንዲሁም ህመም ማስታገሻ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ህመሙ ከላይ በተዘረዘሩት በቤት ውስጥ በሚደረጉ ክትትሎች ለውጥ ከላሳየ እና የህመም ምልክቶቹ እየተባባሱ ከሄዱ (በተለይም በህጻናት ላይ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ማቃሰት፣ እና ሌሎችም ምልክቶች ከታዩ) ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማገኘት ያስፈልጋል፡፡




Hakim dan repost
የጀርባ (የወገብ) ህመም

የጀርባ ህመም ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ ከሚሹባቸው ወይም ከሥራ ከሚቀሩባቼው በጣም ከተለመዱ የህመም ምክንያቶች አንዱ ነው። የጀርባ ህመም በአለም አቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳት ዋነኛ መንስኤ ነው።

የታችኛው ጀርባ ህመም በራሱ በሽታ እይደለም። የበርካታ የተለያዩ የጤና ችግሮች ምልክት ወይም መገለጫ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የታችኛው ጀርባ ክፍሎች (መዋቅሮች ) ላይ በሚፈጠር ችግር ነው።

ለጀርባ ህመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎች :-

1. • ዕድሜ ( ዕድሜ መጨመር )
2. • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
3. • ከመጠን ያለፈ ክብደት ( ውፍረት )
4. • ስር የሰደዱ የጤና ችግሮች:- የካንሰር፣ አንጓ ብግነት፣ የኩላሊት ችግር )
5. • ከባድ ነገር ማንሳት
6. • የስነ-ልቦና ሁኔታዎች ( ውጥረት ፣ ጭንቀት )
7. • ሲጋራ ማጨስ

የጀርባ ህመም መንስኤዎች

• የጅማቶችና ጡንቻዎች ችግር
* የጡንቻ ወይም የጅማት ውጥረት፣ ቁስለት (መሸማቀቅ)
• የነርቮች ችግር
* ከአከርካሪ አጥንት ስር የሚወጡ ነርቮች ጉዳት
• የአከርካሪ አጥንት ጉዳት
* ሪሂማቶይድ አንጓ ብግነትና ሌሎችም የአከርካሪ አጥንት አንጓ ብግነት አይነቶች
* የአከርካሪ አጥንት መሳሳት፣ መሰበር፣ መጣመም
* የአከርካሪ አጥንት ኢንፌክሽን
• የድስክ ችግርሮች:-
* የድስክ መዘርጠጥ፣ መንሸራተት፣ መጨማደድና መሰበር
• በአቅራቢያው ባሉ የአካል ክፍሎች
* ኩላሊትና የሽንት ፊኛ ችግሮች (የኩላሊት ጠጠር፣ ኢንፌክሽን )
* የማሃፀን ጫፍ ካንሰር፣ የፕሮስቴት ካንሰር

ለጀርባ ህመም የሚያስፈልጉ ምርመራዎች:-

A, ኤክስሬይ ( X Ray ) :-
- የአከርካሬ አጥንት አንጓ ብግነት
- የአከርካሬ አጥንት ስብራት

B, ኤም አር አይ ( MRI ) ወይም ሲቲ ስካን ( CT-SCAN ):-
- የድስክ መዘርጠጥ፣ መንሸራተት ወይን ማፈንገጥ
- እንድሁም በተሻለ ደረጃ አጥንት፣ ጡንቻዎች፣ ነርቮች፣
- ጅማቶችና የደም ስሮች ጋር ያሉ ችግሮችን ያሳየናል።

C, የደም ምርመራዎች:-
- ኢንፌክሽኖች፣
- የአከርካሬ አጥንት አንጓ ብግነት ጠቋሚዎች
- ቫይታሚን ዲ ፣ ካልሺየም

D, ኤሌክትሮሚዮግራፊ (EMG)፣ የነርቭ አስተላላፊ ምርመራ (NCS ):-
- በተንሸራተቱ ወይም በተዘረጠጡ ዲስኮች ፣ የነርቭ መውጫ ቀዳዳ መጥበብና የተለያዩ የነርቭ ችግሮችንና በነርቮች ላይ ያለውን ጫና ለማረጋገጥ ይጠቅማል።

የጀርባ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው መቼ ነው!?

1. ከጥቂት ሳምንታት በላይ ከቆየብዎት፣
2. ከባድ ከሆነና በእረፍት እማይሻሻል ከሆነ፣
3. ህመሙ ወድ አንድ ወይም ሁለቱንም እግሮች ወደ ታች መሰማትና መሰራጫት ከጀመረ ፣
4. በአንዱ ወይም በሁለቱም እግሮች ላይ ድክመት፣ መደንዘዝና መወጠር ካስከተለ፣
5. የጀርባ ህመምዎ ክብደት መቀነስ ጋር ከመጣ ፣
6. ከጀርባ ህመሙ ጋር የአንጀት፣ የፊንጢጣና የሽንት ፊኛ ችግር ካጋጠምዎ፣
7. ከጀርባ ህመሙ ጋር ትኩሳት አብሮ ካለዎት፣
8. የመውደቅ አደጋ ካጋጠመዎት በሗላ የሚመጣ የጀርባ ህመም፣

የጀርባ ህመም መከላከልና ህክምና :-

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ:- ፈጣን እርምጃ፣ ሶምሶማ፣ ፕስክሌት ማሽከርከርና ዉሃ ዋና
• የጡንቻ ጥንካሬና ተጣጣፊነትን ( Flexibility) ማጎልበት
• ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ
• ማጨስን ያቁሙ

• የተስተካከለ አቋቋምና አቋም ይያዙ:- በሚቆሙ ሰዓት የተስተካከለ ዳሌ አቀማመጥን ይያዙ።

• ተስተካክለው ይቀመጡ:- በጥሩ ሁኔታ የታችኛውን ጀርባ የሚደግፍ እና የእጅ መደገፊያ ያለው መቀመጫ ይምረጡ።

1. እንዳማራጭ ትራስ ወይም የተጠቀለለ ፎጣ ከኋላዎት በማስቀመጥ መደበኛውን የወገብ ኩርባ/መለመጥ መደገፍና መጠበቅ ይቻላል።

2. ለረዥም ጌዜ አይቀመጡ፣ በየስዓቱ ከመቀመጫዎት ይንቀሳቀሱ አቀማመጥወን ያስተካክሉ።

• ከባድ ነገር አያንሱ:- ከባድ ነገር ማንሳት ካለብዎት እግሮችዎን ከፍተው ወገብወት ቀጥ እንዳለ ከጉልበት አጠፍና ዝቅ በማለት ያንሱ።

- ወይም ደግሞ ከጓዳኛ ጋር በጋራ በመተግጋገዝ ያንሱ።

# እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩ ጥንቃቄዎች በቋሚነት መተግበር የጀርባ ( የወገብ ) ህመም እንዳይከሰት ለመከላከል በጣም ተቃሚ ነው።

• የመኝታ ሁኔታን ያስተካክሉ :-
1. በጎንዎ መተኛት:- በጎንዎ ከተኙ እግሮችዎን ከጉልበት በትንሹ ወደ ደረት በማጠፍ ትራስ በእግሮችዎ መካከል ያድርጉ።

2. በጀርባዎ መተኛት:- በጀርባዎ ከተኙ ትራስ ከጉልበትዎ በታች በማስቀመጥ ታፋውዎ (ባትዎን) ትንሽ ከፍ ማድረግ።

• ከጀርባ ህመም ጋር በተቻለዎት መጠን የዕለት እንቅስቃሴዎትን ይቀጥሉ።
1. እንደ መራመድና የእግር ጉዞ ያሉ ቀላል እንቅስቃሴዎችን ይሞክሩ።

2. ህመሙን የሚጨምርና የሚያባብስ እንቅስቃሴን ያቁሙ። ነገር ግን ህመሙን በመፍራት እንቅስቃሴን ማቆም አይመከርም።

3. የትኛው የእንቅስቃሴ እይነት ለእርስዎ እንደሚመከር የፊዚዬቴራፒ (Physiotherapy) ባለሞያ ያማክሩ።

• የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች :- መድሃኒቶቹ እንደ የጀርባ ህመሙ ደረጃ አይነትና መንስኤ ይወሰናሉ።
1. የህመም ማስታገሻ ክኒኖች
2. የሚቀቡ ( መታሻ ) ህመም ማስታገሻዎች:- ክሬም፣ ቅባትና ፕላስተሮችን
3. የጀርባን ጡንቻ ዘና የሚያደርጉ መድሃኒቶች
4. ፀረ-ጭንቀት ማስታገሻዎች
5. በወገብ አከርካሬ አጥንት፣ በነርቭ ገመድ እና በነርቭ ስሮች ስር ዙሪያ የሚሰጡ መርፌዎች

• የቀዶ ጥገና ህክምና :-
- እንደ የጀርባ ህመሙ መንስኤና የህመሙ ደረጃ የቀዶ ጥገና ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል።

ዶ/ር ሙሃመድ የሱፍ : የውስጥ ዴዌ ስፔሻሊስት
ኢፍቱ ሆስፒታል፣ ድሬ ደዋ

Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

@HakimEthio


EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን dan repost
ዓለም አቀፍ የፀረ - ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ የግንዛቤ ማስጨበጫ የፓናል ውይይት ተካሄደ

ህዳር 12/2017 አዲስ አበባ፡ የጤና ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ያዘጋጁት የፓናል ውይይት ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደተናገሩት የፀረ - ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ዓለም አቀፋዊ ችግር መሆኑን በመግለፅ ለችግሩ ዓለም አቀፋዊ መፍትሄም ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ የችግሩ አንድ አካል እንደመሆኗ በርካታ ህዝብ ጉዳት ላይ ከመውደቁም በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና መፍጠሩን ገልፀው የሀገራችንን ህዝብ ግንዛቤ ለመጨመር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውቀዋል፡፡

የአፍሪካ ሲዲሲን ወክለው በፓናል ውይይቱ ላይ የተገኙት ዶከተር የዋንዴ አሊሚ በበኩላቸው የተባበሩት መንግስታት የፖለቲካል ዴክላሬሽንና የአፍሪካ ህብረትን አቋም ከፀረ - ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ አንፃር ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን እንደዶክተር የዋንዴ ገለፃ ከሆነ አፍሪካ የችግሩ ግንባር ቀደም ተጠቂ ብትሆንም ተገቢው ድጋፍ እየተደረገት አይደለም ብለዋል፡፡ በፓናል ውይይቱ ከአለም ጤና ድርጅት የተገኙ ፅሁፍ አቅራቢዎቸ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን ካቀረቡ በኋላ ሠፊ ውይይት ተደርጎ መድረኩ ተጠናቋል፡፡


















EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን dan repost
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በብሄራዊ የህክምና መሳሪያ ቪጂላንስ ማዕከሉ የህክምና መሳሪያዎች አሉታዊ ክስተቶችን ሪፖርት እንደሚቀበል ያውቃሉ?
የህክምና መሳሪያዎች አሉታዊ ክስተት ሪፖርት ምንድነው?

የህክምና መሳሪያ ጥራት እና ውጤታማነትን ለመከታተል፣ ሊከሰቱ የሚችሉ የህክምና መሳሪያዎችን ደህንነት ጉዳዮችን ለመለየት እና የህክምና መሳሪያዎች የጥቅም-አደጋ ግምገማን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከሚጠቀምባቸው የድህረ ገበያ ክትትል ስርዓት አንዱ ነው።
ምን አይነት የህክምና መሳሪያ አሉታዊ ክስተቶች ሪፖርት ይደረጋሉ?
ከህክምና መሳሪያዎች ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ሞት፣ አካላዊ ጉዳት፣ የጤና መታወክ፣ መሳሪያው የታለመለትን ዓላማ አለማከናወን፣ በማንኛውም የህክምና መሳሪያ ላይ ያለውን ማንኛውንም ጉድለት/ የተሳሳተ ምርመራ ዉጤት የሚያሳይ ወይም በአጠቃቀሙ የሚመጣ ማንኛውንም አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳስብ ማንኛውም ክስተት ናቸው።
ማሳሰቢያ፡ ይህ ሪፖርት መደረግ ያለበት የተሟላ ግብረ መልስ ዝርዝር አይደለም፣ ከህክምና መሳሪያ ጋር በተያያዘ ማንኛቸውም ችግሮች ካጋጠሙዎት እባኮዎ ሪፖርት ለማድረግ አያቅማሙ።
የህክምና መሳሪያዎች አሉታዊ ክስተቶች በማን ሪፖርት ይደረጋሉ?
• በአምራች ፤ አስምጭ፤አከፋፋይ
• የጤና ባለሙያ፤
• የህክምና መሳሪያ ተጠቃሚ ህብረተሰብ
ሪፖርት ማድረጊያ መንገዶች
• ከታች የተያይዘውን ፎርም በመሙላት።
www.efda.gov.et Services Medical Device Safety Filling the MDAER form Submit
• ይህንን QR ኮድ ስካን በማድረግ


Hakim dan repost
ማሳሰቢያ
_

በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛዎች የስኳር ህመምን ጨምሮ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ሃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተለቀቁ ይገኛሉ። ከሰሞኑም ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች ነዉ።

የህክምና ሞያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎት ህጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በማህበራዊ ሚዲያ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ተበራክተዋል። ይህ ተግባር ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ ፈውስ ፈላጊ ዜጎቻችን ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ ይገኛል።

ስለሆነም በዚህ መሰል ተግባር ላይ ተሰማርታችሁ የምትገኙ አካላት ይህ ተግባር በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን።

ማህበረሰቡም ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልእክቶችን እንዲመረምር፣ አገልግሎቶችንም ከመጠቀማችን በፊት ጥንቃቄ እንድናደርግ፣ አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ"Regulatory.moh@moh.gov.et" ላይ ጥቆማ እንድሰጠን እየጠየቅን ፤ ህዝባችን ሀሰተኛ የጤና መረጃ የሚለቁትን በማጋለጥ ፣የጤና ባለሙያ በማማከር ጤንነቱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

ጤና ሚኒስቴር

@HakimEthio



18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.