መሪ ስንፈልግ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በሃላፍነት የሰሩትን፤ ለዝማሬ ከሆነ ጥሩ ድምፅ ያላቸውን፤ ለተለያዬ አገልግሎቶች የንግግር ችሎታ፤ ቅልጥፍና፡ የመሳሰሉት ቀዳሚ መመዛኛዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ጠቃሚ ናቸው፡፡ ያሰፈልጋሉም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ካልጠራ በራሳቸው ለአገልግሎት ብቁ አያደርጉም፡፡ ታዲያ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ትልቁ ችግር ብቃታቸው ብቻ እየታየ ወደ አገልግሎት ስለተሰማሩ፤ ብዙዎችን የምናውቃቸውና ቦታ የምንሰጣቸው በጥሪያቸው፤ በራዕያቸውና በፍሬአቸው ሳይሆን በዕውቀታቸውና፤ በሥልጣናቸው፤ ነው፡፡
ስለዚህም #አንድ_የፋብርካ_ሥራ_እስኪያጅ መሪ ከሆነ ጉባዔ ሁሉ ወዝ አደር ይመስለዋል፡፡
#አንድ_ትምህርት_ቤት_ዲይረክተር መሪ ከሆነ አማኝ ሁሉ ቁጭ በሉ፤ ተነሱ የሚባሉ ተማሪዎች ይመስሉታል፡፡ #አንድ_የትራፊክ_ፖሊስ መሪ ከሆነ ሰው ሁሉ ፊሽካ እየነፋ የሚያስቆመው ሾፈር ይመስለዋል፡፡
ለዚህም ነው አንዳንድ መሪዎች መሰዋዕትነት እየከፈሉ የሚያገለግሉ አገልጋዮችን በሥራቸው ላይ ቆይተው አንድ ቀን ይመጡና አባርርሃለሁ ተባርረሃል እያሉ የሚያስፈራሩት፡፡
እግዚአብሔር ለመሪነት የጠራቸው፤ ሸክም ያላቸው ከሆኑ በተለያዩ ቦታዎች በኃላፍነት ቦታ የሚሰሩ ሰዎች ይጠቅማሉ፡፡ ነገር ግን የውጭ ብቃታቸው እግዚአብሔር ካልጠራቸውና ሸክም ከሌላቸው በራሱ የቱንም ያህል ታዋቂ ቢሆኑ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ብቁ አያደርጋቸውም፡፡
#ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቤት ሥራ የሚሰራ በውጫዊ ብቃት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስለሆነ..
ከዚህ የተነሳ የልፋታችን ያህል ፍሬያማ አልሆነንንም፡፡
እግዚአብሔር ብቁ ሰዎችን አይጠራቸውም ነገር ግን የተጠሩትን ሰዎች ብቁ ያደርጋቸዋል፡፡
በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ዘካርያስ 4፥6
@SOLA_TUBE