ብዙ ጊዜ እኖራለሁ የምትለውን ምኞትህን አሳጥር
➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿
የሞቱ ሰዎች በአጠቃለይ ከመሞታቸው በፊት መቼ እንደሚሞቱ አያውቁም ነበር።
የተለያዩ የወደፊት እቅዶች ነበሩዋቸው። ተውበት አድርጌ፣ትዳር ይዤ፣ ቤት ሰርቼ፣መኪና ገዝቼ፣ዝምድናን ቀጥዬ፣ያስቀየምኳቸውን እቅርታ ጠይቄ ወዘተ------- እያሉ ይህንን ሁላ እቅድ ይዘው አንዱንም ሳይፈፅሙት የተፃፈችዋ ቀን ደርሳ ሰይወዱ በግድ ወደ ዘላለማዊ ሀገር ሄደዋል። ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ አሁን ያለንባት ሰአት ለእኛ ትልቅ አጋጣሚ ናትና ንፁህ የሆነ ተውበት አድርገን ወደ አላህ እንመለስ።
🥀ሞት ማለት ሩቅ አይደለም። ተዘጋጁ
ልመጣ ነው ብሎም አይነግረንም።
አንድ ቀን👇
እሞታለሁ
ትሞታለህ
ትሞቺያለሽ
እንሞታለን።
🥀ስለዚህ ውዶቼ ከፈናችን ኪስ
የለውምና ለነገው ለጨለማው ቤታችን
ስንቅ እንያዝ።
🥀ይህን መልዕክት እኛ ጋር እንዳይቀር
ለተለያዩ ወዳጆቻችን በማስተላለፍ
የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።
🥀 የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ኢስላማዊ
እውቀቶችን ለማግኘት ከስር ያለውን
ሊንክ በመንካት ቻናሉን ጆይን ብለው
ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+ZZzCjxcbaso3YzM0