የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በአስደናቂ የማጠናቀቂያ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
ስታዲየሙ ባለፈው ሐምሌ ላይ ስንመጣ ከነበረው ገፅታ በእጅጉ ተለውጦ ምድረ ግቢው የተሻለ አምሮ የተመልካች ወንበሮች ገጠማ እየተፋጠነ፣ ሳሩ ተተክሎ እና ሌሎች የውስጥ ስራዎችን እየተሰሩ ተመልክተናል።
የስታዲየሙ ግንባታ በሁሉም መሠረተ ልማቶች የካፍ እና ፊፋን ዓለም አቀፍ ደረጃ ጠብቆ በመጨረሻው የግንባታ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
ግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየሙ ሀገራችን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንድታስተናግድ ዕድል የሚፈጥር ነው። በተጨማሪም ለባህር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት፣ የገቢ ምንጭና ለስፖርት ዘርፉ መነቃቃት የሚኖረው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው።
በዚህ ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር በጉብኝታችን አይተናል። [ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ]
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et