TIMRAN (ትምራን)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


Website: timran-et.org
FB: facebook.com/timranethiopia
Twitter: twitter.com/TIMRAN_et
Timran is dedicated to advancing women’s participation in politics and public decision-making in Ethiopia regardless of their political opinion or party affiliation.

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ትምራን በተለያዩ ውትወታ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ስታከብር የቆየችውን የአራተኛ ዓመት ክብረ በዓል አጠናቀቀች
ትምራን ሴቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲኾኑ እና በሀገሪቱ ውሳኔ ሰጭነት ውስጥ ተገቢ ውክልና እንዲኖራቸው የማስቻል ራእይ በመሰነቅ መጋቢት 2012 ዓ.ም ከኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት በማግኘት ሥራ ከጀመረች አራት ዓመታት ተቆጥረዋል።
መጋቢት ዓለም አቀፍ የሴቶች ወር እንደመኾኑ መጠን ትምራን የተለያዩ የውትወታ እና የአቅም ግንባታ ተግባራት በማከናወን አራተኛ ዓመት ክብረ በዓሏን ስታከብር ቆይታለች። የትምራን መሥራቾች፣ የቦርድ አባላት፣ ባለድርሻ አካላት፣ ተባባሪዎች እና ለጋሾች እንኳን ለትምራን አራተኛ ዓመት ምሥረታ አደረሳችኹ።
ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ትምራን ባስቀመጠቻቸው የውትወታ፣ ጥናት እና ምርምር፣ ጥበቃ እና ከለላ፣ አቅም ግንባታ እንዲኹም ትስስር እና አጋርነት በተሰኙ አምስት ምሰሶዎች መሠረት ከበርካታ ሀገር በቀል እና ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በርካታ ሥራዎችን አከናውናለች።
ትምራን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በምርጫ ጊዜ ለሴት ፖለቲከኞች የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ የውይይት መድረክ የማዘጋጀት፣ ለሴት ተመራጭ እጩዎች አቅም ግንባታ ሥልጠና የመስጠት እና በምርጫ ታዛቢነት የመሳተፍ፣ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሲቋቋም ለኮሚሽነርነት ሴት እጩዎችን የማቅረብ፣ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ተግዳሮቶች እና እድሎች ላይ ምክክር የማድረግ፣ ለሴት ሚዲያ ባለሞያዎች ለሥርዓተ ጾታ ትኩረት የሚስቡ ዘገባዎችን የማቅረብ እንዲኹም ለሐዋሳ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የአመራርነት ሥልጠና የመስጠት ሥራዎች ሠርታለች።
በስምንት ክልሎች የሴቶችን የሰላም ግንባታ ሚና ለማሳደግ ያለሙ መድረኮች እና የሰላም የእግር ጉዞዎች አዘጋጅታለች፤ በአገራዊ የሰላም ስትራቴጂ ላይ ከፌዴራል ሥራ አስፈጻሚ ሴት አመራሮች ጋር ምክክር አድርጋለች፤ ለሴት ፖለቲከኞች የአመራርነት፣ በፖለቲካ ውስጥ የተግባቦት ክሂሎት እና ምርጫ ቅስቀሳ ሥልጠና ሰጥታለች፤ በፖለቲካ ውስጥ በጾታ ላይ የተመሠረተ ጥቃት የተመለከተ ሥልጠና ለወንድ ፖለቲከኞች አዘጋጅታለች።
በሀገር በቀል የሰላም ግንባታ ሥርዓቶች ላይ የሴቶች ሚና፣ በፌዴራል እና በክልል የመንግሥት የሕግ አውጭ እና አስፈጻሚ አካላት ውስጥ የሴቶች ውክልና ኹኔታ፣ በኢትዮጵያ የዳኝነት ሥርዓት ውስጥ የሴት ዳኞች ውክልና፣ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ብሎም በሀገር በቀል የሰላም ግንባታ ዘዴዎች የሴቶች ሚና የሚሉ ጥናቶችን አዘጋጅታ ለኅትመት አብቅታለች።
ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች መብቶች እና አካታችነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና በመስጠት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የሲቪክ ማኅበራት ብሔራዊ የጥናት ጉባኤ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ፣ በትውልዶች መካከል ለሚደረግ የፖለቲካ ውይይት ምክረ ሐሳብ ማፍለቂያ መድረክ በማዘጋጀት፣ ሴቶች በሰላም አመራር ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳየት ያለመ ትምራን የተሰኘ የሥዕል ዐውደ ርእይ አዘጋጅቶ በማሳየት፣ በ4ኛው የአፍሪካውያን ሴት ከፍተኛ አመራሮች የሰላም እና ደኅንነት ሚና ውይይት ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ አድርጋለች።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የልምድ ልውውጥ በማካሄድ ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክከር መድረክ መሥራች አባል በመኾን ላለፉት ኹለት ዓመታት በጽ/ቤትነት በማገልገል ላይ ትገኛለች።
ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ኹለት ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በዘጠኝ ክልሎች የሴቶችን አጀንዳዎችን ለመለየት የሚያስችሉ 4000 በላይ ሴቶች የተሳተፉባቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መድረኮችን አዘጋጅታለች። ከየመድረኮቹ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን በማጠናቀር ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቅረብ ሂደት ላይ ትገኛለች።
እስካኹን የተከናወኑት ተግባራት ትምራን ሴቶች በሀገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ተገቢ ድርሻ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሰነቀችውን ራእይ እውን ለማድረግ አበረታች ናቸው።
በዚኹ አጋጣሚ ለትምራን ሥራዎች እገዛ በማድረግ አብረውን ሲሠሩ ለቆዩት የኖርዌይ ክርስቲያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ኦፕን ሶሳይቲ፣ ዩኤስኤይድ/ኤንዲአይ፣ ኦቲአይ፣ ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ እና አይአርአይ፣ የብሪታኒያ መንግሥት ሲቪል ሳፖርት ፕሮግራም 1 እና 2፣ ፕላን ኢንተርናሽናል፣ አይሪሽ ኤይድ፣ ፍሪደም ሐውስ፣ ዩኤን ዉመን፣ ፍሬደሪክ ኤበርት ስቲፍተንግ፣ የጀርመን ኤምባሲ፣ የጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር የሲቪል ፒስ ሰርቪስ፣ ሲሃ፣ ኢንክሉሲቭ ፒስ እና የካናዳ ኤምባሲ ምስጋና ታቀርባለች።




To further enhance the impact of affirmative action and quota system for women in politics, there is a need for continued advocacy, awareness campaigns, and capacity-building programs. Strengthening support networks for female politicians, implementing mentorship programs, and addressing structural barriers within political institutions are essential steps towards achieving greater gender parity.

Affirmative action and quota system for women in politics plays a vigorous role in promoting gender equality and empowering women to actively participate in decision-making processes. While progress has been made, ongoing efforts are necessary to address existing challenges and create a more inclusive political landscape that reflects the diversity of Ethiopian society.


በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት መኖር አስፈላጊነት

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት መኖር የሥርዓተ-ጾታ አድልኦን ለመቅረፍ እና ሴቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ጉልህ ተነሣሽነት ነው። ኮታዎች በሕግ አውጭ አካላት ውስጥ ለሴቶች የተከለሉ መቀመጫዎች ዝቅተኛ ገደብ ወይም መቶኛ እንዲኖር እድል ይሰጣሉ። እነዚህ ኮታዎች በፖለቲካ ተቋማት ውስጥ የወንዶች እና የሴቶችን ሚዛናዊ ውክልና ለማረጋገጥ በማሰብ በሕግ የተደነገጉ ወይም በፈቃደኝነት የተመሠረቱ ሊሆኑ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሴቶች በፖለቲካዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ አድርጓል። እነዚህ ጥረቶች ሴቶችን በማብቃት፣ ውክልናቸውን በማሳደግ እና የበለጠ አሳታፊ አስተዳደር እንዲኖር አስተዋጽኦ ለማድረግ ወሳኝ ናቸው።

አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት እርምጃዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በሴቶች ተሳትፎ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ አሳድረዋል። እነዚህ ውጥኖች በተለያዩ የመንግሥት እርከኖች ውስጥ የፖለቲካ ሥልጣን የሚይዙ ሴቶች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል። በፓርላማ እና በአካባቢ ምክር ቤቶች ለሴቶች የተያዙ መቀመጫዎችን በማዘጋጀት በፖለቲካ ውክልና ላይ ያለውን የሥርዓተ ጾታ አድልኦ ለማቃለል ረድቷል።

አዎንታዊ እርምጃ እና በኮታ ሥርዓት የተገኘው እድገት እንዳለ ሆኖ፣ አሁንም በፖለቲካ ውስጥ ሙሉ የጾታ እኩልነትን የሚያደናቅፉ ተግዳሮቶች አሉ። ሥር የሰደዱ ባሕላዊ ልማዶች፣ የሀብቶች አቅርቦት ውስንነት እና ኅብረተሰቡ ከሴቶች በኩል የላቀ አፈጻጸም ጥበቃ መኖሩ ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ ባላቸው ንቁ ተሳትፎ ላይ እንቅፋት መፍጠራቸውን ቀጥለዋል። በተጨማሪም በአመራርነት ሚና ውስጥ በሴቶች ላይ የሚሰነዘሩ አመለካከቶች እና አድሎአዊ ድርጊቶች አሁንም ቀጥለዋል፣ ይህም የፖለቲካ መብቶቻቸውን በተሟላ መልኩ ለመጠቀም ፈታኝ ያደርገዋል።

እ.አ.አ 2021 ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ሲቪክ ማኅበር እና በኢፌዴሪ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ትብብር የወጣ ጥናት በፖለቲካ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት ዝቅተኛ መኾኑን ያመላከተ ሲኾን፣ የሴቶችን የፖለቲካ እና የሕዝብ ተሳትፎ በየደረጃው ለማሳደግ አዳዲስ ኮታዎችንና ሌሎች አዎንታዊ እርምጃዎችን እንዲወሰድ ጠቁሟል።

በፖለቲካ ውስጥ የሴቶችን አዎንታዊ ተግባር እና የኮታ ሥርዓት የበለጠ ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ቅስቀሳ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች እና የአቅም ግንባታ መርሐ ግብሮች ያስፈልጋሉ። ለሴት ፖለቲከኞች የድጋፍ ትስስሮችን ማጠናከር፣ የማማከር መርሐ ግብሮችን መተግበር እና በፖለቲካ ተቋማት ውስጥ ያሉ መዋቅራዊ ማነቆዎችን መፍታት የላቀ የጾታ እኩልነትን ለማምጣት ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

በፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች የሚሰጥ አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት የጾታ እኩልነትን በማጎልበት እና ሴቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማብቃት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ትንሽ ለውጥ እየታየ ቢሆንም ያሉትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የኢትዮጵያን ኅብረተሰብ ብዝኀነት የሚያንፀባርቅ የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር ቀጣይነት ያለው ጥረት አስፈላጊ ነው።

The need of affirmative action and quota system for women in Ethiopian politics

Affirmative action and quota system in the Ethiopia political system for women has been a significant initiative aimed at addressing gender inequality and promoting women’s participation in decision-making processes. Quotas establish a minimum threshold or percentage of seats reserved for women in legislative bodies. These quotas can be either legislated or voluntary, aiming to ensure a more balanced representation of men and women in political institutions.

The government of Ethiopia has implemented various policies and strategies to ensure equal opportunities for women in political spheres. These efforts are crucial to empower women, enhance their representation, and ultimately contribute to more inclusive governance.

Affirmative action and quota system measures have had a notable impact on women’s participation in Ethiopian political system. These initiatives have led to an increase in the number of women holding political positions at different levels of government. By providing reserved seats for women in parliament and local councils, affirmative action and quota system has helped bridge the gender gap in political representation.

Despite the progress made through affirmative action and quota system, there are still challenges that hinder full gender equality in politics. Deep-rooted cultural norms, limited access to resources, and societal expectations continue to pose barriers to women’s active involvement in politics. Additionally, stereotypes and biases against women in leadership roles persist, making it challenging for them to fully exercise their political rights.

A 2021 report by Network of Ethiopian Women Association (NEWA) and Ministry of Women, Children and Youths (MoWCY) presents there is low political participation and decision making in Ethiopia. Thus, it highlights the need of inventing new quotas and affirmative actions to change the situation.










በፖለቲካ ተግባቦት እና የምርጫ ቅስቀሳ ክሂሎት ላይ ለትምራን ባለሞያዎች የተዘጋጀው የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ

የጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር የሲቪል ፒስ ሰርቪስ ከትምራን ጋር በመተባበር በፖለቲካ ተግባቦት እና የምርጫ ቅስቀሳ ክሂሎት ላይ ከመጋቢት 09-13 ቀን 2016 ዓ.ም ለትምራን ባለሞያዎች ያዘጋጀው የአሠልጣኞች ሥልጠና ተጠናቀቀ።

በሥልጠናው ላይ የፖለቲካ ተግባቦት ምንነት፣ ተዋናዮች እና መገለጫዎች፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አማካሪዎች እና ሚዲያ ሚና፣ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የማሳመን ጥበብ እና የፕሮፓጋንዳ ምንነት፣ መራጮች ዕጩዎችን ለመምረጥ አልያም ላለመምረጥ እንዲወስኑ የሚያደርጉ ምክንያቶች፣ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ዕውቀት ያላቸው መራጮች መገለጫዎች እና ድምፅ ማግኛ መንገዶች፣ የምርጫ ቅስቀሳ ስልቶች እንዲኹም የኢትዮጵያ ምርጫ ዘመቻ የሕግ ማእቀፎች የሚሉ ጭብጦች ከተዳሰሱት መካከል ናቸው።

ሥልጠናውን ለአምስት ቀናት የሰጡት ዳንኤል ወርቁ ከገለጻ በተጨማሪ፣ የግል እና የቡድን ተግባራት፣ ተሞክሮዎች፣ ጥናቶች፣ ማሳያዎች፣ ሰነዶች፣ ንግግሮች፣ ምስለ ተግባራት፣ ጨዋታዎችን በማካተት ሠልጣኞች በንቃት እንዲሳተፉ አድርገዋል።

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ለሠልጣኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት የሰጡት የትምራን መሥራች አባል ብሌን ዐሥራት፣ ትምራን ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ሥልጠና ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለተውጣጡ ሴት ፖለቲከኞች መስጠቷን አውስተው፣ ለባለሞያዎቿ መዘጋጀቱ በቀጣይ በውስጥ አቅም መሰል ሥልጠናዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ለመስጠት የሚያስችላት በመኾኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም የሀገራችን ፖለቲካ እጅግ ፈታኝ ቢኾን እንኳን፣ ሴት ፖለቲከኞች ተግዳሮቱን ፈርተው እንዳይርቁ ለማስቻል ትምራን ተከታታይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ማዘጋጀት እንደሚኖርባት አሳስበዋል።

በመጨረሻም ሠልጣኞች ከክብር እንግዳዋ ጋር የጋራ ፎቶ ተነሥተው መርሐ ግብሩ ተጠናቅቋል።






TIMRAN staff started a five-day ToT on Political Communication Skill
TIMRAN staff started a five-day ToT on Political Communication Skills on March 18, 2024, G.C.
The skill training aimed at preparing the staff to support women's meaningful political participation in the upcoming elections of the nation.
In her opening remark TIMRAN Executive Directress (ED), Eyerusalem Solomon, noted TIMRAN established and strives to address women's meaningful political participation and decision-making capability within the nation’s politics.
She added last year this training was piloted for women political members and leaders comprised from different political parties of the country by accessing them through their coalition.
In the upcoming time, the nation has elections, so as a civic organization working on women's political empowerment, the staff needs to get such skill training to commit their work professionally as trainers and facilitators of women in politics, electees, and electors, she underscored.
Lastly, she thanked the GIZ-Civil Peace Program for their generous financial support to conduct TIMRAN staff ToT on Political Communication skills.










ትምራን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን “ሴቶችን እናብቃ፣ እድገትን እናፋጥን” በሚል ጭብጥ በጽ/ቤቷ አከበረች

ትምራን #“ሴቶችን እናብቃ፣ እድገትን እናፋጥን” በሚል ጭብጥ በመከበር ላይ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ ቢሮ ፕሮግራም አስተባባሪ ከኾኑት ናታሊ ኩክ እና ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ደስታ ጥላሁን ጋር የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጽ/ቤቷ አከበረች።

በበዓሉ ላይ የትምራን ባልደረቦች በባሕላዊ አልባሳት ተውበው የቡና ማፍላት ሥነ ሥርዓት አከናውነዋል፤ የጋራ ባሕላዊ ማዕድ ተቋድሰዋል።

ዕለቱ ትምራን የተመሠረተችበት 4ኛ ዓመት መኾኑ በዓሉን ልዩ ያደረገው ክስተት ነበር።

ትምራን ሴቶች የትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ይያዙ ወይም ፓርቲ ውስጥ ይሳተፉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ውሳኔ ሰጭነት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የምትሠራ በ2012 ዓ.ም የተቋቋመች ከማንም የማትወግን ሀገር በቀል የሲቪክ ማኅበር ነች።

ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለማሳደግ የተቋቋመ ገለልተኛ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ ፋውንዴሽን ነው።

ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ትምራን እያከናወነችው የሚገኘውን ሴት አመራሮችን የማብቃት ፕሮጀክት በገንዘብ በመደገፍ ላይ ይገኛል።

TIMRAN celebrated International Women’s Day by a theme “Invest in Women: Accelerate Progress” at her office

TIMRAN celebrated this year International Women’s Day by a theme #“Invest in Women: Accelerate Progress” with the National Endowment for Democracy (NED) Ethiopian office Program Officer, Natalie Cooke and Ethiopian Political Parties Joint (EPPJ) Council Secretary Desta Tilahun on March 08, 2024, G.C at her office.

TIMRAN staff decorated with cultural clothing, delivered coffee ceremony and served a get together lunch.

The day was special in which TIMRAN celebrated its 4th year birthday.

TIMRAN is a local nonpartisan civil society organization dedicated to advance women’s participation in politics and public decision making in Ethiopia regardless of their political opinion or party affiliation established in March 2020.

NED is an independent, nonprofit foundation dedicated to the growth and strengthening of democratic institutions around the world.

NED funded TIMRAN Women Leadership Empowerment project.




#Invest in women: Accelerate progress-TIMRAN


#ሴቶችን ማብቃት፣ ለማፋጠን እድገት

ሴቶች እና ልጃገረዶችን ለማብቃት ሦስት ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል።

#በቀዳሚነት የሚያስፈልገው ሥራ ላይ መዋል የሚችል፣ ዘላቂነት ላለው ልማት መዋል የሚችል እና በብድር ጫና ውስጥ የሚገኙ በርካታ ታዳጊ ሀገራትን ችግር መቅረፍ የሚችል መዋዕለ ንዋይ መኖር ነው። ይኽ ኹኔታ ካልተሟላ ሀገራት በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ሊሠሩ አይችሉም።

#ሁለተኛው ሀገራት እኩልነት የመብት ጉዳይ ብቻ ሳይኾን ሰላማዊ እና የበለጸገ ማኅበረሰብ ለመገንባት መሠረት መኾኑን በማመን ለሴቶች እና ልጃገረዶች እኩልነት ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል። ይኽም ማላት መንግሥታት አድሏዊ አሠራርን መግታት፣ ሴቶች እና ልጃገረዶችን ማብቃት የሚያስችሉ መርሐ ግብሮችን መደጎም ብሎም ፖሊሲዎች፣ በጀቶች እና ኢንቨስትመንቶች ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

#በሦስተኛነት ወደ አመራርነት የሚመጡ ሴቶችን ቁጥር መጨመር ያስፈልጋል። ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት የሴቶችንና ልጃገረዶችን ፍላጎቶችን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ፖሊሲዎች እና መርሐ ግብሮች እንዲቀላጠፉ ያደርጋል።

#Invest in women accelerate progress

Securing the investment we need in women and girls requires three things.

#First, increasing the availability of affordable, long-term finance for sustainable development and tackling the debt crisis strangling many developing economies. Otherwise, countries simply won't have the funds to invest in women and girls.

#Second, countries must prioritize equality for women and girls - recognizing that equality is not only a matter of rights but the bedrock of peaceful, prosperous societies. That means governments actively addressing discrimination, spending on programs to support women and girls and ensuring that policies, budgets and investments respond to their needs.

#Third, we need to increase the number of women in leadership positions. Having women in positions of power can help to drive investment in policies and programs that respond to women's and girls' realities.

Adapted from Express Tribune

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.