ምዝገባው ዛሬ ያበቃል!የ2024 የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ምደባ (Matching) በቅርቡ ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ በአመልካቾች ያልተመረጡ በተለያዩ ፕሮግራሞች እና ትምህርት ቤቶች
373 ክፍት ቦታዎች መኖራቸውን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል (ከላይ ተያይዟል።)
በመሆኑም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ለክፍት ቦታዎቹ ማመልከትና መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
በምታመለክቱበት ወቅት ሙሉ ስም፣ የመታወቂያ ቁጥር፣ የአንድ ፕሮግራም ምርጫ እንዲሁም የሁለት ትምህርት ቤቶች ምርጫችሁን በደረጃ በመግለፅ በኢሜይል አድራሻ
ermpvacantspots@gmail.com መላክ ይኖርባችኋል፡፡
@tikvahuniversity