Ministry Of Education


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


📚ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው
🔵ከ1-12 መፅሃፍት ለማግኘት: @STBookbot
🔴ለFreshman : @Freshman_Robot
«Buy Ads» @MoeAds_bot or https://telega.io/c/Tmhrt_minister

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


#Ad

2 ነፃ ፈተናዎች እንዲሁም 80% ቅናሽ እድለኛ ይሁኑ!

አስደሳች ዜና ለተማሪዎች ይዘንላቹ መተናል!

Lightup ከሚያዘጋጃቸው ፈተናዎች 2ቱን በነፃ ሊሰጣቹ ነው። ኮፖን ኮድ 767KEQSC በመጠቀም ብቻ ነፃ ፈተናዎችን ይውሰዱ!
ይሄን እድል ለማግኙት ማድረግ ያለባቹ ነገር ቀላል ነው
1, ይመዝገቡ እና አካውንትዎን አክቲቬት ይድርጉ
2, በመለያዎ ገብተው ኮርሶችን እና ፈተናዎችን ይመልከቱ
3, የፈለጉትን ፈተና በመምረጥ ወደ ክፍያ ገጽ ላይ ሲገቡ ኮዱን ያስገቡት(767KEQSC)
4, ነፃ ፈተናዎችን ይውሰዱ! ለእያንዳንዱ ተማሪ ኮዱን 2 ጊዜ መጠቀም ይችላል!

ይህ ብቻ አይደለም...
🔥 ሁሉም ፈተናዎች ላይ 80% ቅናሽ አድርገናል እስከ ሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ድረስ ያገኛሉ!
📚 ሙሉውን ፈተናዎች ለማግኝት 👉 https://lightup.et/courses

ከ Lightup Digital Solution ጋር ይቀላቀሉ እና ወደ ስኬት መንገድዎ ይጀምሩ! ለጓደኞችዎ እንዲሁም ለቤተሰባ ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

#LightupDigitalSolution #Givingaway #FreeExams #Education #CouponCampaign #Learning #Students #Opportunity #Ethiopia


ቀለሜ dan repost
🤖 Qeleme Exams Mobile Application

ለ Freshman ተማሪዎች ድንቅ የ ጥያቄ መስሪያ አፕልኬሽን!

በ ጥያቄ የሚማሩበት
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተደጋጋሚ ቅርጻቸውን እየቀየሩ የሚመጡ የተመረጡ ጥያቄዎችን ከ ሙሉ ማብራሪያቸው 'ና አጫጭር ትምህርቶች ጋር ያቀፈ።

እራስዎን የሚፈትሹበት
የፈለጉትን ምዕራፍ እና የጥያቄ ብዛት መርጠው ስሀት በመመደብ ፈተና እየወሰዱ እራስዎን የሚፈትሹበት።

Offline ሁነው የሚጠቀሙት     
አንድ ጊዜ ጥያቄዎችን በማውረድ ያለምን Internet ግንኙነት በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ የሚያገኙት።

ለ አጠቃቀም ምቹ 
እጅግ ዘመናዊ፣ ውብ እና ማራኪ በሆነ አቀራረብ ጥያቄዎችን የሚሰሩበት።


📱 አፕልኬሽኑን አሁኑኑ ከ Play Store በማውረድ የ Freshman ፈተናዎትን ያሸንፉ!

🖥Play Store Link: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.qeleme.exams

💬 Telegram Channel: https://t.me/keleme_2013

👨🏾‍💻 Need help?: https://t.me/QelemeExamsAdmin


#MoE

" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።

" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዞ መግባት ሊከለከል ነው‼️
“ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል “ - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል።

“ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል “ ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ድግሪ እና በላይ ለተመረቃችሁ ምሩቃን በሙሉ:-

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መምህራንን አቅርቦት ለማሳደግ የተለያዩ የስልጠና ሰርዓቶችን ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት አጠናቋል፡፡

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያ ድግሪና በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላችሁ ምሩቃን ከታች የተያያዘውን link በመጠቀም የፅሁፍ መጠይቁን እንድትሞሉ

https://forms.gle/N8uPaW7uXYTEZWQC8

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


Grade 12 Maths units 1-4 worksheet.pdf
1.1Mb
📚Grade 12 Maths units 1-4 worksheet

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#Digital_ID

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች እና ሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ እንዲይዙ እና የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ኮራ ጡሹኔ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ በዚህ ዓመት ሰኔ 2017 ዓ.ም ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ሁሉም የግል እና የመንግሥት ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ መሆኑን አስታውሰዋል።

በመሆኑም ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎቻቸው የፋይዳ መታወቂያ እንዲያወጡ እንዲያደርጉ እና የተማሪዎቹን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ቁጥር በኤሜል አድራሻ eyobie2002@yahoo.com በኩል እንዲልኩ አሳስበዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ማድረግ መጀመራቸው ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

ፈተናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት እስከ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትናንት ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የምዘና ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በተወሰኑ ተቋማት መቋረጡን ሰምተናል።

በዚህም ትናንት የተሰጠውን ፈተና ያልወሰዱ ተመዛኞች ቅዳሜ ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ቀጥሎ በዛሬው ዕለት የፋርማሲ፣ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ እና ሚድዋይፈሪ ተመዛኞች ፈተናውን እየወሰዱ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ተማሪዎች ሁሉ የግድ ሊኖራቸዉ የሚገቡ ምርጥ ቻናሎች እነሆ 😊 ፦

1. Ministry Of Education 📚

2. MOE Library 📚

3. Matric Fetena 📚

4. Freshman Journey 📚

Bonus +

5. 𝚙𝚒𝚗𝚝𝚎𝚛𝚎𝚜𝚝 ᴇᴛ 🌁


#AksumUniversity

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የስፔሻሊቲ ሬዚደንሲ ተማሪዎች ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመግቢያ ቀናት ከሚያዝያ 5-8/2017 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት አክሱም ከተማ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ግቢ በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➫ ማንነታችሁ የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ፣
➫ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ወደ ዩኒቨርሲቲው ዋናው ሬጅስትራር ማስላክ።
ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


English2016 - [with answer & explanation] ( (2).pdf
2.3Mb
📚English2016 - with answer & explanation

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት "በኢትዮጵያ መልቀቂያ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የቅርብ ጊዜ ተለዋዋጭነት ግምገማ" በሚል ርዕስ ለአንድ ዓመት የቆየ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።

ኢንስቲትዩቱ ካቀረባቸው የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች መካከል፣ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የማኅበራዊ ልማትና አካታችነት ማዕከል ኃላፊና ከፍተኛ ተመራማሪ ደሳለኝ አንጭሶ (ዶ/ር)፥ የተማሪዎች ውጤት እንዲቀንስ ካደረጉ ቁልፍ ምክንያቶች መካከል የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱ መቀየር በተለይ ከከተሞች ራቅ ካሉ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተማሪዎች ላይ የፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ምክንያት ጥሩ ውጤት ማምጣት የነበረባቸው ተማሪዎች ውጤት ሳያመጡ መቅረታቸው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

"ተማሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎች እንዲሞሉ በማድረግ እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የደኅንነት ካሜራዎችን በመግጠም የቁጥጥር ስራ በመስራት፣ ተማሪዎች ከሚኖሩበት አካባቢ ሳይርቁ ፈተናውን እንዲፈተኑ ትምህርት ሚኒስቴር የረዥም ጊዜ ዕቅድ ይዞ እንዲሠራ" ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ገልፀዋል።

የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል እና ከታች ጀምሮ ጥራት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው፤ የትምህርት ቤት አመራሮች ዕውቀትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሊመደቡ እንደሚገባም ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ተናግረዋል።

ጥናቱ በፀጥታ ችግር ምክንያት የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን እንዳላካተተ ተገልጿል። #Reporter

ትምህርት ሚኒስቴር


የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#Residency_GAT_Registration

በ2017 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችሁ የሕክምና ስፔሻሊቲ ሬዚደንሲ አመልካቾች የትምህርት ማስጀመሪያ የገለጻ ፕሮግራም ረቡዕ ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ገለጻው በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዳራሽ አስተዳደር ሕንጻ አንደኛ ፎቅ፣ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ይሰጣል።

አመልካቾች ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፈተና (GAT) ለመውሰድ መመዘገብ ይኖርባችኋል።

ለ'GAT' ይመዝገቡ፦

https://Portal.aau.edu.et ይግቡ።

➫ Exam Application የሚለውን ይጫኑ።

➫ Test Taker Registration የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።

➫ የፓስፖርት መጠን ፎቶ ያለው ፎቶ ያስገቡ።

➫ Submit የሚለውን ይጫኑ።

➫ ሲስተሙ የሚሰጠዎን መለያ ቁጥር ይያዙ።

➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ 750 ብር ይክፈሉ።

➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው ይያዙ።

የ'GAT' ፈተና ከሚያዝያ 6-10/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#ExitExam

👉የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች መረጃ አሰጣጥ


፨ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

ጉዳዩ- የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ አሰጣጥን ይመለከታል!


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገራዊ የቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኖ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 919/2014 ወጥቶ ተግባር ላይ ውሏል፡፡ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 12 (12.3) ላይ የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ እና ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ በተደረገው ሰርተፍኬት ፎርማት መሠረት እንዲፈጸም እናሳውቃለን፡፡ (ትምህርት ሚኒስቴር)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


@Tmhrt_Minister G-12 BIOLOGY THE NERVOUS SYSTEM.pdf
1.5Mb
@Tmhrt_Minister G-12 BIOLOGY, UNIT 6 CLIMATE CHANGE.pdf
1.1Mb
📚Biology Grade 12 😊 ምርጥ PPT ( Shorte Note ) ለፈተና ዝግጅት

📁Unit 5 Nervous System
📁Unit 6 Climate Change

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


" 10ኛ ክፍል ላይ ሀገር አቀፍ ፈተና ሳይወስዱ ወደ 11 የተዘዋወሩ ተማሪዎች ልዩ የማካካሻ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፣ ካልሆነ ግን መውደቅ ይቀጥላል  " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር በየጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ተከትሎ አካሄድኩት ባለው እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ጥናት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መገኘታቸውን ገልጿል።

የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ከተካሄደ በኋላ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ከሚችሉት በላይ ተማሪዎችን ያስተምራሉ ያለ ሲሆን ከዚህ በፊት 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረውን ፈተና በመቅረቱ ሳይፈተኑ 11ኛ ክፍል መግባታቸው ለችግሩ ዋና ተጠቃሽ ምክንያት መሆኑን አመላክቷል።

በትምህርት ቤቶች በሚሰጠው የሞዴል ፈተና እና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው የሀገር አቀፍ ፈተና ሰፊ ልዩነት እንዳለውም ገልጿል።

" በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መካከል የማለፍ ንፅፅር ሲታይ ልዩነት አለ " ያለው ሚኒስቴሩ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወደ ከፍተኛ ተቋም ይገባሉ፣ ይሁን እንጂ በቂ አይደለም፣ ብዙ ነገሮች መሻሻል እንዳለባቸው ጥናቱ አሳይቶናል " ብሏል።

ጥናቱ ምን አይነት የትምህርት ዘርፍ ችግር ነው ይሄን ያክል ውድቀት ያመጣብን ፣ ከተማሪዎች መውደቅ እና ማለፍ ጋር ተያይዞ የትምህርቱ ባህሪ ምንድን ነው የሚለውን እና በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የያዘ ነው።

በሁሉም የትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ ችግሮችን ያሳየው ይሄ ጥናት በመጨረሻም የመፍትሄ ሃሳቦችንም አቅርቧል።


ትምህርት ሚኒስቴር ምን የመፍትሄ ሃሳብ አቀረበ ?

" ከዚህ በፊት 10ኛ ክፍል ላይ ይሰጥ የነበረውን ሀገራዊ ፈተና ሳይወስዱ 11ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ልዩ የማካካሻ ፕሮግራም ያስፈልጋቸዋል። ይሄ ካልሆነ ግን መውደቅ ይቀጥላል ፣ ምክንያቱ የሚፈለገውን ያህል እውቀት እና ክህሎት ይዘው አይወጡም።

በገጠር በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢዎች ላይ ያለው የትምህርት ዘርፍ ልማት አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እጅግ ወደ ኋላ እየቀረ ስለሆነ ማካካሻ መሰራት አለበት።

ሌላው ደግሞ ከትምህርት አመራር፣ መምህራን እና ከአቅም ግንባታ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች ውጤት በሚያመጡ ጉዳዮች  ላይ ብቻ ትኩረት ተደረጎ የትምህርት አመራሩ አቅም እስካልሰጠ ችግሮቹ ይቀጥላሉ።

ለመምህራን የደመወዝ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን መምህሮችን የሚያቅፍ የ insensitive package እስካልመጣ ድረስ ችግሮቹ ይባባሳሉ።

በተጨማሪም በሀብት ክፍፍል ላይ ክፍተት በመኖሩ በትምህርት ዘርፉ ልማት ላይ ተግዳሮት መኖሩን ያሳያል፣ ይሄም መፈታት አለበት
" ሲል መፍትሄ ያለውን ሃሳብ አቅርቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር ጥናቱን ባቀረበበት ወቅት የህዝብ ተወካዮች የተለያዩ አስተያየቶች፣ ጥያቄዎች እና ሃሳቦችን አቅርበዋል።

በጥናቱ ላይ የመፍትሄ ሃሳቦች መቅረባቸው ጥሩ ሁነው ሳለ እንደዚሁ ተወርተው መሬት ላይ ሳይወርዱ ከቀሩ ትርጉም አልባ ናቸው፣ በመሆኑም ሁሉም በአፅንኦት ሊመለከተው እንደሚገባ በተወካዮች ተጠቁሟል።

ከ1 እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አነስተኛ ነው፣ ይሄም አሁን ላለንበት ውጤት ማጣት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ፤ በጥናቱስ ላይ ለምን ይሄ ሳይካተት ቀረ፣ ምክንያቱም የትምህርት መሰረቱ ከታች ጀምሮ ስለሆነ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስቷል።

የተለያዩ ተማሪዎች በህገወጥ መንገድ ወደተለያዩ ሀገሮች እየተሰደዱ ነው፣ ተማሪዎች ይሄ ሲፈጠር ተረጋግተው መማር እየቻሉ አይደለም፣ ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister




#MoE

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት  እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።

ውይይት ሲደረግ ነበር።

በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት (እሳቸው  በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🎙የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ንግግር

ከተቻለ በሚቀጥለው ዓመት ካልሆነም በ2019 ዓ.ም. የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት የተማሩበትን ማህበረሰብ እንዲያስተምሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

፨ይህ አዲስ አሰራር ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር ለምሳሌ አምስት ዓመት የሚማር የምህንድስና ተማሪ የአራተኛ ዓመት ትምህርቱን ሲጨርስ ለአንድ ዓመት የተማረበትን ማህበረሰብ እንዲያስተምሩ ይደረግና በቀጣዩ ዓመት አምስተኛ ዓመት ትምህርቱን ይቀጥላል። ከዚያም ይመረቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.