ሕይወትን ሰጠው
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا
"ሄዩቶ" ἑαυτῷ ማለት "ራስ"own self" ማለት ሲሆን አንድ ምንነት የራሱ ማንነት እንዳለው ለማመላከት የሚል ድርብ ተውላጠ ስም"Reflexive pronoun" ነው፦
ዮሐንስ 11፥51 ይህንም የተናገረ "ከራሱ" አይደለም። τοῦτο δὲ ἀφ’ ἑαυτοῦ οὐκ εἶπεν,
እዚህ አንቀጽ ላይ "ራሱ"himself" ለሚለው የገባው ቃል "ሄዩቱ" ἑαυτοῦ ሲሆን ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ የራሱ "እኔነት" እንዳለ አመላካች ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "አብ በራሱ" ሲባል አብ የራሱ እኔነት እንዳለው ሁሉ ወልድም የራሱ እኔነት እንዲኖረው አብ ለወልድ ሕይወትን ሰጠው፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ እንዲኖረው ሕይወት ሰጥቶታልና። ὥσπερ γὰρ ὁ Πατὴρ ἔχει ζωὴν ἐν ἑαυτῷ, οὕτως καὶ τῷ Υἱῷ ἔδωκεν ζωὴν ἔχειν ἐν ἑαυτῷ.
"ሕይወትን ሰጥቶታልና" የሚለው ይሰመርበት! "ኤዶኬን ዞኤን" ἔδωκεν ζωὴν ማለት "ሕይወት ሰጠው" ማለት ነው። ወልድ በራሱ የራሱ ማንነት እንዲኖረው አብ ለወልድ የሰጠው ሕይወት ነው፥ "አብ ሕይወት አለው" ማለት "አብ ህልውና አለው" ማለት ከሆነ "ወልድ ሕይወት እንዲኖረው" ማለት "ወልድ ህልውና እንዲኖረው" ማለት ነው። እዚህ ዐውድ ላይ "ሕይወት" የተባለው የራስ ሃልዎት"self existence" ነው፥ እያንዳንዱ ማንኛውም ማንነት የራሱ ሃልዎት አለው። አንዱ አምላክ አብ ለእያንዳንዱ ሰው በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሕይወትን ይሰጣል፦
የሐዋያት ሥራ 17፥25 እርሱም ሕይወትን እና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና። αὐτὸς διδοὺς πᾶσι ζωὴν καὶ πνοὴν καὶ τὰ πάντα·
አብ የሕይወት ምንጭ ስለሆነ አብ የወልድ ሕይወት ምንጭ እና ሥር መሆኑን አንብሮስ ዘሚለን"Ambrose of Milan" ተናግሯል፦
"አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"
Exposition of the Christian Faith (Ambrose)> Book IV(4) Chapter 10 Number 133
አውግስጢኖስ ዘሂፓ"Augustine of Hippo" አብ ለወልድ ሕይወትን እንደሰጠው አስረግጦ እና ረግጦ ተናግሯል፦
"ያ በመወለድ አብ ለወልድ የሰጠው ሕይወት ከሰጠው ከአብ ሕይወት ጋር አብሮ-ዘላለማዊ ነው"።
On the Trinity(Augustine) Book XV(15) Chapter 26 Number 47
"እንዲህ አለ፦ "በራሱ እንዲኖረው ለወልድ ሕይወት ሰጥቶታልን" በአጭሩም እላለሁኝ፦ "እርሱ(አብ) ወልድን ወልዶታል"።
Tractates on the Gospel of John (Augustine) > Tractate 19 Number 13
ኢየሱስ ሕያው ሆኖ በሕይወት የሚኖረው ሕያው አብ ሕያው ስላረገው ነው፥ ኢየሱስ በሕይወት የሚኖረው በአምላክ ኃይል ነው፦
ዮሐንስ 6፥57 ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔ ከአብ የተነሳ የምኖር ነኝ። καθὼς ἀπέστειλέν με ὁ ζῶν Πατὴρ κἀγὼ ζῶ διὰ τὸν Πατέρα,
2 ቆሮንቶስ 13፥4 ነገር ግን በአምላክ ኃይል በሕይወት ይኖራል። ἀλλὰ ζῇ ἐκ δυνάμεως Θεοῦ.
ኢየሱስ አብ ሕይወት ከሰጠው በኃላ ይሞት እና ድጋሚ ሕይወት እንደሚቀበል እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 10፥17 ሕይወቴን "ዳግም" እወስድ ዘንድ አኖራታለውና ስለዚህ አብ ይወደኛል። διὰ τοῦτό με ὁ Πατὴρ ἀγαπᾷ ὅτι ἐγὼ τίθημι τὴν ψυχήν μου, ἵνα πάλιν λάβω αὐτήν.
"ፓሊን" πάλιν ማለት "ድጋሚ" "ሁለተኛ" "ዳግም"again" ማለት ነው፥ ድጋሚ ሕይወቱን እንደሚቀበል መናገሩ በራሱ መጀመሪያ ሕይወት እንደተሰጠው አመላካች ነው። "አኖራታለውና" ማለቱ ወልድ ሕይወቱን በጽድቅ ለሚፈርደው ለአብ እንደሚሰጥ ነው፥ ነፍሱን ከሰጠ በኃላ ይሞታል። ከሞተ በኃላ "ድጋሚ" ሕይወትን ከአብ ይቀበላል፦
ዮሐንስ 10፥18 እኔ በራሴ አኖራለው እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ "ዳግምም" ልቀበላት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ። οὐδεὶς ἦρεν αὐτὴν ἀπ’ ἐμοῦ, ἀλλ’ ἐγὼ τίθημι αὐτὴν ἀπ’ ἐμαυτοῦ. ἐξουσίαν ἔχω θεῖναι αὐτήν, καὶ ἐξουσίαν ἔχω πάλιν λαβεῖν αὐτήν· ταύτην τὴν ἐντολὴν ἔλαβον παρὰ τοῦ Πατρός μου.
ሕይወት ዳግም እንደሚቀበል መናገሩ ቅድሚያ ሕይወት እንደተሰጠው አመላካች ነው። እንደ ባይብሉ ፈጣሪ ለፍጡሩ ሕይወትን የሚሰጠው በአፉ እስትንፋስ ነው፦
ኢዮብ 33፥4 የያህዌህ መንፈስ ፈጠረችኝ፥ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠችኝ። רֽוּחַ־אֵ֥ל עָשָׂ֑תְנִי וְנִשְׁמַ֖ת שַׁדַּ֣י תְּחַיֵּֽנִי׃
በአንስታይ የሴት አንቀጽ የተቀመጡት የግሥ መደብ "ዓሳቴኒይ" עָשָׂתְנִי ማለት "ፈጠረችኝ" ሲሆን "ታሐዪኒይ" תְּחַיֵּֽנִי ማለት ደግሞ "ሕይወትን ሰጠችኝ" ነው፥ ከአፉ የሚወጣው እስትንፋስ ማርያም ማኅፀን ውስጥ ፅንስ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፦
ማቴዎስ 1፥20 ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና። τὸ γὰρ ἐν αὐτῇ γεννηθὲν ἐκ Πνεύματός ἐστιν Ἁγίου·