የህዝብን የህይወት ለውጥ ከነፍስ ወከፍ ገቢ ባሻገር ማሰብ ያስፈልጋል! (የIMF: World Happiness Report, 2023፡ Looking beyond GDP)……
ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) በአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ያሉ በአንድ ዓመት ውስጥ ለፍጆታ የወጣ ወጪ (Consumption) ለኢንቨስመንት የወጣ ወጪ (Investment) የመንግስት ጠቅላላ ወጪ (Government Expenditure) እንዲሁም ከውጪ ምርት ለማስገባት የሚወጣን ወጪ (Import) ለውጪ ምርት በማቅረብ ከሚገኝ ገቢ (Export) በማቀናነስ ያሰላል፡፡
የዛሬ 50 ዓመት በወቅቱ የአሜሪካ ሴናተር የነበሩት ሮበረት በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ላይ ጠንከር ያለ ትችት አቀረቡ እሱም “ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ህይወትን ጠቃሚ ከሚያደርጉት ምክንያቶች በስተቀር ሁሉንም ነገር ይለካል“(GDP measures everything...except that which makes life worthwhile) የዚህ አይነቱ ትችት ጠቅላላ ሀገራዊ ምርትን በተለየ ሁኔታ ማሰብ ያስፈልጋል የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
ፖሊሲ አውጪዎች የአንድ ሀገርን ነዋሪዎችን የህይወት ለውጥ ሁኔታን በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ከማየት ይልቅ ዜጎች በህይወታቸው ደስተኛ ስለመሆናቸው መለካት መጀመር አለባቸው ከሚለው አመክንዮ በመነሳት በየዓመቱ ከተለያዩ መለኪያዎች በመነሳት የዓለም የገንዘብ ድርጅት የዓለም ህዝቦች የደስተኝነት ደረጃ (World Happiness Report) ያወጣል፡፡
የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን ለጠቅላላ ህዝቦች ሲካፈል የነፍስ ወከፍ ገቢ ስሌትን ይሰጣል (GDP per capita) ይህ ቁጥር እየጨመረ በመጣ ቁጥር በኢኮኖሚ የተሻለ ሀገር ወይም የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ ዜጎች ያላት ሀገር በሚል ሲሰላ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የነፍስ ወከፍ ገቢ (Per Capita Income) ወይም ዜጎች በዓመት የሚያገኙት ገቢ መጠንን ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ብቻ ለመውሰድ ከሞመከር ዜጎች ያላቸው ማህበራዊ ድጋፍ፤ የጤና ሽፋን፤ በህይወት የመኖራቸው እድሜ ጣሪያ፤ የመኖር እና የመናገር ነጻነታቸው፤ ደግነታቸው/ልግስናቸው፤ አነስተኛ ሙስና መኖር፤ ወዘተ የዜጎች የኑሮ ደስተኝነት መለኪያ አድርጎ መጠቀም ያስፈልጋል በሚል ወደተግባር ሀገራት ገብተዋል፡፡
የዓለም የገንዘብ ድርጅት የዚህ ዓመት የዓለም ሀገራት ዜጎች ያላቸውን የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን እና የደስተኝነት ደረጃ ምን እንደሚመስል ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ባለፈ ማሰብ ያስፈልጋል በሚል ርዕስ (Looking Beyond GDP) ሪፖርት አውጥቷል (World Happiness Report, 2023) ፡፡ ዜጎቿን ደስተኛ በማድረግ ቀዳሚዋ ሀገር ፊንላንድ ስትሆን የመጨረሻዋ ሀገር ደግሞ አፍጋኒስታን ሆናለች፡፡
በዓለም ዜጎቻቸውን ደስተኛ ያደረጉ ሀገራት ከ1 እስከ 10 በደረጃ ፊንላንድ፤ ዴንማርክ፤ አይስላንድ፤ እስራኤል፤ ኔዘርላንድ፤ ሲዊዲን፤ ሲዊዘርላንድ፤ ሉግዘምበርግ፤ ኒውዚላንድ እና ኦስትሪያ ሲሆኑ፤
በዓለም የዜጎቻቸው የደስተኝነት ደረጃ የመጨረሻዎቹ ሀገራት ከ1 እስከ 10 በደረጃ አፍጋኒስታን፤ ሊባኖስ፤ ሴራሊዮን፤ ዛምቢያ፤ ኮንጎ፤ ቦትስዋና፤ ማላዊ፤ ኮሞሮስ፤ ታንዛኒያ፤ እና ዛምቢያ ናቸው፡፡
በዓለም ላይ ዜጎቻቸው ደስተኛ ከሆኑባቸው ሀገራት 14ኛ የሆነችው ሃያሏ ሀገር አሜሪካ (ዜጎች 76ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ላይ ደርሰዋል) ስትሆን ከመጨረሻዎች ሀገራት 14ኛላይ ደግሞ የተቀመጠች ኢትዮጲያ (ዜጎች 1ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ ላይ ደርሰዋል) ነች፡፡
የዓለም የገንዘብ ድርጅት ሪፖርት ለማነጻጸር እየሞከረ ያለው በጠቅላላ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ የሆነችው ሉግዘምበርግ (120ሺ ዶላር በላይ የነፍስ ወከፍ ገቢ) ነገር ግን ዜጎቿ በደስተኝነት መለኪያ በዓለም 9ኛ ናቸው፡፡ ዜጎቿ በደስተኝነት መለኪያ አንደኛ የሆኑላት ሀገር ፊንላንድ በነፍስ ወከፍ ገቢ (48ሺ ዶላር የነፍስ ወከፍ ገቢ) ሲታይ በዓለም ላይ ከ20ኛ በታች ነች፡፡
ስለዚህ የዓለም የገንዘብ ድርጅት አመክንዬ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (የነፍስ ወከፍ ገቢ) በዘለለ መመልከት ይገባል (ዜጎች ያላቸው ማህበራዊ ድጋፍ፤ የጤና ሽፋን፤ በህይወት የመኖራቸው እድሜ ጣሪያ፤ የመኖር እና የመናገር ነጻነታቸው፤ ደግነታቸው/ልግስናቸው፤ አነስተኛ ሙስና መኖር፤ ወዘተ) ለማለት ነው፡፡
የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን በኑሮ ደስተኝነትን አይፈጥርም (IMF, 2023)! የዜጎችን በኑሮ ያላቸውን ደስተኝነት ከGDP እና ከነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን ለይቶ መመልከት ይገባል (IMF: Looking beyond GDP)! በ2023 ጠንካራ ኢኮኖሚ ኖሯቸው ዜጎቻቸው በደስተኝነት መለኪያ ዝቅተኛ የሆኑ ሀገራት ዝርዝር! በ2023 ደካማ ኢኮኖሚ ኖሯቸው ዜጎቻቸው በደስተኝነት መለኪያ የተሻሉ ሀገራት ዝርዝር! የኢትዮጲያ ዜጎች በኑሮ ያላቸው የደስተኝነት ደረጃ ከመጨረሻዎቹ መካከል ነው! የዚህን የIMF: World Happiness Report, 2023 ሪፖርት ንጽጽር ለመመልከት የሚከተለውን የትንታኔ ቪዲዮ
https://youtu.be/SdCqjjHrXOI ይመልከቱ!