👉ከሱና ቤተሰብ ላይ ያለ በሽታ‼️
------------------------------
👉....ልክ እንደ ቂያማ ቀን ነፍሴ ነፍሴ በማለት የራሱን ህይወት ማመቻቸት እንጅ ወንድሜስ ወይም እህቴስ የሚል የመዋደድ ተስፋ የመተዛዘን ተግባሩ ብቻ ሳይሆን ጠረኑም እየጠፋ ነው ይህ እጅግ ያሳዝናል።
እርስ በርስ መጠያየቅን ፣መዘያየርን፣መመካከርን፣መተሳሰብን ያዘዘው አሏህ ያስተማሩት ነብዩ ቢሆንም የሱናው ሰው ከዚህ ተግባር በአብዛኛው አምጿል ለምን ሲል የሚጠይቅም የለም‼️
👉ማንም የማንም ጉዳይ አያሳስበውም በል እንደውም በተቃራኒው ይህን ነገር የቢዲዓ አካላት በሚገርም ጥበብ ሲፈፅሙትና ሲተገብሩት ይስተዋላል።
👉የኛ ሰወች ግን ከመገፋፋት ፣ከመከፋፋት፣ከምቀኝነትና ከቅናት ውጭ በመልካም ስንረዳዳና ስንተዋወስ አንስተዋልም።
.....በግሩፓችን ቅዱስ ለመሆን ሞክረን ፃድቅ ፃድቅ ተጫውተን በግል ወይም በውስጥ መስመር ግን እከሌን እንደት እንጥለፈው እሱን በምን ተሰሚነቱን እንቀንስበት ከኛ በታች የሚሆነው በምንድነው ማንን በምን መልክ ልከን ወደ ፊትና አስገብተን ስሙን እናጠልሽበት የሚሉ የሰይጣን ፈረሶች እየበዙ ነው።
👉ዋጋ የከፈልክላቸው ሰወች ሳይቀሩ ስምህን የሚጠሩህ የችግራቸው መውጫ ሰበብ እስከምትሆንላቸው ድረስ ነው ለችግራቸው ሰበብ ከሆንካቸው በኋላ የመጀመሪያም የመጨረሻም ጠላታቸው አንተ ነህ ለምን⁉️
ይህ አይነት ባህሪ የሱና ሰው ነኝ ከሚል አካል ለምን ድክመታችንን ማን ይንገረን⁉️
👉በሴቶች ጉዳይ ከግንባር ቀደምትነት ስማችን በመጥፎ የሚነሳው የሱና ሰወች ነን ይህስ ጉዳይ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው ⁉️መንሀጃን አይጎዳውም⁉️ እህቶችን ከሱና አያርቅም⁉️
ሆን ብለው ሴቶችን እያጠመዱ ክብረ ንፅናቸውን ብሎም ገንዘባቸውን መጠው ከጨረሱ በሗላ አዕሞሯቸውን አዝገው የሚያሰናብቱ እጅግ የከፉ አውሬወች በሱና ፕሮፋይል ስር የተሸጎጡ ናቸው።
👉በነገር ተክነው ➍➌ሜትር የረዘመ ምላስ ይዘው ያለምንም ሀያዕ ለፊትና ብቅ የሚሉት አል-አሰርይ፣አሰለፍይ፣ሌላም ሌላም የሚል የረቀቀ ፕሮፋይል የለጠፉ እንስቶች ናቸው።
👉የስንቶችን በፍቅር የተሞላ ህይወት በምቀኝነትና በቅናት በክፋትም ጭምር በሴራ የጥላቻ መርዝ የሚነፉበት በሱና ስም የሚነግዱ #ዶዩስ ሴትና ወንዶች ናቸው።
👉በስደት ምድርም ሆነ በሀገር ቤት እጂግ ዘግናኝ ግፍ የምንሰማው አብዛኛው ከ100%90 እናውቃለን በሚሉ ደናቁርቶች ነው።
ከሁሉም የሚያሳዝነው ነገር ይህ ሁሉ ግፍ ከመኖሩ ጋር አሁንም በማስመሰል መቀጠሉን ተክነንበታል።
አንዳንዶቻችንማ እንዳትናገረኝ አልናገርህም በሚመስል ቃል ኪዳን ውስጥ ነን ።
ያሳዝናል በዚህ ነገር ላይ ትኩረት የሚሰጥበትም ለመናገርም የሚፈልግ አለመኖሩ ደግሞ የበለጠ ጉዳዩን እያባባሰው ነው።
⛔️መቼ እንደምንነቃ አላውቅም ብቻ እናሳዝናለን ሀቂቃ አንዳችን ለአንዳችን የመተባበር፣ የመጠያየቅ፣የመተዛዘን ዲናዊ ግደታችንን እየሳሳ የመጣበት ጊዜ ላይ ነን።
👉ወንድማችን በምን ሁኔታ ላይ ይሆን⁉️
👉እህታችን እንደት ሆና ይሆን እስኪ እንጠይቃት⁉️
የሚለው የመተዛዘን የዲን ትልቅ ክንፍ ከመሆኑም ባሻገር አንዳችን ለአንዳችን የምንጠነካከርበት ግሩም ቁልፍ ነበር።
እኛ ግን በመዋደድ ፈንታ መጣላት በመተዛዘን ፈንታ መቀናናት በመተዛዘን ፈንታ ምቀኝነትን እየሰነቀርን ብዙ መሆን የሌለባቸው ነገሮች ሆኑ ዛሬስ አንነቃምን⁉️
ማስመሰል ሰልችቶን በግሩፕም፣በቻናልም፣ በግልም፣ምድር ላይ ባለን ኑሮም ሆነ ሚዲያ ላይ ባለን ተግባር አንድ አይነት የምንሆነው መቼ ነው።
እኔ መቸም ወላሒ ተጨንቄ ነው የፃፍኩት ማስመሰል ይሰለቻል ይጨንቀኛልም።
👉የሚሆነውን ሁሉ እንዳላዩ ማለፍም ከባድ ውድቀት እንዳያመጣም ያስፈራል።
«በሽታውን የደበቀ መድሀኒት አይገኝለትምና ይልቅ ልብ ለልብ እንገናኝ ማስመሰሉ አይጠቅመንም።»
....✍️አቡ-ፋሩቅ
http://t.me/nuredinal_arebihttp://t.me/nuredinal_arebi