በዘመናችን አብዛሀኛው የትዳር መዘግየትና የፍቺ መጨመር ምክንያቶች
ሼይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ይላሉ፡- "የትዳር መዘግየት ምክንያቶች አሉት፤ ከእነዚህም መካከል የጋብቻ ወጪ መጨመር ይገኝበታል። ከእነዚህ ምክንያቶች ይበልጥ አሳሳቢ የሆኑት ደግሞ የሴቶች ተቀጥሮ መሥራትና የተለያዩ የሥራ መስኮች መብዛት ናቸው።
አንዲት ሴት በሩቅ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብ ወይም ምሥራቅ አገር ተቀጥራ በመሥራት ቤቷን ትታ ገንዘብ ለማግኘት ትሯሯጣለች። ባል አያስፈልጋትም፤ ምክንያቱም ባል ሥራዋን ያውክባታል፣ ይገድባታል። ስለዚህ ትዳርን ትተዋለች፤ ሀሳቧ ሁሉ ገንዘብ ማከማቸት ብቻ ነው። ይህ ደስታ ነው ብላ ታስብ ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ እውነተኛ ደስታ አይደለም። እውነተኛ ደስታ የሚገኘው መልካም ባል በማግኘት፣ ጥሩ ዘር በመተከልና በቤት ውስጥ በመርጋት ነው።
እሷ ግን ደሞዝና የሥራ ዕድልን እያሳደደች ትኖራለች። ይህ ነው ለትዳር መዘግየት ምክንያት የሆነው። ወንዶች በትዳር ውስጥ የማይታዘዙ፣ ልጆችን የማያሳድጉና በቤታቸው የማይገኙ ሴቶችን አይመርጡም። የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ለወንዶች አይጥማቸውም፤ እናም ይኸው ጉዳይ የትዳር ዕድሜ እንዲረዝምና ፍቺ እንዲበዛ ምክንያት ሆኗል።"
•
እውነተኛ ደስታን መፈለግ: ሼይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን እንደገለጹት፣ እውነተኛ ደስታ በገንዘብ ብቻ አይገኝም። ቤተሰብ መመስረት፣ ልጆችን ማሳደግ እና በትዳር ውስጥ መረጋጋት ትልቅ ደስታን ያመጣሉ።
•
ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች መወሰን: አንዲት ሴት ለትዳር እና ለቤተሰብ ቅድሚያ መስጠት አለባት ወይስ ለስራ እና ለገንዘብ? ይህን ጥያቄ ለራሷ መመለስ ያስፈልጋታል።
•
በትዳር ውስጥ መተሳሰብ እና መከባበር: ትዳር ስኬታማ እንዲሆን ሁለቱም ባለትዳሮች መተሳሰብ እና መከባበር አለባቸው። ሴት ለባሏ መታዘዝ እና የቤተሰቡን ፍላጎት ማሟላት አለባት። በተመሳሳይ መልኩ ባል ለሚስቱ ፍቅር እና እንክብካቤ መስጠት አለበት።
•
የሃይማኖትን መመሪያ መከተል: እስልምና ስለ ትዳር እና የቤተሰብ ህይወት ግልጽ መመሪያዎችን ይሰጣል። እነዚህን መመሪያዎች በመከተል ደስተኛ እና የተሳካ ትዳር መመስረት ይቻላል።
ወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይንt.me/Abu_hibetillah_Asselfiy