💰
ዘካ ሚወጣበት መጠን :-
1
ከሚዘሩ ነገራቶች በዝናብ ውሀ የበቀለ ከሆነ 1/10
በመስኖ የበቀል ከሆነ 1/20
2
ከጌጣጌጥ ነገራቶች ከሁሉም አይነት 1/40
3
ከቤት እንስሳ ግመል
ከ5 እስከ 25 በያንዳንዱ 5 ግመል 1በግ
25-35 ከደረሰ ቢንት መሃድ
36-45 ቢንት ለቡን
46-60 ሂቃ
61-75 ጀዘአ
76 -90 ሁለት ቢንት ለቡን
91-120 ሁለት ሂቃ
ከብት/በሬ/
30 ከደረሰ 1 ጥጃ አመት የሞላው
40 ከደረሰ 1 ወይፈን 2 አመት የሞላው
በግና ፍየል
ከ40 -120 ከደረሰ 1 በግ
ከ121 - 200 ከደረሰ 2 በግ
ከ201 - 300 ከደረሰ 3 በግ
ከ300 በላይ ከሆነ በየ መቶ 1 በግ
💰
የዘካ ገንዘብ ሚገባቸው ሰዎች ስምንት አይነት ናቸው :- 1. ድሀ
2. ድሀ ሆኖ የተወሰነ ነገር ያለው ።
3. ዘካ መሰብሰብ ላይ የተሰማራ ።
4. አዲስ የሰለመ በዲን እንዲጠነክር
5. ባረያ (ከባርነት ነፃ ሊወጣ የተፃፃፈ)
6. እዳ የገባ ሰው
7. በአላህ መንገድ ለሚታገሉ
8. መንገደኛ በእጁ የጉዞ የጨረሰ
ለነዚህ ሰዎች መሰጠቱ የአላህ ውሳኔ ነው።
📌
በአሁን ጊዜ ያለው የብር ኖት ሚመደበው በነብዩ صلى الله عليه وسلم ጊዜ በነበረው ዲናርና ዲርሃም ነው ሚሰላው ።
ዲርሃም 200 ከደረሰ ዲናር ደሞ 200 ከደረሰ ነው ዘካ ሚወጅበው በሀዲስ እንደተረጋገጠው ። 👉 እነሱ ወደ ግራም ሲቀየሩ ዲናር (ወርቅ)
85 ግራም አካባቢ ይሆናል ዲርሃም (ብር)
595 ግራም ።
ተንቀሳቃሽ ንብረት ያለው ሰው አሁን ባለው የብር ኖት አስልቶ ከመቶ 2.5 ፐርሰንት ያወጣል ወይም አጠቃላይ የመጣለትን ለ40 አካፍሎ የመጣለትን ያወጣል ።
📌
በዚህ አሁን ባለንበት ወቅት ያለው ዘካ ግዴታ ሚሆንበት መጠን በተንቀሳቃሽ ንብረት ሚለካው በዲናርና በዲርሃም ምትክ የመጡ ስለሆኑ በነዚ ከሁለት አንዱ መጠኑ ባነሰው ነው ። የዲናር መጠን 85*12000 = 1,020,000 ይሆናል ዲርሃም መጠን 595*240 =142,800 ነው ስለዚህ ልናወጣ ግዴታ ሚሆንብን አነስ ባለው መጠን ነውና 142,800 መጠን የደረሰ አመት የዞረበት ካፒታል ያለው ሰው ለአርባ 40 አካፍሎ 1/40ኛ ዘካ ከላይ ለተወሱ ለሚገባቸው ሰዎች ይሰጣል ።
ምሳሌ አንድ ሰው 200,000 ቢኖረው ለ40 ሲካፈል አምስት ሺህ ይሆናል ግዴታ ሚሆንበት ከ200ሺ ብር 5ሺ ብር ነው ።
👉ሌላው ተንቀሳቃሽ ሀብት ዘካ ሚወጣበት በተገዛበትና በሚሸጥበት ሳይሆን አሁን ገበያ ላይ ባለው ዋጋ ነው በእለቱ ዘካ በሚወጣበት ቀን ።
🚙
መኪና ቤት ህንፃ የመሰሉ ንብረቶች ዘካ የለባቸውም ነገር ግን ለንግድ የተያዙ ከሆነ ግን ዘካ አለባቸው ።✍ኡስታዝ ሙራድ ኸሊፋ
حفظه الله ورعاه
https://t.me/Muradkelifahttps://t.me/Muradkelifa👆
👉
https://t.me/AbuEkrimahttps://t.me/selefya/1940https://t.me/Abu_Yehya_ilyas_Awel/6180