በረመዳን ሙስሊም ከማህበረሰብ ጋር ያለው ግንኙነትይህ የእርስ በእርስ ግንኙነት ከሌሎች ግንኙነቶች አንፃር እጅግ እይታው ከፍ ያለ ሲሆን እያንዳንዱ እንቅስቃሴም በተግባር የሚገለፅ ነው፡፡ሙስሊሞች በማህበረሰባዊ ስራዎች ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባው ተሳትፎ ከፍተኛ ሊሆንም ተገቢ ነው፡፡በማህበረሰባዊ ግልጋሎቶች ላይ መከባበር፣መረዳዳትን ያጠቃለለ ስራዎች የሚሰሩበት የለውጥ ክፍል ነው፡፡
إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ አልሁጁራት 49፤10
ويقول رسول الله – صلى الله عليه وسلم -: ((مثل المؤمنين في توادِّهم وتراحمهم وتعاطفهم مثل الجسد، إذا اشتكى منه شيء تداعى له سائر الجسد بالسهر والحمى)) መልእክተኛው(ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ “ሙስሊሞች እርስ በርስ መዋደዳቸው፣ በእዝነታቸውና በርህራሄያቸው እንደ አንድ ሰውነት ናቸው። አንዱ የሰውነት ክፍል የታመመ እንደሆነ ሌላው የሰውነት ክፍል በትኩሣት እና ያለ እንቅልፍ በማደር ይታመማል” (ቡኻሪና ሙስሊም)
ሙስሊም ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋርይህ ማህበረሰባዊ ለውጥ ከስብከት በዘለለ መልኩ በተግባር እንዲገለፅም ኢስላም ያዛል፡፡ ከሌሎች ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር የማህበረሰባዊ ስራዎችን አለመተግበር ከኢስላማዊ መርህ ጋርም ያጋጫል፡፡አንድ ሰው ሁልጊዜም ቢሆን ጉጉቱ መልእክተኛውን(ሰዐወ) መከተልና እርሳቸውን መምሰል ይኖርበታል፡፡ መልእክተኛው(ሰዐወ) ደግሞ ከሙስሊሙም ጋር ሆነ ሙስሊም ካልሆኑ የማህበረሰቡ አካሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት በጥበብና በእዝነት ብሎም በመልካም ግሳፄ የታጀበ ነው፡፡ይህም ትልቅ ተግባር የኢስላም መንፈሱም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ አነህል 16፤125
ويقول رسول الله – صلى الله عليه وسلم : ((فوالله لأنْ يَهدِيَ الله بك رجلاً، خير لك من أن يكون لك حُمْر النَّعَم))
ነብዩ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፡ በጌታዬ እምላለሁ አንድን ሰው ወደ እውነተኛው መንገድ መምራት የቀያይ ግመሎች ባለቤት ከመሆን የተሻለ ነው፡፡
እነዚህ የለውጥ ክፍሎች ላይ በፅናት መታገልና መበራታት እንዲሁም ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት የአዎንታዊነትን አዲስ ገፅ መክፈት ነው፡፡ ከረመዳን ትምህርት ቤት እነዚህን ሙሉ የለውጥ ክፍሎች ለመሰነቅ እንዘጋጅ!
አላህ በሰላም ያድርሰን…….
https://t.me/alanisquranacademy