4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ
እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው።
ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc & @Kiya988
Buy ads: https://telega.io/c/amazing_fact_433

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ያልተዘመረለት የካራማራው ድል (የታሪክ ገጽ)

በ Youtube ቻናላችንን ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/VVF48oNiDm8?si=wt_va8joqHLigsCZ


Repost

እንግሊዝና ጋና የሚሻሙበት የቀን ሰራተኛ ፍሪዚ ማክቦንስ ።
.........
በጠዋት ይነሳና ፡ በጋና ዋና ከተማ አክራ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች ወዳሉበት ቦታ በመሄድ ፡ የቀን ሰራተኛ ይፈልጉ እንደሆን ይጠይቃል ። ስራ ከተገኘ ቀኑን ሙሉ ሲሚንቶ ሲሸከም ፡ ኮንክሪት ሲያቦካ ፡ በአካፋ ሲዝቅ ፡ በባሬላ ሲሸከም ይውልና ፡ ሲደክመው ፡ የእሱ ብጤ ከሆኑ ሰወች ጋር በጋራ በተከራዩት ፡ መብራት የሌለው ጨለማ ክፍል ውስጥ ሄዶ ጎኑን ያሳርፋል ።
............
ስራው ድካም አለው ፡ ተመጣጣኝ ክፍያም አያገኝም ፡ ሆኖም ሁሌም ህይወት ፊቷን አጥቁራበት እንደማትቀር ያስባል ። እና በአንድ ኢንተርቪው ላይ እንደገለፀው ፡ አንድ ቀን ህይወት እንደምትስቅልኝ አውቅ ነበር ብሏል ።
..................

🎚ፍሪዚ ማክቦንስ ፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ፡ አንድ ቀን ባላሰበው አጋጣሚ እንግሊዝ የመሄድ እድል አጋጠመው ፡ ሆኖም እዛ ሄዶ. ..  ቢያንስ ጋና ውስጥ እያለ የሚሰራው አይነት ፡ የቀን ስራ እንደሚያገኝ አስቦ ለንደን የደረሰው ፍሬዚ ነገሮች እንዳሰበው አልሆንለት አሉት ።
እና ለምኖ እየበላ ፡ የማክዶናልድ መደብሮች በረንዳ ስር ማደር ጀመረ ።
.........

🎚እንዲህ እንዲህ እያለ ፡ ቋንቋውን ፡ ሀገሩን እየለመደ ሲሄድ በአንድ የነጻ ጂም ውስጥ ተመዝግቦ መስራት ጀመረ ። ይህ ሁሉ ሲሆን ፡ በህልሙም በውኑም አንድ ቀን ቦክሰኛ እሆናለሁ ብሎ፡አስቦ አያውቅም ነበር ። እና በአንድ አጋጣሚ ፡ ለገቢ ማሰባሰቢያ ተብሎ በተዘጋጀ የቦክስ ግጥሚያ ላይ ተሳተፈ ። በዚህ ውድድርም በሚያስደነግጥ ሁኔታ ፡ ተጋጣሚውን በመርታት አሸነፈ ።
......
ልክ በዚያን እለትም የቦክስ አሰልጣኞች አይን ውስጥ ገባ ።
..........
ህይወት መልካም ጎኗን እንደምታሳየኝ ፡ አንድ ቀንም እንደምትስቅልኝ እያሰብኩ የኖርኩ ሰው ብሆንም ፡ በዚህ መልኩ ህይወቴ ይለወጣል ብዬ ግን አስቤ አላውቅም ፡ ነገር ግን ፈጣሪ መንገዶች እንዴት እንደሚጠርግ ያውቅ ነበርና ባላሰብኩት መንገድ አስጉዞ እዚህ አድርሶኛል ይላል ።
.........

🎚ከአመታት በኋላ ዛሬ ላይ ። ያ ፡ በፍቃደኝነትና በነጻ የውድድር መድረክ ፡ የቦክስ ጓንቱን አሟሽቶ ፡ የሪንጉን አለም የተዋወቀው ፍሪዚ ማክቦንስ ፡ በተለያዩ የቦክስ ውድድሮች ላይ ባሳየው ብቃት አብዛኛው ግጥሚያዎቹን በዝረራ እያሸነፈ ፡ እንግሊዛዊው ማይክ ታይሰን የሚል ስም ተሰጥቶታል ።  ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ  በእንግሊዝ ውስጥ በተካሄደው ታላቅ የቦክስ ውድድር ላይ ካሸነፈ በኋላ የዚህ ሰው ስም ይበልጥ መግነን ጀምሯል ።

🎚በጋና የኮንስትራክሽን ግንባታዎች ላይ ባሬላና አካፋ በመዛቅ የድህነት ጥግ ውስጥ ይኖር የነበረው ፍሬዚ ማክቦንስ አንድ ቀን የአለም ሻምፒዮን እንደሚሆን እያሰበ ፡ ወደፊት መገስገሱን ቀጥሏል ። ዛሬ ጋና እና እንግሊዝ ይህን ሰው ይሻሙበታል ። እንግሊዛዊው ማይክ ታይሰን ሳይሆን ጋናዊው ነው መባል ያለበት የሚል ነገር ሁሉ ይነሳበታል ።
.............

🎚ገንዘብና ዝና ከስር ከስሩ የሚከተሉት. ... በእንግሊዝና አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስሙ እየገነነ የመጣው የ32 አመቱ ፍሬዚ ማክቦንስ. ....

  በእጆቼ የሲሚንቶ መዛቂያ አካፋ ይዤ ፡ አንድ ቀን ህይወት እንደምትስቅልኝ አስብ የነበረው ነገር እንደተሳካ አውቄያለሁ ፡ ባልታሰበ አጋጣሚ ወደቦክስ ስፖርት አለም የገባሁት እጅግ ዘግይቼ ነው ።  ነገር ግን . ..... 
ዘግይቼ ጀመርኩ ማለት .... አልችልም ማለት አይደለም ። አንተም የዘገየህ ቢመስልህ እንኳን ማድረግ አትችልም ማለት አይደለምና ፡ የተሻለ ነገር ለመስራት ፡ የተሻለ ህይወት ለመኖር ዛሬውኑ ተነስ ። ሲል ይመክራል ።

..........

🛒@Amazing_fact_433
🛒@Amazing_fact_433


ፈረጃ : ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ

| በህዝብ መዋጮ የሚሰራዉና በኢትዮጵያ የመጀመርያዉ (croudfunding) ፊልም የሆነዉ ፈረጃ የተሰኘዉ የቦክስ ፊልም ከብዙ ዝግጅትና አድካሚ ጉዞ በኋላ የታሰበዉ በጀት ባይሞላም ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ።

አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ሂደቱ ከባድ እንደነበር ተናግሮ የቦክስ ፊልም እንደመሆኑ ለቀረፃዉ ብዙ ሰው እንደሚያስፈልግና በተሳትፎ እንዲያግዙት ወጣቱን ኃይል ጠይቋል።

በገንዘብና በሀሳብ ላገዙት ሰዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋናዉንም አቅርቧል።


@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433


አልበርት አንስታይን የካቲት 5 1930 ዓ.ም ላይ ለልጁ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከለት፦

“ህይወት ብስክሌት እንደመንዳት ናት ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ። የስኬት ሰው ብቻ ለመሆን አትሞክር ይልቅ ዋጋ ያለው ሰው ለመሆን ሞክር። ምክንያቱም ስኬት የሚለካው በምትወስደው ነገር ሲሆን ዋጋ የሚለካው ደግሞ በምትሰጠው ነገር ነው።

ሞኝ ማለት አንድ አይነት ነገርን ደጋግሞ ሰርቶ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነው። የተለየውን መንገድ ተከተል አዲስ ነገር ታገኛለህ። አትቀመጥ ምክንያቱም ምድራችን አደገኛ የሆነችው በክፉ ሰዎች ስራ ሳይሆን ምንም በማይሰሩ ሰዎች ውጤት ነው።

ትምህርት እውነትን አያስተምርም ይልቅ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበልጸጊያ ልምምድ ነው። የሌሎች ጫጫታ የአንተን የውስጥ ድምፅ እንዲውጠው ማድረግ የለብህም። ማንም ሰው ባንተ ላይ ገደቦች እንዲጥል አትፍቀድ፤ ገደብህ በራስህ ያወጣኸው የህይወት መመርያ መሆን አለበት


🛒@Amazing_fact_433
🛒@Amazing_fact_433


ፕሮፌሰሩ

ፕሮፌሰሩ ክፍል ውስጥ የተሰበሰቡትን ተማሪዎች እንዲህ ብሎ ይጠይቃል "86,400 ብር አላችሁ እንበል፤ አንድ ሰው ይመጣና 1ዐብር ይዞባቹ ይሮጣል፤ እና ለዛች 1ዐብር ብላቹ 86,390ብሩን ትታቹ ሰውየውን ተከትላቹ ትሮጣላቹ ወይስ የቀረውን 86,390ብር ይዛቹ መንገዳችሁን ትቀጥላላቹ?"

ተማሪዎቹም ቀላል ጥያቄ ይሆንባቸውና "የቀረውን ብር ይዘን እንቀጥላለን እንጂ!" ብለው መለሱ።

ፕሮፌሰሩም እንዲህ አላቸው "ይሄውላቹ በቀን ውስጥ 86,400 ሰከንዶች አላችሁ። እናም አንድ ሰው በ1ዐ ሰከንድ ውስጥ ለተናገራቹ ነገር ቀኑን ሙሉ ስትበሳጩ፣ ስታዝኑ፣ ስትናደዱ የምትውሉ ከሆነ 86,390 ሰከንዶቹንም ታጣላቹ።

ሰው አሉታዊ ነገር የሚናገራቹ ከራሱ አንፃር ነው። እናም መንገዳችሁን ቀጥሉና የቀሩትን 86,390 ሰከንዶችን አትርፉ!"

(ከማህበራዊ ሚዲያ
)

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

6.5k 0 91 5 228

ከቅርብ ወራት ወዲህ በቻይናዋ Zhejiang province
ጎዳናዎች ላይ የሚታይ አንድ ድቡልቡል ጎማ የሚመስል እንግዳ ሮቦት አለ ።
...
ይህ ሮቦት አንዴ ሀይል ከተሞላ ፡ ለሀያ ሰአታት ያህል በዝግታ ወደዛ ወደዚ እየተሽከረከረ ፡ ሲለውም አማካኝ ቦታ መርጦ በመቆም ፡ በዛ ጎዳና የሚያልፈውን ሰው ሁሉ እጅግ ጥራት ባለው HD ካሜራ አይኖቹ ይቃኛል ።
.......
በዚህ መሀል ታዲያ ወንጀል የሚሰራ ወይም ፡ በፖሊስ የሚፈለግ አንድ ሰው ካገኘ በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ሪፖርት ያደርግና ተፈላጊውን ሰው በቅርብ ርቀት መከታተል ይጀምራል ።

በስፍራው የፖሊስ ሀይል ከሌለ ደግሞ ወንጀለኛን ለመያዝ ተብሎ በውስጡ የተገጠመውን መረብ በመተኮስ ሰውየው በመረቡ ተጠምዶ መንቀሳቀስ እንዳይችል ካደረገው በኋላ ፖሊስ መጥቶ እስኪወስደው ይጠብቃል ።
....
RT-G robot ይባላል ፡ ይህ ባለፈው አመት ወደስራ የገባው ይህ ሮቦት ፡ ከፖሊሶች ጋር በህብረት በመሆን ፡ እና ብቻውንም ሮንድ በመውጣት በተጨናነቁ የገበያ ቦታዎች እንዲሁም የፀጥታ ጥበቃ በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች እየተዘዋወረ የአካባቢውን ደህንነት ይቆጣጠራል ።
የገበያ ቦታዎችን ከዘራፊዎች ይጠብቃል ፡ በዚህ መሀል ለዘረፋ የተሰማሩ ወንጀሎች ከሆኑና ይህንን ሮቦት ሊተናኮሉት ከሞከሩ ደግሞ እራሱን ለመከላከልና ፡ ቦታውን ከዘረፋ ለማዳን የታጠቀውን የጭስ ቦንብ በመልቀቅ ፡ ወንጀለኞቹን ከስፍራው እንዲለቁ ማድረግ ይችላል ። ከጠንካራ ቁስ ስለተሰራም በምንም ነገር ሊጎዳ አይችልም ።
...

RT-G robot የፖሊስ አጋዥ ሆኖ ፀጥታን ከማስከበር ባለፈም ፡ የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜም ወደቦታው በፍጥነት ደርሶ ፡ የነብስ አድን ስራ ይሰራል ።

ይህ ሮቦት ባለበት ሰርቆ ወይም ወንጀል ሰርቶ ማምለጥ አይታሰብም ፡ በሰአት እስከ ሰላሳ ኪሎ ሜትር እየሮጠ ወንጀለኛውን ለመያዝ ይጥራል ።
በውሀ ውስጥ ይሄዳል ፡ አስቸጋሪ የተባሉ መንገዶች ሁሉ ለሱ ምንም ማለት አይደለም ።
ይህ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ለመሰማራት በጥቅም ላይ የዋለው ይህ ሮቦት በዚህ መሰል ስራ ላይ የተሰማራና በጥቅም ላይ የዋለ የአለማችን የመጀመሪያው ሮቦት ሆኗል


አንብበው ከጨረሱ 👍

6.9k 0 10 4 262



የscholarship እድል የሚያስገኘው የALX Pathway ፕሮግራም ምዝገባ ሊያልቅ 4 ቀን ብቻ ቀረው!

የALX ‘Pathway’ ፕሮግራምን በመውሰድ፣ የአለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ እድል ለማግኘት ይመዝገቡ። የዚህ ስኮላርሺፕ እድል በጥቅሉ በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር፣ ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር፣ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው።

ALX ከ14 በላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት አለው። አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙት America ሲሆን፣ በEurope እና South Africa የሚገኙም አሉ።

የዚህ የትብብር ስምምነት ዋና ይዘት፣ የALX Pathway ኘሮግራምን በስኬት የሚጨርሱ ልጆች፣ በእነዚህ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት እና የስኮላርሺፕ እድሎች የሚያገኙበትን መንገድ ማስፋት ነው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለማየት፣ እንዲሁም ምዝገባውን በተሳካ ሁንያ ለማጠናቀቅ፣ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch.

ወደ ምዝገባው ቀጥታ ለመሄድ ይህንን ተጫኑ - https://www.alxafrica.com/join-pathway/

7.1k 0 14 25 18

Old Group ካላችሁ ታማኙ አቡሼ አለላችሁ ?👍

2022 - 500 ብር
2021 - 500 ብር
2020 - 500 ብር
2019 - 500 ብር
2018 - 500 ብር

ያላችሁ መሸጥ ከፈለጉ ያዋሩኝ👉 @Abushe433

History Clear ያሎነ ትክክለኛ Old ብቻ ነው ምፈልገው ልታደክሙኝ አትምጡ🫡


የቻይና ወጣቶች ቤት ተከራይቶ ከመኖር ይልቅ በሆቴሎች ማደር እየመረጡ ነው

#Ethiopia | በቻይና ቤት ተከራይቶ ወይም ገዝቶ ከመኖር ይልቅ በሆቴሎች በቋሚነት መኖርን የሚመርጡ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::

ወጣቶቹ በሀገራቸው ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ አንጻር ሆቴሎችን ምርጫቸው አድርገዋል::

በተለይ ደግሞ ቀለል ያለ ህይወትን ልመምራት እና ጭንቀትን ለማስወገድ ሆቴል ተመራጭ እየሆነ ነው::

መኖርያ ቤት መከራየት ማለት ተቀማጭ ሊሆን የሚችልን ገንዘብ እንደመክፈል ነው:: በዛ ላይ በየወሩ የውሃ የመብራት እንዲሁም የኤሌክትሪክም ክፍያዎች መከፈል አለበት።

በሆቴል ውስጥ ግን ይህንን ሁሉ ክፍያ አንዴ ነው የምንከፍለው በማለት ሆቴል እንደሚሻላቸው ወጣቶቹ መናገራቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ከቤታቸውም የሚሰሩት ስራ ያላቸውም ሆኑ በየጊዜው ስራ እና አካባቢን የሚቀይሩ ቢሆኑ ይሄ አኗኗር ተስማምቷቸዋል።

ይሄን የኑሮ ዘይቤ በኮቪድ 19 በተነሳበት ጊዜ እንደተጀመረ እና ሆቴሎችም ብዙ እንቅስቃሴ ስለሌላቸው በጊዜው ዋጋቸው ቅናሽ ስለነበር አብዛኛውን ሆቴሎች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ደንበኞችን ይቀበሉ ነበር።

ታድያ እድሜ ለኮቪድ ይሁንና የሚሉት ቻይናውያን ወጣቶች ጠባብ መኖርያ ቤትን ከሚከራዩበት ባነሰ ዋጋ ጥሩ በሚባሉ ሆቴሎች መኖር ምርጫቸው ሆኗል።


በአለም ከአንድ እናት ብዙ ልጆች የተወለዱት ትልቁ ቁጥር 69 ሲሆን ሪከርዱም በአንዲት ሩሲያዊት ዜጋ ይገኛል። ከነዚህም 16ጊዜ መንታ ... 7ጊዜ በአንዴ ሶስት ሶስት እና አራት ጊዜ ደግሞ አራት አራት ልጆችን መውለድ ችላለች።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

7.6k 0 33 25 166

ሺ በላይ የአማርኛ እና English መጽሐፎች(በpdf) በነፃ የሚገኙባቸውን

📚ሳይኮሎጂ ,
📚ልብወለድ ,
📚ታሪክ እና
ሌሎችም

«እንደምርጫዎ» ቻናላችንን  ይቀላቀሉ!


https://t.me/Enmare1988/5301
https://t.me/Enmare1988/5301
💬https://t.me/Enmare1988/5301


የኮሪደር ልማት ጉዳት ያደረሱ ከብቶች ተቀጡ::

13 ከብቶች የኮሪደር ልማት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው 65 ሺ ብር በቅጣት የከብቶቹ ባለቤቶች እንዲከፍሉ ተደረገ

በቦሌ ወረዳ 12 አስተዳደር የኮሪደር ልማት ላይ በቸልተኝነት ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉ የከብት ባለቤቶች በ13 ከብት እያንዳንዳቸው 5ሺ ብር በጠቅላላ 65 ሺ ብር እንዲቀጡ በዛሬው እለት ተደርጓል።

የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ማህበረሰቡ ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠብ አሳስቧል ።

ምን ትላላቹ እናንተ

@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433

7.4k 0 25 11 236

ከ2ሺህ በላይ አባወራዎች እንደሚነሱ አስታወቀ

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚያስነሳቸው 2,500 አባወራዎች መኖሪያ ቤቶች እንደሚገነባ እና በሚቀጥለው ዓመት ሕዳር ወር እንደሚያስረክባቸው እንዲሁም በተመሳሳይ ወር የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ እንደሚጀመር ተናግረዋል።

አየር መንገዱ በቢሾፍቱ አቅራቢያ አቡሴራ አካባቢ አዲስ የሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚቀጥለው ዓመት ሕዳር ወር እንደሚጀመር አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

በቢሾፍቱ አቅራብያ ይገነባል የተባለው ግዙፍ አውሮፕላን ማረፍያ 3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፍ መሆኑን የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ከመሬታቸው ለሚነሱ 2,500 አባወራዎች "በሕዳር ወር ወደ አዲሱ መኖርያቸው እንደሚዘዋወሩ" አስታውቀዋል።

አቶ መስፍን በአካባቢው የግብርና ምርቶች ማቀነባበርያ እና የንግድ ተቋማትን ጨምሮ አዳዲስ አገልግሎት መስጫዎች እንደሚገነቡ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያስገነባው አየር ማረፊያ ግንባታ ከአራት ዓመታት በኋላ የሚጠናቀቅ መሆኑን እና በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የአውሮፕላን ማረፊያ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው ይህ አዲሱ አየር መንገድ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን እደሚያስተናግድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

"በሁለት ምዕራፍ ግንባታው የሚከናወን ይሆናል። በመጀመሪያው ምዕራፍ 60 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችለው ይገነባል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 50 ሚሊዮን ተጓዦችን የሚያስተናግደው ሁለተኛው ምዕራፍ ይገነባል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ እአአ በ2029 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል" ብለዋል።

ለዓመታት በአዲስ አበባ የሚገኘው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።
የአየር መንገዱ ዕድገት በጨመረ ቁጥር ለአውሮፕላን ማረፊያው የተለያዩ የማስፋፊያ ስራዎች ሲከናወኑ ቢቆይም፣ በዓመት 25 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ በሚችልበት የመጨረሻ አቅሙ ላይ መድረሱን አቶ መስፍን አስታውቀዋል።


አንብበው ከጨረሱ👍




"  ማን እንደሆንክ ባላውቅም ፡ ዝነኛ እንደሆንክ ሰምቻለሁ "

ስለ አሜሪካን የነጻ ትግል ስፖርት ሲነሳ ፡ ስማቸው ቀድመው ከሚጠሩ ሰወች መሀል አንዱ Ric Flair ነው ።
ሪክ ከአመታት በፊት ከ16 ጊዜ በላይ የአሜሪካን የነጻ ትግል ስፖርት ሻምፒዮን የሆነ ፡ ስሙ በአለም ዙሪያ ባሉ የዚህ ስፖርት አድናቂዎች ዘንድ የገነነ
በተለይ በአሜሪካን እስካሁን በሄደበት በክብር የሚስተናገድ ታዋቂና ተወዳጅ ሰው  ነው ።

እና ባለፈው ሳምንት ፡ በአንድ መዝናኛ ቦታ ውስጥ እያለ ፡ አንዲት ቲክቶክ ያገነናት ፡ ታዋቂነቷ ከቲክቶክ ፎሎወሮቿ ያላለፈ ወጣት ሴት ፡  ሪክ ፍሌር እየተዝናና ወዳለበት ቦታ በመሄድ ፡ ትከሻውን ከነካች በኋላ

" HI ...ቲክቶክ ላይ ላይቭ ሆኜ ነው የማወራህ ፡ እና ጓደኞቼ አንተ ታዋቂ እንደሆንክ ነግረውኝ ነው ፡ በርግጥ እኔ ባላቅህም ፎቶ ብንነሳ ደስ ይለኛል "  በማለት ጠየቀችው ።
ሪክ የዚህችን ወጣት  ስርአት የሌለው ጥያቄ ከሰማ በኋላ. ..ፊቱን እንኳን ወደሷ አዙሮ ሳያያት ......
" No  አብሬሽ ፎቶ ለመነሳት ፍቃደኛ አይደለሁም "  አላትና ከነመፈጠሯ ረስቷት ወደነበረበት ሙድ ተመለሰ ።
.....

ቲክቶከሯ ላይቭ የሚከታተሏት ፎሎወሮቿ እያዩኣት በራሷ የስነምግባር ችግር ምክንያት ሀፍረቷን  ተከናነበች ። ይህች ቲክቶከር ራሷን ያሰበችው ሁሉም ሰው ከሷ ጋር ፎቶ ለመነሳትና ቪዲዮ ለመቀረፅ እንደሚፈልግ ፡ በእንዴትም ያለ አቀራረብ ብትቀርብ ችግር እንደሌለው አድርጋ ነው የምታስበው ።

ሪክ ፍሌር እጅግ በበዛ ትህትናው የሚታወቅ ሰው ነው ፡ ይህ ሰው ፡ በየቀኑ በየሄደበት  አክብረውት ፍቅራቸውንና አድናቆታቸውን ሊገፁለት ከሚመጡ ከብዙ ሰወች ጋር ፎቶ ሲነሳና ፡ ሲፈርም የሚውል ሰው ነበር ።
ሆኖም ለዚህች ሴት ፊቱን እንኳን ሳያዞር እንቢታውን የገለፀው በልጅቱ ስርአት የጎደለው ጥያቄ ነበር ።
ማን እንደሆንክ ባላውቅም ታዋቂ እንደሆንክ ጓደኞቼ ነግረውኛል ከምትል ፡ ማን እንደሆነ ጠይቃ በስርአት ብታወራው በፍቅር ጥያቄዋን በመለሰና በላይቭ እየታየች ባላፈረች ነበር  ።
....
ማነው የተከበረ. .. ማክበርን ያወቀ የሚባለው ለዚህ ነው ። መልካም ምግባር ሁሌም  ያስከብራል

7.8k 0 11 3 130

ሚጢጢዬዋ ደሴት

በሀገረ ኮሎምቢያ  የምትገኝ ደሴት ስትሆን
Santa Cruz Island 🇨🇴 Colombia ትባላለች

1,200 ህዝብ ይኖርባታል
150 ቤቶች አሉ
ለከተማዋ በሙሉ የሚበቃ 4 ጄኔረተሮች አሉ
1ሆቴል አለ
2 ሱቅ
እስከ 10 ክፍል አንድ ትምህርት ቤት አለ ከዛ ብኃላ ወደ ኮሎምቢያ  ሄደው ይማራሉ
ምንም አይነት ፖሊስ የለም ተዋደው ተከባብረው እና ተፋቅረው ይኖራሉ ግን የራሳቸው መተዳደሪያ ደንብ አላቸው
አሳ በብዛት ይመገባሉ( የሁሌም ምግባቸው ሊባል ይችላል)
በቀን ውስጥ ከ3 ጊዜ በላይ እየተሰበሰቡ ይደንሳሉ
ከህፃናች ልጆች ጀመሮ ሁሉም በሚባል ሁኔታ ዋና ይችላሉ
እንደ አንድ መኖሪያ መንደር ከተመሰረተች ወይም ሰው ይኖርባት ከጀመረ 150 አመት ሆኗታል

9.1k 0 16 14 202

2023 1 - 10 ወር የተከፈተ group yalew in box @Mr_jomann


ይህ ቦታ ''million dollar point'' በመባል ይታወቃል ፓሲፊክ ውቂያኖስ Vanuatu በምትባል ደሴት ውስጥ ነው ፣ ብዙ ዋጋ የያዙ አሜሪካ  ለ2ተኛው የአለም ጦርነት የተጠቀመችውን የተለያዩ መሳሪያዎችና እቃዎችን ያስቀመጠችበት ቦታ ነው ።  በጊዜው እቃዎችን ወደ አሜሪካ ከመውሰድ ይልቅ እዚው ማስቀመጡ ኪሳራውን ዝቅ ስለሚያደርግ ነበር ።

@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433

10k 0 9 36 87

የ 1922 የ ኖቬል ተሸላሚ ሽልማት የተሸለመዉ 'Neils Bohr' h'carlsberg' የቢራ  ፋብሪካ የእድሜ ልክ የቢራ ሽልማት ቀርቦለት ነበር፤

ቢራዉ ከፋብሪካው እስከ መኖሪያ ቤቱ ድረስ በቧንቧ ይመጣለት ነበር።

10.6k 0 32 26 340
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.