ዐቢይና ድሮናቸው
ዐቢይ አህመድ “ለማይቀረው ጦርነት ድሮን በማምረት ዝግጅት አድርጌያለሁ” አሉ
ከሰሞኑ ዐቢይ አህመድ አሊ በተለያዩ ተቋማት እየተንቀሳቀሱ አዲስ ጦርነት አይቀሬ መሆኑን የሚጠቁሙ ንግግሮችን እያደረጉ ነው፡፡
ከአራት አመታት በፊት የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ ዛሬ ጦር ሊገጥሙ ከሚዝቱባቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ከሳዋ እስከ ደብረዘይት ተጉዘው የጦር መሳሪያ አቅማቸውን ሲፈትሹና ዛቻ ሲያስተላልፉ ነበር፡፡
እንዳሰቡትም መሳሪያቸውን ከፈተሹና ከተመለከቱ በኋላ በሚዲያዎቻቸው በኩል የመሳሪያ አቅም እንዳላቸውና የሰው ሃይላቸውም ዝግጁ መሆኑን አሳውቀው በይፋ ወደ ጦርነት ገብተዋል፡፡
እንዲሁም በአማራ ክልል ከፋኖ ጋር የሚያደርጉት ጦርነት ጠንከር ሲል በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ እያሉ ወታደራዊ አቅም ያላቸው በማስመሰል ይዝታሉ፡፡
ከሰሞኑ ግን የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያሳጣቸው ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ከፋኖ እና ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር የጀመሩትን ውጊያ ማሸነፍ ያቃታቸው ዐቢይ ፣ ከህወሃት ጋር ለሌላ ዙር ጦርነት የተፋጠጡት የበሻሻው ሰው ፣ አሁን ደግሞ በባሰ መልኩ ከኤርትራ ጋር አዲስ ጦርነት ውስጥ ለመግባት ተዘጋጅተዋል፡፡
ይህን ዝግጅታቸውንም በሚያረጋግጥ መልኩ የኮሪደር ልማት ላይ ሳይክል የመንዳት ትርኢታቸውን ገታ አድርገው የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘኖቻቸውን ቅኝት ላይ ተጠምደዋል፡፡
ከሰሞኑ ሞርታር ፣ ታንክና መድፍን ጨምሮ ተተኳሾችንም ማምረት ጀምሬያለሁ ሲሉ መሬት ያልረገጠ ውሸት አስምተው ነበር፡፡
ሳምንት እንኳን ሳይሞላው በትናንትናው እለት የጦር ድሮን እያመረትኩ ነው ብለዋል፡፡ እነዚህን ድሮኖች የማመርተው ደግሞ ጦርነት ስለሚያጋጥምና ዝግጅት ስለሚያስፈልገኝ ነው ሲሉ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት አይቀሬ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሰውዬው ይህን የሚሉት ታንክና መድፍም ይሁን ድሮን እውን እያመረቱ ሳይሆን ፣ የጠላቶቼን ስነልቦና ይቆጣጠርልኛል በሚል ነው የሚል አስተያየትም እያሰጠ ነው።
ሮሃ ቲቪ
መጋቢት /07/2017 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ
# አዲሱን የአሻራ ፌስቡክ ገፅ ይወዳጁ 👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900ይሕ አዲሱ የአሻራ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል ነው
በጠየቃችሁን መሰረት በዩቱዩብ መረጃወችን ለማድረስ ቻናሉን ከፍተናል አሁኑኑ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ትኩስና አዳዲስ ሁነቶችን ለማግኘት አዲሱን የአሻራ ዩትዩብ ቻነል Subscribe ያድርጉ‼
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/UH4zZz1lxmcየተከበራችሁ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች ነባሩ የአሻራ ዩትዩብ ቻነል ስለተዘጋ አዲሱን ቻነል
ሰብስክራይብ በማድረግ መረጃዎችን ይከታተላሉ ‼
👇👇👇
https://www.youtube.com/@asharaPress-s7b4n