🍁“𝚊𝚢𝚖𝚒 𝚒𝚜𝚕𝚊𝚖𝚒𝚌 𝚙𝚘𝚜𝚝"🍁


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የጀነት ስብስብ ያደርገን ዘንድ ምኞታችን ነው 🌛
for cross and sugesstion👇
https://t.me/aymi52

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


✍በቁርአን ውስጥ ከተጠቀሱ 25 ነብያት መካከል ስማቸው በሱራ ( በቁርአን ምዕራፍ) የተሰየሙት ነብያቶች ስንት ናቸው??
So‘rovnoma
  •   3
  •   5
  •   6
  •   7
  •   8
  •   9
  •   18
  •   መልስ የለም
25 ta ovoz




✍በኢብራሂም አ.ሰ ጊዜ አለምን ያስተዳድር የነበረው አመፀኛ ንጉስ ማን ይባላል??

@aymi22

መልስ👍መ// ነምሩድ✅

ታሪኩ በጣም ረጅም ቢሆንም ቀንጨብ አድርገን👇

ከሀድዎች የሚያመልኩትን ጣኦት ኢብራሁም ዐ.ሰ በሰባበሩት ጊዜ...

ጣዖት ተገዢዎች #ለነምሩድ ሁኔታውን ተረኩለት። ነምሩድ #ኢብራሒምን አስጠራቸው። በደንባቸው መሠረት ማንኛውም ሰው ወደ #ነምሩድ ሲገባ ሱጁድ ይወርዳል። #ኢብራሒም (ዐ ሰ) ሲገቡ ሱጁድ አልወረዱም ነበር።
#ነምሩድ_ኢብራሒምን ለምን እንዳልሰገዱ ሲጠይቃቸው #ኢብራሒም እንዲህ በማለት መለሱለት፦

#ኢብራሒም፦ አንተንም እኔንም ለፈጠረ አምላክ እንጅ አልሰግድም…!"

#ነምሩድ፦ ጌታህ ማነው?_

#ኢብራሒም፦ የእኔ ጌታ ያ ሕይወት ሰጪ እና ሐይወት ነሺ የሆነው (አምላክ) ነው። "

#ነምሩድ፦ እኔም ህያው አደርጋለሁ፣ እገድላለሁም!"_
ሁለት ሰዎችን ከእስር ቤት አስመጣ እና አንዱን ገድሎ አንዱን በነፃ አሰናበተው። ቀጥሎ እንዲህ አለ፦
"አየህ! እኔም ይህንን ማድረግ እችላለሁ" አለ።

#ነምሩድ ያልገባው ነገር ቢኖር ሕይወት የአምላክ እስትንፋስ፣ ሞት ደግሞ የሩህ ከአካል መለየት መሆኑን ነው። እዚህ ላይ ኢብራሒም እንዲህ አሉ፦

"የእኔ ጌታ ፀሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣታል፣ አንተ አቅሙ ካለህ በምዕራብ እንድትወጣ አድርጋት!" አሉት።

ቁርአን ይህንን ክስተት በሚከተለው መልኩ ይገልፀዋል፦

أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

ወደዚያ አላህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ እገድላለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አላህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል (አንተ) ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ፤ (መልስ አጣ) አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡
📚አል-በቀራህ - 258📚

የቁርአን ሙፈሲሩ አል በይዷዊ ስለ ነምሩድ ሲናገሩ፦

ቂልነቱ የጀመረው መለኮታዊነትን ለራሱ ለማድረግ ሲሞክር ነው» ይላሉ። አላህ (ሱ ወ) አብዝቶ በሰጠው የገንዘብ እና የሹምነት ፀጋ በማመስገን ፋንታ ተቃራኒውን አደረገ። አስተባበለ። የአላህን ህልውና ካደ።~~~~~~~
~~~~~
~~~~ኢብራሒም አ.ሰ ስደት ከወጡ በኋላ በግብዝነታቸው እና በትዕቢተኛነታቸው እምነትን ባልተቀበሉ ሰዎች ላይ የትንኙ መንጋ እንደ አቧራ ነበር የወረደባቸው። ትንኞቹ የጣዖታውያኑን ደም መምጠጥ ጀመሩ። ሰዎቹም በያሉበት ደርቀው ቀሩ። አንዷ ትንኝ #በነምሩድ_አፍንጫ ውስጥ ገብታ ጭንቅላቱ ውስጥ ድረስ ዘለቀች። #ነምሩድ የሚሰማውን ህመም ለማስታገስ ያለማቋረጥ ጭንቅላቱን ይደበድብ ነበር። በመጨረሻም ጭንቅላቱ ተሰንጥቆ ለህልፈት በቃ።

ቁርአን ክስተቱን በዚህ መልኩ ይገልፅልናል፦

وَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَخْسَرِينَ
በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ በጣም ከሳሪዎችም አደረግናቸው፡፡
📚ሱረቱ አል-አንቢያ 70📚


✍በኢብራሂም አ.ሰ ጊዜ አለምን ያስተዳድር የነበረው አመፀኛ ንጉስ ማን ይባላል??

ሀ// አዘር
ለ// ፈራኦን
ሐ// አቡ ጀህል
መ// ነምሩድ
ሠ//ፈህረዝ
ረ// ጀርሙዝ
ሰ// ሃማን
ሸ// መልስ የለም

@aymi22


📌ጥያቄ📌
📌 ብዙ ጊዜ በየማህበራዊ ሚዲያው የሚተላለፍ አንድ ሀዲስ አለ ፣ እሱም ረመዷን መች እንደሆነ #ለመጀመሪያ ጊዜ ለወንድሙ የተናገረ #እሳት ከሱ ሀራም ትሆንበታለች ይላልና ይህ ሀዲስ ትክክለኛነቱ እንዴት ነው⁉️

✅መልስ✅
✅ ይህ ሀዲስ #በየትኛውን የሀዲስ ኪታብ ላይ በጭራሽ ሊገኝ #ይቅርና በተቀጠፋ ሀዲሶች መዝገብ ውስጥ እንኳን #የማይገኝ በነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ #የተቀጠፈ ሀዲስ ነው።ይህን ሀዲስ በየትኛውም መልኩ #ማሰራጨትም ሆነ #ማስተላለፍ የተከለከለ ነው።

♻️ ምንጭ: ኢማሙ ሲዩጢይ ፣
ተድሪቡ ራዊ

እባካችሁ በዚህ ነገር ላይ ብዙ ሰው ስለሚሳሳት ሼር በማድረግ ስተቱን ያሳወቁ

JOIN & SHARE

@aymi22
@aymi22

👆👆 ይ🀄️ላ🀄️ሉን 👆👆


በየቀኑ በሰላምና ጤና ስለምንቀበላቸው ቀናት ሁሉ ምስጋና ለአላህ ይሁን፤   አልሐምዱሊላህ!!

ሰበሀል ኸይር!🥰

@aymi22


✍ከትልልቅ የቂያማ ምልክቶች መካከል ያልሆነው የቱ ነው??

@aymi22


መልስ👍ረ// የረሱል ሰ.አ.ወ መላክ✅ ይህ ከትንንሽ ምልክት ነው።

#ታላላቅ_የቂያማ _ምልክቶች_አስር ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ አንዱም አልተከሰተም፡፡ ኢማም ሙሰሊም ከሁዘይፋ ኢብን አስየድ እንዳስተላለፉት

« اطلع النبي صلى الله عليه وسلم علينا ونحن نتذاكر ، فقال : ما تذاكرون ؟ قالوا : نذكر الساعة . قال : إنها لن تقوم حتى تروا قبلها عشر آيات : فذكر الدخان والدجال ، والدابة ، وطلوع الشمس من مغربها ، ونزول عيسى ابن مريم صلى الله عليه وسلم ، ويأجوج ومأجوج ، وثلاثة خسوف : خسف بالمشرق وخسف بالمغرب وخسف بجزيرة العرب ، وآخر ذلك نار تخرج من اليمن تطرد الناس إلى محشرهم » صحيح مسلم

“በሆነ እለት አብረን እየተዋወስን ሳለን ነቢዩ ሰዐወ ወደኛ ብቅ አለሉና “ምንድ ነው ምትመካከሩት?” አሉን እኛም “ቂማን እየተዋወስን ነው” ብለን መለስን እሳቸውም እንዲህ አሉ “#አስር_ተአምሮች_ሳይከሰቱ_ቂያማ_አይቆምም ከዚያ አስሩን ሲዘረዝሩ
1✅ጭስ፣
2✅ደጀል፣
3✅እንስሳ፣
4✅የፀሐይ ከምዕራብ መውጣት፣
5✅የኢሳን መውረድ፣
6✅ጊዜ ምስራቅ ምዕራብና የአረብ ደሴት የሚከሰቱ የመሬት መስመጥ ጠቅሰው የመጨረሻው
7✅ከየመን ተቁስቅሶ ሰዎችን ወደ መሰብሰቢያቸው የምትሰድ እሳት እንደምትቀሰቀስ ተናገሩ፡፡” (ሙስሊም 2901)

በሌሎች ሀዲሶች
8✅የመህዲ መምጣት
9✅የከዕባ መፍረስና
10✅የቁርአን ከምድር መነሳት ተነግሯል፡፡

አብዛኞች ዑለማዎች እንደሚሉት ከሆነ አስሩ የቂያማ ምልክቶች ከላይ የተጠቀሱ ሶስቱ ምልክቶችና የሁዘይፋ ኢብን አስየድ ሀዲስ ላይ ከተጠቀሱት ከመሬት መስመጥ ውጭ ላይ ምልክቶች ናቸው፡፡

✅የመሬት መስመጥ ሀዲሱ ላይ እንደተባለ ከቂያማ ምልክቶች አንዱ ቢሆንም ከአስሩ ምልክቶች ቀደም ብሎ የሚከሰት ምልክት ነው፡፡

@aymi22


✍ከትልልቅ የቂያማ ምልክቶች መካከል ያልሆነው የቱ ነው??


ሀ// የደጃም መምጣት
ለ// ፀሀይ ከምዕራብ መውጣት
ሐ// የመህዲ መምጣት
መ// የኢሳ መውረድ
ሠ// የካዕባ መፍረስ
ረ// የረሱል ሰ.አ.ወ መላክ
ሰ// ሁሉም መልስ ነው
ሸ// መልስ የለም


አሏህ ሚስቶቻችሁንም / ባሎቻችሁንም እንዲሁም ልጆቻችሁን ሷሊህ ያድርግላችሁ
ለሚስቶቻችሁ የትኛውን ቃል ትጠቀማላችሁ ?

የኔ ሴትዮ 🙄🙄 ??
የኔ ሚስት 😍😍 ??
የኔ ጎደኛ 🤔🤔 ??



ጥያቄ ? 🤔🤔🤔

በሶስቱ ቃሎች መሀል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ሴት ሚስት ጎደኛ ?

መልስ :

ሴት :

በአንድ ወንድና ሴት መሀል የአካል መቀራረብ ኖሮ ነገር ግን የአስተሳሰብና የውዴታ መገጣጠም ከሌለ " ሴት " የሚለውን እንጠቀማለን ።


ሚስት :

በሁለቱ መሀል የአካል መቀራረብ ኖሮ በተጨማሪ በአስተሳሰብና በፍቅር መገጣጠም ካለ " ሚስት " እንላለን

ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ :
‏( ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻧﻮﺡ ‏) የኑህ ሴት
‏( ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻟﻮﻁ ‏) የሉጥ ሴት

የኑህ ሚስት ወይም የሉጥ ሚስት ብሎ አልጠራቸውም ምክኒያቱም በመሀላቸው የእምነት ልዩነት ስለነበረ !!!

ሁለቱም ነብያቶች የነበሩ ሴቶቹ ግን ያላመኑ ነበሩና ሁለቱንም ሴት በሚል ጠቀሳቸው ።

የፊርዓውንን ሚስት እንደዚሁ " ሴት " በሚል አወሳት ምክኒያቱም እሷ በአሏህ አንድነት ስታምን እሱ ደግሞ በክህደቱ ቀጠለ ስለዚህ " ሴት " እንጅ ሚስት አላለም ።

በሌላ ቦታ ደግሞ ቁርአን " ሚስት " የሚለውን በእምታቸውና በአካል የተዛመዱትን ሲያወሳ እንመልከት
ስለ አባታችን አደም ቁርአን እንዲህ አለ :

( ﻭﻗﻠﻨﺎ ﻳﺎ ءاﺩﻡ ﺍﺳﻜﻦ ﺃﻧﺖ ﻭﺯﻭﺟﻚ ﺍﻟﺠﻨﺔ ‏)

አዳም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ ።

ነብያችንን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በተመለከተ ደግሞ :

‏( ﻳﺎ ﺃﻳﻬﺎ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﻗﻞ ﻷﺯﻭﺍﺟﻚ ‏)
አንተ ነብይ ሆይ ለሚስቶችህ እንዲህ በላቸው

በመሀላቸው የእምነትም ሆነ የፍቅር የአካል መወዳጀት ስለነበር " ሚስት " በሚል አወሳ ።

ሰይዲና ዘከሪያ ዓለይሂ ሰላም ሚስታቸው በእምነትም በአካልም በፍቅርም ተወዳጅተው እያለ እሳቸው ግን " ሴት " የሚለውን ቃል ተጠቅመው ነበር ቁርአን እንዲህ ይነግረናል

ﻳﻘﻮﻝ الله تعالى :
‏( ﻭﻛﺎﻧﺖ ﺍﻣﺮﺃﺗﻲ ﻋﺎﻗﺮﺍً ‏)
ሚስቴም መካን ነበረች

ምክኒያቱ ደግሞ ባለመውለዷ በመሀላቸው ችግር እንዳለ ለማመላከት ጭንቀታቸውን ወደ አሏህ አቤቱታ እያቀረቡ ስለነበር ።

ነገር ግን አሏህ ከሷ ልጅ ከሰጣቸው በሃላ ቁርአን ላይ እንዲህ ተቀምጦ እማገኘዋለን „

فقال الله تعالى
‏( ﻓﺎﺳﺘﺠﺒﻨﺎ ﻟﻪ ﻭﻭﻫﺒﻨﺎ ﻟﻪ ﻳﺤﻴﻰ ﻭﺃﺻﻠﺤﻨﺎ ﻟﻪ ﺯﻭﺟﻪ ‏).
ጥሪውን ተቀልን ምላሽም ሰጠነው የህያ የሚባል ልጅም ሰጠነው " ሚስቱንም" እንድተወልድ አደረግን ይላል

አቡ ለሀብ ቤት አለመግባባት መኖሩን አሏህ አጋልጧለረ
ﻓﻘﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ :
‏( ﻭﺍﻣﺮﺃﺗﻪ ﺣﻤﺎﻟﺔ ﺍﻟﺤﻄﺐ ‏)
ሴትዮዋም እንጨት ተሸካሞ ናት

በሁለቱ መሀል ምንም አይነት መጣጣም አለመኖሩን ለማሳየት !!!

ባልደረባ ( ጎደኛ )

በባልና ሚስት መሀል የአስተሳሰብ ብሎም የአካል መወዳጀት ሲጠፋ ቁርአን ጎደኛ ( ባልደረባ ) የሚለውን ይጠቀማል

አሏህ ብዙ ቦታ ላይ በቂያማ ቀን ክስተት ላይ ባልደረባ የሚለውን ቃል ይጠቀማል
قال تعالى :
‏( ﻳﻮﻡ ﻳﻔﺮ ﺍﻟﻤﺮﺀ ﻣﻦ ﺃﺧﻴﻪ ﻭﺃﻣﻪ ﺃﺑﻴﻪ ﻭﺻﺎﺣﺒﺘﻪ ﻭﺑﻨﻴﻪ ‏).
ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን ከናቱም ከአባቱም ከባልደረባውም ከልጁም

አስፈሪ ቀን በመሆኑ ሁላቸውም በራሳቸው ጉዳይ በመጨነቅ የአካልም ሆነ የመተሳሰብ ሁኔታው ስለተቋረጠ

ﻓﺴﺒﺤﺎﻥ ﺍﻟﻠﻪ الذي أنزل هذا الكتاب المعجز
والذي قال فيه في سورة
االإسراء - الآية 88
(قُل لَّئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنسُ وَالْجِنُّ عَلَىٰ أَن يَأْتُوا بِمِثْلِ هَٰذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرا.)

جعلنا الله جميعاً ممن يقولون:
(رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَاما )

أعجبتني فتمنيت لكم الفائدة فنقلتها لكم .


🌺 ሁሉም ነገር ላይመለስ ይጎዛል …
ዱዓ ሲቀር በምኞት ልከሀው ስጦታ ይዞ ይመለሳል …💐

ያ አሏህ ንግግሬ የደረሰቻቸውን ሁሉ በቀልባቸው ውስጥ ደስታን ሙላላቸው,
ያንተን ፍቅርና ውዴታ ለግሳቸው አንተን የወደደን ሁሉ ውዴታንም ጭምር ወፍቃቸው,

አምላኬ ሆይ ወዳንተ የሚያቃርብ ማንኛውንም ስራ እንዲሰሩ አግራላቸው, በምድርህ ላይ የተረጋጉ ሆነው እንጅ አይጎዙ እዝነትህ በየትም ሆነው ይከተላቸው ጭንቀታቸውን አንሳላቸው መልካሙን ነገር ሁሉ አግራላቸው
ያ ረብ !!!
@aymi522
@aymi522


ይቺን ቀልድ ጀባ ልበላችሁ
አንዱ አእራብይ(የገጠር ሰዉ) ዲነል ኢስላምን የማያቅ ግሮ ሰሪ ገብቶ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ
አስተናጋጇን ጠራት
አስተናጋጅ:-ምን ልታዘዝ
ሰዉየዉ፡-ዳሽን ቢራ
አስተናጋጅ፡-ዳሽን ቢራ የለም ቅዱስ ጊወርጊስ ቢራ ነዉ ያለዉ
ሰዉየዉ:-ላኢላሀ ኢለሏህ ሙሀመዱ ረሱሉሏህ አንቺ ሸይጧን አላህን አፈሪም ልታከፍሪኝ ሀይማኖቴን ልታስቀይሪኝ ነዉ..ባልነቃ ሸዉደሽኝ ነበር አንች አጭበርባሪ አላህ ከአንቺ ተንኮል ጠበቀኝ ብላት ከተቀመጠበት ወንበር ሊነሳ ሲል ...
አስተናጋጇ:-እሺ ጋሼ ይቅርታ ግን አረቄ አለ እሱን ልቅዳልህ??አለችዉ
ሰዉየዉ፡-እሱ ይሻላል እሱን ቅጅልኝ አላት
ከዛም አስተናጋጇ አረቄዉን ይዛ መጥታ ስትቀዳለት ምን ቢል ጥሩ ነዉ
አንቺ ነግሬሻለሁ ስትቀጂ ቀስ አርገሽ ቅጂ .... ልብሴ ጡሀራ ነዉ ይሄን አረቄ አፍሰሽ እንዳነጂሽኝ😆😆😆 ብሏት እርፍ

ምን ለማለት ነዉ የእኛ የብዙዎቻችን ሂወት ከዚህ ቀልድ ጋር የተያያዘ ነዉ ሀራም መሆኑን እያወቅን ግን በሌላ ሲስተም ያንን ሀራም ነገር መጠቀም ልባችን ይከጅላል ለማለት ያህል ነዉ...ከሀራም ለመራቅ ዛሬ ነገ መባል አያስፈልገዉም የሞት መሄጃዉ ባቡሩ ፈጣን ነዉ....ዛሬ ላይ ስንሆን ደቂቃዎች ሰከንዶች ሲሽከረከሩ ከእድሚያችን እየቀነስን መሆኑን አንዘንጋ፡፡


እና @aymi22

✍✍ 👇👇👇👇👇
@aymi522
@aymi522


أختي المسلمة لا تطردي نفسك من رحمة الله

አንቺ ሙስሊም የሆንሽው እህቴ ሆይ ከአሏህ ረህመት ራስሽን አታርቂ በገዛ ፍቃድሽ።


قال اﻹﻣﺎم ﻣﺴﻠﻢ رحمه الله:

حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ يَحْيَى ، أَخْبَرَنَا أَبُو مُعَاوِيَةَ ، عَنْ هِشَامِ بْنِ عُرْوَةَ ، عَنْ فَاطِمَةَ بِنْتِ الْمُنْذِرِ ، عَنْ أَسْمَاءَ بِنْتِ أَبِي بَكْرٍ ، قَالَتْ : جَاءَتِ امْرَأَةٌ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ، فَقَالَتْ : يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّ لِي ابْنَةً عُرَيِّسًا أَصَابَتْهَا حَصْبَةٌ فَتَمَرَّقَ شَعْرُهَا أَفَأَصِلُهُ ، فَقَالَ : لَعَنَ اللَّهُ الْوَاصِلَةَ وَالْمُسْتَوْصِلَة"َ صحيح مسلم

ኢማሙ ሙስሊም ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ:- ያህያ ኢብኑ ያህያ አውርቶናል ፣ አቡ ሙዓዊያ ነግሮናል ከሂሻም ቢን ዑርዋ ከፊጢማ ቢንት ሙንዚር ከአስማእ ቢንት አቢ በከር ረድየላሁ ዐንሃ እሷም እንድህ ትላለች "አንዲት ሴት ወደ ነብያችን ﷺ መጣችና እንዲህ አለች:-

"ያ ረሱለሏህ እኔ ሙሽራ ልጅ አለችኝ ፀጉራን (ቁስል ነገር) አግኝቷት ተነቃቀለ ወይም ተሰባበረባት ስለዚህ ልቀጥልላት(ዊግ)?

“የአላህ መልክተኛ ﷺ ዊግ ቀጣይዋንና ተቀጣይዋን ተረግመዋል" አሉዋት።

@aymi22
@aymi22


✍ከሚከተሉት ምንዳቸው ያለ ገደብ የሚከፈላቸው የትኞቹ ናቸው??

@aymi22

መልስ 👍ረ✅ ነው

"ሀ" ና "ለ" ድርብ ሽልማት ነው ያላቻው ያ ማለት የታወቀ ነው።

🌸አላህ ያለ ሂሳብ (ያለ ገደብ) የሚመነዳቸው 3 (ሦስት) ነገሮች ናቸው።
#እነሱም:-👇

1✅ታጋሾች ( ሰብረኞች)
#አላህ እንድህ ይላል:-
قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَـٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ

(ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ #ታጋሾቹ_ምንዳቸውን_የሚሰጡት_ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡
📚አል-ዙመር 10📚

2✅ይቅር ባዮች
#አሁንም አላህ እንድህ ይላል:-

وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ

የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ #ይቅርም_ያለና_ያሳመረ_ሰው_ምንዳው_በአላህ_ላይ_ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡
📚ሱረቱ አል-ሹራ 40📚

3✅ፃም
አቡ ሁረይራ ረ.አ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
#ኃያሉና የተከበረው አላህ እንዲህ ይላል፡- #ፆም_የኔ_ነው፤ #ለእርሱ_ምንዳ_የምሰጠውም_እኔ_ነኝ፡፡ (አንድ ሰው) ለእኔ ሲል ወሲባዊ ስሜቱን፣ ምግቡን እና መጠጡን ይተዋል፡፡ ፆም ልክ እንደጋሻ ነው፤ የሚፆም ሰው ሁለት ደስታ አለው፡፡ ፆሙን ሲፈታ የመጀመሪያውን ደስታ (ሲጎናፀፍ)፤ ጌታው ጋር ሲገናኝ ደግሞ (በፆሙ በሚያገኘው ሽልማት ምክንያት) ሌላ ደስታ ይጠብቀዋል፡፡ የፆመኛ ሰው አፍ ጠረን መለወጥ በአላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ነው፡፡”

عَنْأَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " يَقُولُ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ : الصَّوْمُ لِي، وَأَنَا أَجْزِي بِهِ، يَدَعُ شَهْوَتَهُ وَأَكْلَهُ وَشُرْبَهُ مِنْ أَجْلِي، وَالصَّوْمُ جُنَّةٌ ، وَلِلصَّائِمِ فَرْحَتَانِ : فَرْحَةٌ حِينَ يُفْطِرُ، وَفَرْحَةٌ حِينَ يَلْقَى رَبَّهُ، وَلَخُلُوفُ فَمِ الصَّائِمِ أَطْيَبُ عِنْدَ اللَّهِ مِنْ رِيحِ الْمِسْكِ "

☝️ሀዛ ወላሁ አዕለም☝️ አላህ ከሚጠቀሙት ያድርገን

@aymi22


....... "
ገበያውም አይደል — ናፍቆቱ ’ሚጎዳ
መኪናም ከንቱ ነው — ቢቆምም ቢነዳ
መስጂድና ቂርአት — ደርሱ ሆድ ያባባል
ያለነዚህ ህይወት —ከቶ ምን ይረባል? !!?
የመጣብንን በላእ አላህ ያንሳልን! መጨረሻችንን በተውሒድ በሱና ላይ
ያድርገው።

Amiinn

©️©️©️©️

@aymi22
@aymi22


وعن لقيط بن عامر رضي الله عنه: أنه أتى النبي صلى الله عليه وسلم، فقال: إن أبي شيخ كبير، لا يستطيع الحج، ولا العمرة، ولا الظعن قال: ((حج عن أبيك واعتمر)) رواه أبو داود والترمذي، وقال: ((حديث حسن صحيح)).



ለቂጥ ኢብኑ ዓሚር رضي الله عنه እንዳስተላለፉት፥ ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘንድ መጡና:- አባቴ አዛውንት ነው። ሐጅም ዑምራም ማድረግ አይችልም። ጉዞ ለመሄድም አቅም የለውም" በማለት ጠየኳቸው። መልዕክተኛውም صلى الله عليه وسلم " ስለ አባትህ ሆነህ ሐጅም ዑምራም አድርግለት" አሉት።



Join and share
@aymi22
@aymi22


Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!


ሴት ልጅ የአካሌ ክፋይ ናት ያስከፋት ያስከፋኛል
ያሳዘናት ያሳዝነኛል

ረሱል ﷺ


✍ከሚከተሉት ምንዳቸው ያለ ገደብ የሚከፈላቸው የትኞቹ ናቸው??

ሀ//የአላህንና የአሳዳሪውን ሀቅ የጠበቀ ባሪያ
ለ// ሴት ባሪያን ጥሩ አህላቅ አስተምሮ ነፃ ያለ
ሐ// ታጋሾች ( ሰብረኛ)
መ// ይቅር ባዮች
ሠ// ሀ ና ሐ መልስ ናቸው
ረ// ሐ ና መ መልስ ናቸው
ሰ// ሁሉም መልስ ነው
ሸ// መልስ አልተጠቀሰም


ወንጀል ለመስራት ባሰብን ቁጥር ሁልጊዜ እነዚህ ሶስት የቁርአን አያቶችን እናስታውስ።
1)"ألم يعلم بأن الله يرى"
"አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?"
2)"ومن يتق الله يجعله مخرجا"
"አላህን የፈራ መውጫ መንገድ ያደርግለታል።"
3)"ولمن خاف مقام ربه جنتان"
"ጌታው ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ጀነቶች አሉለት
።"

@aymi22
@aymi22


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
@aymi22


✍የሰላት ቅድመ ሁኔታዎች (መስፈርቶች) ስንት ናቸው??

@aymi22

መልስ👍ሰ//9✅
እነሱም:-👇

1✅ሙስሊም መሆን

2✅ጤናማ አዕምሮ ያለው መሆን

3✅ነገሮችን ለይቶ የሚችልበት እድሜ ላይ መድረስ

4✅ሀደስን ማስወገድ ማለትም በብልት (በመቀመጫ) በኩል የሚወጣ ማንኛውንም ነገር ማሶገድ (ማፅዳት)

5✅ ነጃሳን ማስወገድ

6✅ሀፍረተ ገላን መሸፈን

7✅የሶላት ጊዜ መግባት (ሰአቱ መድረስ)

8✅ወደ ቂብላ (ካዕባ) አቅጣጫ መዞር

9✅ ኒያ ናቸው።

☝️ሀዛ ወላሁ አዕለም

@aymi22

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.