የምላጭ ጠርዝ ፅንሰ-ሀሳብ /The Razor’s Edge
አንዱ “ሊጀምር” ያለውን ፕሮጀክት ሌላው ይጀምረዋል፡፡ አንዱ ግለሰብ ሊያጠናቅቅ “ትንሽ የቀረውን” ተግባር ሌላው ሰርቶ ያጠናቅቀዋል፡፡ አንዱ ያየውን አጋጣሚ ፤ ሌላው በተግባር ይተረጉመዋል፡፡ አንዱ ተማሪ ሊያልፍ “ትንሽ” ውጤት ቀርቶት ሲወድቅ፤
ሌላው ተማሪ አልፎ ይገኛል ምንም እንኳ በሁለቱ ተማሪዎች መሀል ያለው ልዩነት ከመቶው የአንድ ነጥብ ልዩነት ቢሆንም ያቺ አንድ ነጥብ ግን ሁሉንም ልዩነት ትፈጥራለች፡፡ የሥፖርቱ ዓለም ታሪክ ዜናዎች በምላጭ ጠርዝ ፅንሰ-ሀሳብ ምሳሌዎች የበለፀገ ነው፡፡
ለምሳሌ በ1976 ዓ.ም እ.ኤ.አ በሞንትሪያል ካናዳ ውስጥ በተደረገው የኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ ለመቶ ሜትር ርቀት ሩጫ ሥምንት የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ቀርበው ነበር፤ የኦሎምፒኩን የወርቅ ሜዳልያ የወሰደው ተወዳዳሪ መጨረሻ ከወጣው ተወዳዳሪ አንድ- አስረኛ ሰከንድ በመቅደም ብቻ ነበር፡፡
በ1946 ዓ.ም እ.ኤ.አ አርምድ የሚል መጠሪያ ያለው በዩናይትድ ስቴት ታሪክ የመጀመሪያው የውድድር ፈረስ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ለሚያስገኙ ሽልማቶች በሙያው ላይ በቆየበት ጊዜ ተወዳድሮ - 76,500 $ (ሰባት መቶ ስድሳ አንድ ሺህ አምስት መቶ ዶላር) ገቢ አግኝቷል፡፡
በዛ ዓመት በተገኘው ገቢ መሰረት ሁለተኛ በመውጣት 75,000 ዶላር ገቢ ያገኘው የውድድር ፈረስ ፤ አንደኛ በወጣው ፈረስ “አፍንጫ” ርቀት ልክ ተቀድሞ ነው፡፡ አሁን እነዚህ ፈረሶች ለየቅል ያሸነፉትን ሪከርድ ብንመረምር አርምድ ከቅርብ ተፎካካሪው አስራ ሶስት እጥፍ የተሻለ ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁለት ፈረሶች በውድድራቸው ወቅት ያስመዘገቡትን “ሰዓት” ብናነፃፅር አርምድ በአራት ፐርሰንት እንኳ የበላይ እንዳልሆነ ትደርስበታለህ!
📓ስትወለድ ሀብታም ነበርክ
✍️ ቦብ ፕሮክተሮ
📖
@Bemnet_Library