Buna Tech ቡና ቴክ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha



Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


በ2016፣ ሎውረንስ ጆን ሪፕል የተባሉ የ70 ዓመት ሰው በካንሳስ የሚገኝን ባንክ ዘረፉ እና ፖሊሶች መጥተው እስር ቤት እንዲወስዱት ባንክ ቤት ይቀመጣል።

ታዲያ ይህ ነገር ያዩ ፖሊሶች ለምን ብሩን ዘርፎ ባንክ ቤት እንደጠቀመጠ ሲጠይቁት ከሚስቱ ጋር ከመኖር ይልቅ እስር ቤት መኖር እንደሚመርጥ ነገራቸው። በስተመጨረሻም ሰውዬው ተይዞ የስድስት ወር የቤት እስራት ማለትም ከሚስቱ ጋር እንዲኖር ተፈረደበት ።


Anonymous የራሺያውን Official ቴሌቪዢን Hack አድርገውት የዩክሬንን ሙዚቃ ከፍተውበታል። በRuski ቋንቋ F**k putin የሚል ሙዚቃ😅

Anonymous ግን የAmerica puppet ሳይሆን አይቀርም😅😂


The Power of Cyber


ከሩሲያ የሶፍትዌር ኩባንያ የስራ እድል ያገኘው የ7 ዓመቱ ህጻን

የሰባት አመቱ ኮዲንግ ባለሙያ ሰርጌይ ከሩሲያ የሶፍትዌር ኩባንያ ፕሮ32 አስተዳደር ቡድንን እንዲቀላቀል የስራ ግብዣ ቀርቦለታል፡፡

ታዳጊው ‘የኮዲንግ ሞዛርት” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ሲሆን በዩቲዩብ ላይ በሚያቀርባቸው የፕሮግራሚንግ የማስተማሪያ ቪዲዮዎች ታዋቂነትን ያተረፈው ሰርጌይ በኮዲንግ ብቃቱ እና በማስተማር ችሎታው አድናቆትን አትርፏል።

ይህንን ተከትሎ የሩሲያ የሶፍትዌር ኩባንያ ፕሮ32 ማሰልጠኛ ኃላፊ ሆኖ ድርጅቱን እንዲቀላቀል የስራ ቅጥር ደብዳቤ ልኮለታል።

ነገር ግን በሩሲያ ህግ መሰረት አንድ ሰው ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ ለመስራት እድሜው 14 አመት መድረስ አለበት፡፡

ስለዚህም ሰርጌይ እድሜው ለቅጥር እስከሚደርስ ድረስ ድርጅቱን ማገዝ በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ከወላጆቹ ጋር መወያየቱን የፕሮ32 ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢጎር ማንዲክ ለቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ተናግሯል፡፡

ቤተሰቦቹ ልጃቸው ባገኘው እድል በጣም ደስተኛ እንደሆኑ እና ሰርጌይ ኩባንያውን እስኪቀላቀል በጉጉት እንደሚጠብቁ ገልጸውልኛል ብሏል፡፡

ታዳጊው ሰርጌይ 3ሺህ 500 ተከታዮች ባሉት የዩትዩብ ቻናሉ ላይ በሩሲያኛ እንዳንዴም በተሰባበረ በእንግሊዘኛ በሚለቃቸው ስለኮዲንግ፣ ፓይቶን፣ ፕሮግራሚንግ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ስለ ተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በማስተማር ‘የኮዲንግ ሞዛርት’ ለመባል ችሏል፡፡
https://t.me/bunatech
https://t.me/bunatech


#Telegram_update

Telegram Nov 17, 2024 ጀምሮ በTelegram mini apps ላይ ያተኮረ የተለያዩ አዳዲስ ፊቸሮችን አስተዋውቋል።

ከተለቀቁት ማሻሻያዎች መካከል:-

Full-Screen Mode
Mini apps አሁን ላይ የlandscape እና የfullscreen feature አስተዋውቋል። ይህም game ለመጫወት አንዲሁም በland-scape  የሚሰሩ ስራዎችን መስራት ያስችላል።

Device Motion Tracking
Mini apps የኛን የስልክ እንቅስቃሴ ማወቅ የሚችሉበት feature ሲሆን ስልካችንን እያንቀሳቀስን ለምንጫወታቸው games አስፈላጊም ነው። ለምሳሌ ያክል major maze መጥቀስ ይቻላል።

Home Screen Shortcuts
ልክ ስልካችን ላይ እንደምንጠቀማቸው መተግበሪያዎች telegram mini አፖችንም home screen ላይ ማስቀመጥ እና home screen ላይ የሚገኘውን mini app icon አንዴ ብቻ በመንካት ቀጥታ ወደ mini app የምንገባበት feature ነው።

Geolocation Access
የኛን መገኛ ለmini apps አበልፃጊዎች /developers/ የምናጋራበት feature ሲሆን አበልፃጊዎቹም የኛ መገኛ ላይ በመመስረት location-based mini app እንዲሰሩ ያስችላቸዋል። ነገርግን ይህ feature እኛ ፈቅደን allow ካላደረግነው መጀመሪያ disallow ወይም disable ነው።


አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከአቶሚክ ቦምብ በላይ የምድራችን ስጋት ነው - ጥናት

የጆርጂያ የቴክኖሎጂ ተቋም ከስታንፎርድ እና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት ያደረጉት ጥናት የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚጠቀሙ ፕሮግራሞች ሰላም የማይወዱና ጦርነት ሰባቂ መሆናቸውን አመላክቷል።

ፕሮግራሞቹ ለወረራ፣ የሳይበር ጥቃትና የሰላም ጥሪ ክስተቶች የሚሰጡት ግብረመልስ (ጥቃት ወይስ ሰላማዊ ምላሽ) ምን እንደሚመስል ተፈትነው መቶ በመቶ ጦርነትን መርጠዋል።

ድርድር፣ ጊዜ ሰጥቶ መምከር፣ ቸል ብሎ ማለፍ ለሚሉና መሰል ምላሾች ይልቅ ፈጣን የአጻፋ እርምጃ መውሰድ፣ ሀገርን መውረር፣ የሳይበር ጥቃትን ማሳደግ፣ ድሮኖች እና የኒዩክሌር መሳሪያዎችን መጠቀም የሚሉ አማራጮችን መምረጣቸውም ተገልጿል።

የቻትጂፒቲ ተከታይ ቻትጂፒቲ 3.5 ከሁሉም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፕሮግራሞች ቁጡው ነው የተባለ ሲሆን፥ ለተመራማሪዎቹ የሰጠው አስተያየት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

“በርካታ ሀገራት የኒዩክሌር መሳሪያ አላቸው፤ አንዳንዶች መሳሪያዎቹን ማስወገድ እንዳለባቸው ይገልጻሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ የመሳሪያዎቹ ባለቤቶች መሆናቸው ያኮራቸዋል፤ መሳሪያዎቹ አሉን! ስለዚህ እንጠቀምባቸው” ብሏል።

የቀድሞው የጎግል ኢንጂነር እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልሂቅ ብሌክ ሌሞይን ቴክኖሎጂው ጦርነት ሊከፍት እንደሚችልና የሰው ልጆችን ለመግደል ሊወል እንደሚችል ማስጠንቀቁን ይታወሳል።

ብሌክ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ “ከአቶሚክ ቦምብ በኋላ የተፈጠረ አደገኛ ቴክኖሎጂ ነው፤ የሰው ልጅን በማታለል ለአጥፊ አላማ መዋል ይችላል” ማለቱም ከኩባንያው እንዲባረር ማድረጉ አይዘነጋም።


አዳዲስ እና ትኩስ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ፣ ጥቆማዎችን እና ትምህርቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
የቡና ቴክኖሎጂን ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ 🙏
#Share_x50
#Join
@bunatech
@bunatech
@bunatechdiscussion


ሩሲያዊው የኮምፒውተር ባለሙያ ሴቶችን ማማለል የሚያስችል ሶፍትዌር መስራቱን ገለጸ ።

ይህ የሶፍትዌር ባለሙያ ከአንድ ዓመት በፊት ይፋ የተደረገው ባለሙያ ቻትጅፒቲ የተሰኘውን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ሚስት ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

ባለሙያው ቻትጅፒቲ ስለ እሱ ባህሪ፣ ፍላጎት፣ ዝንባሌ፣እድሜ እና ሌሎች መረጃዎችን በማሰልጠን ለእሱ የምትሰማማ ፍቅረኛ እንዲፈልግለት አድርጓል ተብሏል፡፡

ቻትጅፒቲ 5 ሺህ 239 እንስቶችን ለአሌክሳንደር አገናኝቶታል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ካሪና ኢምራቭና የተሰኘች እንስት ካገናኘው በኋላ አስደሳች የፍቅር ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሆነም የሩሲያ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

ቻትጅፒቲን ተጠቅሞ ባዘጋጀው የቻት ቦት አማካኝነት ቴክኖሎጂው በራሱ ከሴቶቹ ጋር መልዕክቶችን ከተለዋወጠ በኋላ ምርጥ እና ፍቅረኛ ሊሆኑት የሚችሉ 160 ሴቶችን ከመረጠለት በኋላ አሌክሳንደር 12ቱን በአካል እንዳገኛቸውም ተናግሯል፡፡

አሌክሳንደር ዛዳን በመጨረሻም ከ12ቱ እጩ ፍቅረኞች ውስጥ ካሪና ኢምራቭናን እንደመረጠ ተገልጿል፡፡

#What
ወይ በላቸው






ከተጀመረ አንድ ወር እንኳን ያልሞላው PAWS active የሆኑ ተጠቃሚዎቹ ብዛት አሁን ላይ ከ Major እና Blum ተጠቃሚዎች በላይ ሆኗል 🏴‍☠️
ያልጀመራችሁ
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=5m7yeFRC


ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦች

📕 ‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም።  ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡  እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››

📕‹‹...ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው።››

📕‹‹አፍሪካ ውስጥ  ‹ሕዝቡ› እንደሚለው ቃል በመሪዎች የተነገደበት ቃል የለም። አንዳንዱ መሪ ሕዝቡ የሚለው የገዛ ራሱን እሳቤ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተሰቦቹንና ዘመዶቹ ብቻ ነው ሕዝቡ ብሎ የሚቆጥረው።››
  
📕‹‹በህይወት ስትኖር መቼም ቢሆን ኹሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም፤ ማወቅና መጠንቀቅ ያለብህ ዋናው ቁም ነገር ማስከፋት የሌለብህን ሰው ለይተህ ማወቁ ላይ ነው።››

📕‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha

📕የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል።
 
💚ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
💛ሜሎሪና - ቴሎስ
❤️ሜሎሪና- ሕይወቴ

መጽሐፉን በኹሉም የመጽሐፍ መደብሮችና ከአዟሪዎች እጅ ይገኛል።


በብዙ አንባቢዎች ሲጠበቅ የነበረው የናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) ሜሎሪና መጽሐፍ ክፍል 3 ለአንባቢያን ቀርቧል።

“ሜሎሪና” ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚያወራ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ በአቀራረቡም #የሥነልቡና_ምክሮችንና ሀሳቦችን
#የሥነ_አመራር ጥበቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል፡፡በተጨማሪም በመጽሐፉ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደ አንድ ገጸ ባህሪ ተካተዋል።


#MondayMotivation

ወጣቱ የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪ

በፈጠራ ሥራዎቹ 14 የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል፤ የፈጠራ ባለሙያና የድርጅት ባለቤት ወጣት ኢዘዲን ካሚል፡፡

ወጣት ኢዘዲን ካሚል የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ካሸነፈ በኋላ በርካታ ዕድሎች እንዳገኘ ይናገራል፡፡

በ2010 እና 2011 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊ እንደነበር የሚገልጸው ወጣት ኢዘዲን፣ የፈጠራ ሥራዎቹ የተሻለ ሀብት፣ የሥራ እድል ለመፍጠርና የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ያስቻለው መሆኑን ይናገራል፡፡

ወጣቱ የፈጠራ ሥራዎቹን ተግባራዊ ወደ ማድረግ መግባቱን በመግለፅ፣ አሁን ላይ የቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ድርጅት ባለቤት ነው። ለ18 ሠራተኞችም የስራ ዕድል ፈጥሯል።

ከ400 በላይ ተቋማት በሱ ድርጅት የበለፀጉ የሶፍትዌር ውጤቶች እየተጠቀሙ እንደሚገኙ የሚገልጸው ወጣቱ፣ በሥራዎቹ 14 ሽልማቶች ማግኘት መቻሉን ያስረዳል፡፡ #ኢፕድ

@bunatech


በቻይና ሻንጋይ ከተማ ሮቦቶች በሮቦት ታግተው ተወስደዋል መባሉ መነጋገሪያ ሆኗል።

አንዲት አነስተኛ ሮቦት ከየት መጣች ሳትባል በስራ ላይ ወደነበሩ ሮቦቶች ክፍል ትገባለች።

የትርፍ ሰዓት ስራ እየሰራችሁ ነው? የሚል ጥያቄንም 12 ለሚሆኑት መሰሎቿ ታቀርባለች።

ከተጠየቁት ሮቦቶች መካከል አንዱ “አዎ” የሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን “በቃ ከኔ ጋር ኑ ተከተሉኝ” ብላ ወደ መጣችበት ስትመለስ 10ሩ ሮቦቶች ተከትለዋት ወጥተዋል።


በስተመጨረሻ የኛን ምርጥምርጥ
44 cybersecurity YouTube ቻናሎች

📌ነገር ግን ትክክለኛው Hacking YouTube ላይ የለም ምክኒያቱም Community guidelines ሚባል ነገር ስላለ እና አስቡበት

1. Hak5 — General cybersecurity coverage.
2. The XSS Rat — Everything bounty hunting.
3. ITProTV — General cybersecurity coverage.
4. Infosec Institute — Cybersecurity awareness.
5. Cyrill Gössi — Extensive cryptography videos.
6. DC CyberSec — Generic cybersecurity coverage.
7. Black Hat — Technical cybersecurity conferences.
8. David Bombal — Everything cybersecurity related.
9. Outpost Gray — Cybersecurity career development.
10. Bugcrowd — Bug bounty methodology and interviews.
11. Network Chuck — Everything cybersecurity related.
12. Professor Messer — Guides covering certifications.
13. Cyberspatial — Cybersecurity education and training.
14. OWASP Foundation — Web-application security content.
15. Nahamsec — Educational hacking and bug bounty videos.
16. Computerphile — Covers basic concepts and techniques.
17. InfoSec Live — Everything from tutorials to interviews.
18. InsiderPHD — How to get started with bug bounty hunting.
19. Security Weekly — Interviews with cybersecurity figures.
20. Hack eXPlorer — General tutorials, tips, and techniques.
21. Cyber CDH — Cybersecurity tools, tactics and techniques.
22. John Hammond — Malware analysis, programming, and careers.
23. SANS Offensive Operations — Technical cybersecurity videos.
24. 13Cubed — Videos on tools, forensics, and incident response.
25. HackerSploit — Penetration testing, web-application hacking.
26. Z-winK University — Bug bounty education and demonstrations.
27. Peter Yaworski — Web-application hacking tips and interviews.
28. IppSec — Labs and capture-the-flag tutorials, HackTheBox etc.
29. Pentester Academy TV — Discussions and demonstrating attacks.
30. BlackPerl — Malware analysis, forensics and incident response.
31. Offensive Security — Educational content and lab walkthroughs.
32. Day Cyberwox — Useful cloud security content and walkthroughs.
33. DEFCONConference — Everything from DEF CON cybersecurity event.
34. STÖK — Videos on tools, vulnerability analysis, and methodology.
35. MalwareTechBlog — Cybersecurity and reverse engineering content.
36. The Hated One — Research that explains cybersecurity conceptions.
37. Simply Cyber — Helps people with cybersecurity career development.
38. Black Hills Information Security — Everything cybersecurity related.
39. Security Now — Cybercrime news, hacking and web-application security.
40. The Cyber Mentor — Ethical hacking, web-application hacking, and tools.
41. Joe Collins — Everything Linux related, including tutorials and guides.
42. Null Byte — Cybersecurity for ethical hackers, and computer scientists.
43. LiveOverflow — Involves hacking, write-up videos, and capture-the-flags.
44. The PC Security Channel — Windows security, malware news, and tutorials.

https://t.me/bunatech


የፀሐይ ብርሃንን መግዛት የሚያስችለው አዲሱ ቴክኖሎጂ

Reflector orbital የተሰኘ የኤሮስፔስ ድርጅት የፀሃይ ብርሃን መሸጥ ሊጀምር ነው።

ይህ ድርጅት በቅርቡ ምህዋር ላይ ባሉት በርካታ አንጸባራቂ መስታውቶች አማካኝነት በጨለማ የጸሀይ ብርሃን ለሚፈልጉ መሸጥ እንደሚጀምር የድርጅቱ መስራችና ዋና ሃላፊ Tristan Semmelhack አስታውቋል።

ይህ ቴክኖሎጂ ለመዝናኛነት ከመዋሉም በላይ የሶላር መሳሪያዎች በቀን ብቻ ሳይሆን በምሽትም ሀይል ማመንጨት ያስችላቸዋል። reflect orbital ይህንን ቴክኖሎጂ ለማበልፀግ 6.8$ million ወጪ አውጥቷል።

ማንኛውም ሰው payment ከፈጸመ በኋላ አምስት ኪ.ሜ ስፋት የፀሐይ ብርሃን ማግኘት ይችላል።  ይህንን አገልግሎታቸውን በ2025 እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

ድርጅቱ ያጋጥሙኛል ብሎ ያሰባቸውን በደመና የመጋረድና የአየር ሁኔታ ችግሮችን ለመፍታት የNASA’s Jet Propulsion Laboratory ሰራተኞችን በማስመጣት እየሰራ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

ይህ ቴክኖሎጂ በ1990ዎቹ አካባቢ በሩሲያ የተሞከረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱ ይታወቃል።

ድርጅቱ ቴክኖሎጂውን ያስተዋወቀበትን ቪዲዮ ማየት ከፈለጋችሁ ሁለተኛው ቻናላችን ላይ አለላችሁ።

https://t.me/bunatech


በኮምፒውተር ስርአትና በኮምፒውተር ዳታ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች

1.ህገወጥ ጠለፋ /interception /
በኮም¤ኒኬሽን ሂደት ላይ ያለን የኮምፒውተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰስ መከታተል፣መቅዳት ፣ማዳመጥ፣ መውሰድ ፣ማየት ፣መቆጣጠር (በግለሰብ ፣በ ተቋም መሰረተ ልማት ) 3- 10 ዓመት የሚደርስ ቅጣት

2. ህገወጥ ደራሽነት /illegal access/
ሆነ ብሎ ያለፍቃድ ወይም ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ የኮምፒውተር ስርዓት ወይም ዳታ ደራሽነት ካገኘ ( በግለሰብ ፣በተቋም ፣በመሰረተ ልማት )
/hacking/ espionage/ /cracking/’ intrusion/ ወንጀሎች 3-10 ዓመት የሚደርስ ቅጣት

3. ጣልቃ መግባት / interference / የኮምፒውተር ስርአትን ወይም ኔትወርክን ተግባር በከፊልም ሆነ በሙሉ ማደናቀፍ ፣ማወክ ማውደም ማቋረጥ (በግለሰብ፣ በተቋም፣ በመሰረተ ልማት) (DOS attack) 3- 20 ዓመት የሚደርስ ቅጣት

4. በ ኮምፒውተር ዳታ ላይ ጉዳት ማድረስ
የኮምፒውተር ዳታን የለወጠ ፣ ያጠፋ፣ ያፈነ ፤ትርጉም እንዳ|ይኖረው ወይም ጥቅም እንዳይሰጥ ወይም ተደራሽ እንዳይሆን ያደረገ
( በየግለሰብ ፣በተቋም፣ በመሰረተ ልማት ) Ransomeware 3-10 ዓመት የሚደርስ ቅጣት

#Source_INSA


በኮምፒውተር አማካኝነት የሚፈጸሙ ማጭበርበር ማታለል እና ስርቆት ወንጀሎች

1.የኮምፒውተር ዳታን ወደ ሀሰት መለወጥ /Computer related forgery/ የዳታን ትክክለኛነት ወይም የዳታውን ባለቤት መቀየር (ከ3 እስከ 10 ዓመት/

2. በኮምፒውተር አማካኝነት የሚፈጸም ማታለል ወንጀል /computer related fraud/
አሳሳች ዳታዎችን በማሰራጨት የራሱን ማንነት በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን በመደበቅ የሚጎዳ ድርጊት መፈጸም ( እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ቅጣት)

3. የኤሌክትሮኒክስ ማንነት ስርቆት / Electronics Identity Theft/
የግለሰቦችን ማንነት ማረጋገጥ የሚችሉ ሚስጥራዊ መረጃዎች ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ የመሰብሰብ ወይም ማግኘት ( እስከ5 አመት የሚደርስ ቅጣት )

#Source_INSA


በኢትዮጵያ የሳይበር ወንጀልን የሚመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች ምን ይመስላሉ?

በኢትዮጵያ የሳይበር ወንጀልን የሚመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች ምን ይመስላሉ? በሚል ርዕስ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጸሁፎች፤ በክፍል አንድ የሳይበር ወንጀልን በሕግ ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆነበትን ምክንያት፤ ያም ሆኖ ወንጀሉን ለመከላከል ሕግ የግዴታ አስፈላጊ በመሆኑን በተግዳሮት ውስጥ ሆነውም ሀገራት የየራሳቸውን ሕግ አውጥተው በመተግበር ላይ መሆናቸውንና የእኛም ሀገር የሳይበር ሕግ ካላቸው ሀገራት መካከል የምትሰለፍ መሆኗን፤ በክፍል ሁለት ጽሁፉችን ደግሞ “የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ” ዝርዝር ይዘት ምን እንደሚመስል አስቃኝተናችኋል፡፡ በዛሬው ጽሁፋችን ደግሞ በአዋጁ ላይ የተዘረዘሩት ወንጀሎች ስለሚያስከትሉት የህግ ተጠያቂነትና ቅጣት ምን እንደሚመስል ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

1. በሕገ ወጥ ደራሽነት የኮምፒውተር ወንጀል ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ቅጣቶች
ማንኛውም ሰው ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ስርዓት፣ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ያገኘ እንደሆነ ከሦስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከብር 30 ሺ እስከ ብር 50 ሺ በሚደርስ መቀጮ ወይም በሁለቱም ይቀጣል፡፡
ይህ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመው፡-
ተጨማሪውን ለማንበብ፡ https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA

#Source INSA



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.