ኤፌሶን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።
⁵ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።
⁶ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።
⁷ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
⁸ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።
⁹ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤
¹⁰ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።
¹¹ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።
¹² ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።
Ephesians 1 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ According as he hath chosen us in him before the foundation of the world, that we should be holy and without blame before him in love:
⁵ Having predestinated us unto the adoption of children by Jesus Christ to himself, according to the good pleasure of his will,
⁶ To the praise of the glory of his grace, wherein he hath made us accepted in the beloved.
⁷ In whom we have redemption through his blood, the forgiveness of sins, according to the riches of his grace;
⁸ Wherein he hath abounded toward us in all wisdom and prudence;
⁹ Having made known unto us the mystery of his will, according to his good pleasure which he hath purposed in himself:
¹⁰ That in the dispensation of the fulness of times he might gather together in one all things in Christ, both which are in heaven, and which are on earth; even in him:
¹¹ In whom also we have obtained an inheritance, being predestinated according to the purpose of him who worketh all things after the counsel of his own will:
¹² That we should be to the praise of his glory, who first trusted in Christ.
@Christian_tweet