Commercial Bank of Ethiopia - Official


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1,940 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ደንበኞች ምን ይጠይቃሉ?


ይመልሱ፤ ይሸለሙ!
********

የባንካችንን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በመቀላቀል የገና እና ጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀነው የጥያቄና መልስ ውድድር ይሳተፉ፤ ይሸለሙ!
**********
• Telegram፡- https://t.me/combankethofficial
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Facebook Afan Oromo፡- https://www.facebook.com/BaankiiDaldalaItiyoophiyaa
• Facebook Tigrigna:- https://web.facebook.com/cbetigregna/
• Tiktok፡- https://www.tiktok.com/@combankethiopia
*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!


#ዜና_ተደራሽነትን_ማሳደግ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ተደራሽነት ለማስፋት እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡
• ባንካችን በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ አል ሀምዱ በሚል ስያሜ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ ለከተማው ሶስተኛውን የሲቢኢ ኑር ቅርንጫፍ በቅርቡ አስመርቆ ሥራ አስጀምሯል፡፡
https://youtu.be/nbLiDxT6PhE


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በካርድዎ ይሸምቱ!
*******

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (ፖስ) በመጠቀም
በካርድዎ በቀን እስከ 500 ሺ ብር ግብይት መፈፀም ይችላሉ፡፡
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #digitalbanking #pos #banking #ethiopia


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Saturday, 21 December 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


ውድ ደንበኞቻችን፡
****

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት ሲያገኙ፣ እንዲሁም የኤቲኤም (ATM)፣ የፖስ (POS) እና የሲቢኢ ብር (CBE Birr) አገልግሎቶችን ከተጠቀሙ በኋላ ከፅሁፍ ማረጋገጫ መልእክት (SMS) ጋር የሚደርስዎትን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም ባንካችን በሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ላይ አስተያየት ቢሰጡን ለቀጣይ መሻሻል ይረዳናል፡፡

ስለትብብርዎ በቅድሚያ እናመሰግናለን!

ማሳሰቢያ፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስልክ በሚላክ መጠይቅ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎንና የሚስጢር ቁጥርዎን አይጠይቅም፡፡
********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፋስት ፔይ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
• የፋስት ፔይ ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል፡፡
******************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ለመላክ አገልግሎት ከሚሰጥባቸው አማራጮች መካከል አንዱ የሆነው የፋስት ፔይ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች የበለፀገው ይህ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ ከውጭ ሀገራት በማንኛውም ቦታ እና ሰዓት በፍጥነት በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺ ዶላር ወደ ተጠቃሚ ሂሳብ በነፃ መላክ የሚያስችል እንደሆነ የፋስት ፔይ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ተስፋዬ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመርቻንት እና ኤጀንት ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ብሌን ኃ/ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞች ቀላል እና ፈጣን ዓለም አቀፍ የገንዘብ መላኪያ አማራጭ መንገዶችን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የፋስት ፔይ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል መለስ በበኩላቸው ከግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር መሥራታቸው ባንኩ ካለው ረዥም ልምድ እና የደንበኛ ብዛት አንፃር ስኬታማ ሥራ መሥራት እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡:


በጭማሪ ይንበሽበሹ!
*******

ከባህር ማዶ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ ከባንካችን ሲቀበሉ፣ በኢትዮ ዳይሬክት (#EthioDirect) እና ካሽ ጎ (#CashGo) ገንዘብ ሲላክልዎ በጭማሪ ይንበሸበሻሉ!
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #gift #EthioDirect #CashGo

13k 1 3 13 38

Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Friday, 20 December 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


የሐራጅ ማስታወቂያ


በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው ከሚገኙ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
***************

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች እና የነቀምቴ ዲስትሪክት አመራሮች በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን አወያይተዋል ።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ደንበኞች ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች፣ የብድር አሠጣጥ፣ አዳዲስ ቅርንጫፎች በሚከፈቱበት ሁኔታ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ናስር ሱልጣን፣ የነቀምቴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ መሠረት አለማየሁ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሸሪዓ መማክርት ኮሚቴ አባል ዶር. መሀመድ ዘይን ለጥያቄዎቹ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ባንኩ የሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ መርሆዎችን የተከተለ ስለመሆኑ በማብራሪያ ወቅት የተገለፀ ሲሆን፣ የብድር አገልግሎትን ጨምሮ ደንበኞች ያነሷቸው ሌሎች ጉዳዮች በባንኩ አሠራር መሠረት ምላሽ እንደሚያገኙ ተብራርቷል፡፡

በወርቅ ማዕድን በበለፀገው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ህብረተሰቡ የባንክ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ ባንኩ የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም እንዲሁ በምላሹ ተነስቷል፡፡

የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች በቅርንጫፎች እና በደንበኞች የሥራ ቦታ በመገኘት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ በቀጣይ መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እንዴት ሲቢኢ ብር ፕላስን ተጠቅመው ከባንክ ሂሳብዎ ነዳጅ ይቀዳሉ?
#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business #fuel #payment


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Thursday, 19 December 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ አጭበርባሪዎች በዝተዋል፤ ይጠንቀቁ!
**************

አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመርን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው የመረጃና ገንዘብ ምዝበራ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ጥቂቶቹን እና መከላከያ መንገዶችን እንጠቁማችሁ፡፡

1. ፊሺንግ (Phishing)

በዚህ የሶሻል ምህንድስና ጥቃት አጭበርባሪዎች ማኅበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በተለያዩ ዲጂታል የመልእክት መለዋወጫ መንገዶች ሀሰተኛ መልእክቶችን በመላክ ተጠቃሚዎች የግል እና ሌሎች እንደ ሂሳብ፣ የይለፍ ቃል የመሳሰሉ መረጃዎቻቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ፣ እንዲሁም አደገኛ ሊንኮችን እንዲከፍቱ እና ሶፍትዌሮችን እንዲጭኑ ያደርጋሉ፡፡

2. የኢንቨስትመንት ማጭበርበሮች (Investment Scams):

የውሸት በሆኑ ወይም በሌሉ ምርቶች ወይም ንግዶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያበረታቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል። ብዙዎችም የምዝበራ ሰለባ ሆነዋል፡፡

3. ነፃ የሙከራ አገልግሎቶች (Free Trial Products):

በሀሰተኛ የምርቶች ነጻ ሙከራ (Free-trial) ማስታወቂያ ሰዎችን በማታለል ለነጻ የምርት ሙከራው እንዲመዘገቡና የክፍያ ካርድ መረጃቸውን እንዲያስገቡ የማድረግ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው፡፡ ተጠቂው ከሱ እውቅና ውጪ ውል ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ክፍያ ያለባለቤቱ እውቅና ተቀናሽ ይሆናል።

4. የኦንላይን ግብይት ማጭበርበሮች

በኦንላይን ግብይት የተለያዩ ምርቶችን በቅናሽ እንሸጣለን በሚል የምዝበራ ተግባር ላይ የተሠማሩ አጭበርባሪዎች አሉና ይጠንቀቁ፡፡

5. ክሊክቤይት (Clickbait)፡

ይህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጠቃሚዎችን ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮችን የያዙ ይዘቶችን በማውጣት ተጠቃሚዎች ይበልጥ ለማወቅ ሊንኩን እንዲጫኑ የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይህን ዘዴ አጭበርባሪዎች ሲጠቀሙበት ተጠቂው ጥቃት አድራሾቹ ወደ ሚመሩት ማስፈንጠሪያ በሚገባበት ጊዜ የግል መረጃውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።

6. የውሸት ጓደኛ ጥያቄዎች (Fake Friend Requests)፡

አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመክፈት ወይም የሌሎችን አካውንቶች በመጥለፍ ወደተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጓደኝነት ጥያቄ ይልካሉ። እነዚህን ጥያቄዎች መቀበል የእርሶን እና የጓደኞቻችሁን መለያ እንዲጠለፍ እና የግል መረጃ እንዲያፈተልክ ያደርጋል።

7. የሥራ እድል ማጭበርበሮች

ሀሰተኛ የስራ እድል ማስታወቂያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት ይተዋወቃሉ። ገቢዎን ያሳድጉ ወይም ከቤት ሆነው ሥራ ይስሩ በማለት አጓጊ ጥቅማጥቅሞችን በመንገር ተጠቃሚው ቶሎ ውሳኔ እንዲወስን (sense of urgency) በማድርግ ማጭበርበሩን ይፈጽማሉ።
እነዚህ አጭበርባሪዎች የተጠቃሚውን መረጃ የግል እና ሊሎች መረጃዎች ይወስዳሉ ወይም ለሥልጠና ወይም ለሌላ ጉዳይ በቅድሚያ ክፍያ ይጠይቃሉ።

8. ስጦታ

በራሳቸውም ሆነ የሌሎችን ስምና ዝና በመጠቀም ሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆችን በመክፈት ተከታይ ስትሆኑ፣ ተከታይ ስታስገቡ፣ ልጥፎችን ስታጋሩ፣ አስተያየት ስትሰጡ፣ ስትወዱ ስጦታ እንሰጣለን በሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ያጭበረብራሉ፡፡ እነዚህ አጭበርባሪዎች የተከታዮችን ግላዊ መረጃ ለመውሰድ መልካም አጋጣሚ ይሆንላቸዋል፡፡


እንዴት ከአጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ?

• ከማያውቁት ግለሰብ የሚደርስዎትን የማኅበራዊ ሚዲያ እንወዳጅ ጥያቄ አይቀበሉ፡፡
• የቅናሽ ማስታወቂያዎችን በጥርጣሬ ይመልከቱ፤
• በኦንላይን ብቻ ለተዋወቁት ግለሰብ ገንዘብ አይላኩ፡፡
• በማኅበራዊ ሚዲያ የግል መረጃዎን አይስጡ።
• የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን ህጋዊነት ሳያረጋግጡ ምንም አይነት እርምጃ አይውሰዱ፡፡
• ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ ይፈትሹ።
• ከማያውቁት አካል በሚደርስዎት አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ኢሜይል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት የሚያገኙትን ማስፈንጠሪያ (link) አይክፈቱ፡፡
• ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይከተሉ፡፡

17.5k 1 47 18 111

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምስተኛ ድሉን አስመዘገበ፡፡
**********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀምበርቾን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 9፡00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ሴናፍ ዋቁማ አራቱንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎሎች አስቆጥራለች፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች አምስቱን ማሸነፍ ሲችል፣ በአንዱ አቻ ተለያይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከታታይ ባስመዘገባቸው ድሎች ቀሪ አራት ጨዋታ እየቀረው ከመሪዎቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ችሏል፡፡


ማጂክ ፔይ!
አጠገብዎ ላለ ሰው በቀላሉ ገንዘብ መላክ ይችላሉ፡፡
ሲቢኢ ብር ፕላስ (CBEBirr Plus)

**

በማጂክ ፔይ አጠግብዎ ላለ ሰው ገንዘብ ለመላክ፡

• የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያዎ ላይ የሚገኘውን ማጂክ ፔይ (Magic Pay) ከፍተው ‘ላክ’ ‘Send’ የሚለውን ይምረጡ፣
• የገንዘብ መጠን አስገብተው ‘ማጂክ ኮድ ይፍጠሩ’ ‘Generate Magic Code’ የሚለውን ይጫኑና የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ፣ የQR ኮድ ይመጣልዎታል፣
• ገንዘብ ተቀባዩ የራሱ ስልክ ላይ ወደ ማጂክ ፔይ በመግባት ‘ተቀበል’ ‘Receive’ የሚለውን መርጦ ላኪው ስልክ ላይ ያለውን የQR ኮድ ስካን ሲያደርግ ገንዘቡ ይደርሰዋል፡፡ አለቀ፡፡
***
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Wednesday, 18 December 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia



18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.