Postlar filtri




"ዓድዋ - ሕያው ተጋድሎ፣ ሕያው ድል" መልቲ ሚዲያ ትርዒት በተመልካች ጥያቄ በድጋሚ ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት በኢቢሲ ይቀርባል
*************************
"ዓድዋ - ሕያው ተጋድሎ፣ ሕያው ድል" መልቲ ሚዲያ ትርዒት በተመልካቾች ጥያቄ መሰረት፤ ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት በድጋሚ በኢቲቪ ዜና ቻናል፣ በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል፣ በኢትዮጵያ ራዲዮ፣ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1፣ በEBC DOTSTREAM ሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ይተላለፋል። እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ።


ማስታወቂያ
****
ሬስ ማይክሮ ፋይናንስ እና ሁድ ሁድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመተባበር የተመቻቸ ብድር


የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል
****************

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጅ እና መመሪያ መሠረት መንግስታዊ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡


ዓድዋ የፅናት ተምሳሌት እና የአብሮነት ማሳያ ነው - አቶ አሻድሊ ሐሰን
***************

የዓድዋ ድል የፅናት ተምሳሌት እና የአብሮነት ማሳያ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ተናግረዋል፡፡

ድሉ የባርነት ቀንበር ተጭኗቸው ለነበሩ አፍሪካውያን እና በመላው ዓለም ለሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ጎህ መቅደዱንም አውስተዋል፡፡

ዓድዋ አፍሪካውያን ለነፃነታቸው በጽናት እንዲታገሉ የወኔ ስንቅ ሆኖ ከማገልገሉም ባሻገር የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ እንዲጎለብት ማገዙን ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ የአሁኑ ትውልድ በተባበረ ክንድ ኢትዮጵያን ከድህነት በማላቀቅ የዓድዋን ድል መድገም እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በነስረዲን ሀሚድ


የዓድዋ ድል በዓል በባህር ዳር እና ደሴ ከተሞች ተከበረ
*************

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በባህር ዳር እና ደሴ ከተሞች ተከብሯል፡፡

በዓሉ በባህር ዳር ከተማ በግዮን አደባባይ በተለያዩ ትዕይንቶች መከበሩ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የዓድዋ ድል በዓል በደሴ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በፒያሳ አደባባይ ተከብሯል፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ፤ የዓድዋ ድል ቁልፍ ምስጢር ሀገርን ከውስጣዊ ልዩነቶች አብልጦ ማየት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከንቲባው ድሉ በቅኝ ግዛት ስር ለነበሩ አፍሪካውያን የነጻነት ብርሃን መፈንጠቁንም አመላክተዋል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ፣ ተስፋሁን ደስታ እና ራሄል ፍሬው


የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ
********************

የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አመራሮች እና አባላት የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላቱ ፤ ማዕከሉ የንግዱን ማህበረሰብ በንግድ ስርዓት ውስጥ በማስተሳሰር ከተቀረው ዓለም ጋር ያለው ተወዳዳሪነት እንዲጨምር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

አባላቱ ማዕከሉ ከሀገር አልፎ በዓለም ደረጃ ሀገር በቀል ምርቶችን ለማስተዋወቅ እና መዲናዋን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለማድረግ ትልቅ ሚና እንዳለውም መናገራቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡


የዓድዋ ድል ነፃነትን ለሚሹ ሁሉ የማይጠፋ የብርሃን ፀዳል ነው - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
*********************

“የዓድዋ ድል ነፃነትን ለሚሹ ሁሉ የማይጠፋ የብርሃን ፀዳል ነው” ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ተናግረዋል፡፡

ድሉ የቅኝ ግዛት እሳቤን ያንበረከከ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰብዓዊ ክብርን ያጎናጸፈ እና የኢትዮጵያውያንን ጅግንነት ለዓለም ያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለድሉ መገኘት መሰረት የሆነው የኢትዮጵያዊነት ሐሳብ እና ፍልስፍና በትውልዱ በጥልቀት ሊመረመር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዓድዋ የኢትዮጵያ ሴት አርበኞችን ብርቱ ተሳትፎ እና የፖለቲካ ብለሃት የገለጠ ድል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የዓድዋ ድል የአንድ ወቅት ብያኔ ሳይሆን ትናንትን የወሰነ፣ ዛሬን የገለጠ እና ነገን የተለመ ጠንካራ አስተሳሳሪ ሰንሰለት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመከበር ላይ ይገኛል።

መሐመድ ፊጣሞ



9 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.