❇️👉በአዲስ አበባ በመብራት ችግር ምክንያት ለፀጥታ ስጋት የሆኑ 174 የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና 197 የመንገድ ዳር አካባቢዎችን በመለየት የመፍትሄ ማስፈፀሚያ እቅድ ስለመዘጋጀቱ ተነግሯል።
❇️👉ይህን ያለው የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ የወንጀል ምጣኔ ከባለፈው አመት አንፃር 33 በመቶ ቅናሽ ቢያሳይም የምሽት ላይ ዝርፊያዎች ግን እየተበራከቱ መሆኑን አሳውቋል።
❇️👉ለዚህ ሲባል የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎትን ጨምሮ 5 አስፈፃሚ አካላት የተካተቱበት እቅድ ተዘጋጅቷል ያለው ቢሮው እነዚህ ለወንጀል ምቹ የሆኑ የውስጥ ለውስጥና የመንገድ ዳር አካባቢዎች መብራት እንዲያገኙ ይሰራል ነው ያለው።
❇️👉የመንገድ ዳር መብራት የተዘረጋላቸው ነገር ግን ብርሀን የሌላቸው የመንገድ ዳር መብራቶች በርካታ ናቸው ያለው ቢሮው ይህን ለማስተካከል እንደሚሰራና ህብረተሰቡም ግቢውና አካባቢው ላይ መብራት እንዲያኖር እንደሚደረግ ጠቁሟል።
❇️👉ኮልፌ ክፍለከተማ የማይሰሩ መብራቶች በብዛት ያሉበትና ወንጀልም የተበራከተበት ቀዳሚ ክፍለከተማ ነው ያለው ቢሮው ልደታምና ለሚ ኩራም እንዲሁም አራዳና ቦሌ ክፍለከተማም ይህ ስራ በዋነኝነት የሚተገበርባቸው 5 ክፍለ ከተሞች ይሆናሉ ብሏል።
❇️👉ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ናቸው። ለሚ ኩራ ከመንገድ ዳር መብራት ይልቅ የውስጥለውስጡ ይበዛል። አራዳና ቦሌም የቸወሰነ ችግር አለባቸው።
❇️👉ህብረተሰቡ ለአካባቢው የሚያበራቸው የደጅ አምፓሎች ስታንዳርድ እንደሚወጣላቸውና ከስታንዳርድ ውጪ የሆኑ የደጅ አምፓሎችን መጠቀም እንደሚከለከል የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሀይል አሳውቋል።
❇️👉በከተማዋ ባሉ 5246 ብሎኮች ውስጥ ወብራቶችን ወደደጅ የማውጣት ውይይት በ15 ቀናት ውስጥ ከህ ብረተሰቡ ጋር እንዲካሄድ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለክፍለከተሞቹ ትእዛዝ ሰጥቷል።
መረጃውን ያደረሰን ሪፖርተራችን አቤል አበበ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews