የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የእኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፡_
🕊🕊በትግራይ ክልል በህወሃት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት ያሳሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዳግም ጦርነትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
❇️▶️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ግብር ከፋዮች የጣራና ግርግዳ ግብር እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓመተ ምህረት ድረስ ከፍለው እንዲያጠናቅቁ ሲል ጥሪውን አስተላለፈ፡፡
🇺🇸👉በኢትዮጵያ የተቋረጠው የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ድጋፍ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኤች አይቪ ኤድስ ህሙማን የድጋፍ አገልግሎት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ማድርጉን የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ፡፡
💠🉐የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት ወይም ዩኤስኤይድ ድጋፍ በአለም ደረጃ መቋረጥ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበራት ስራቸውን የሚያስተጓጉል አደጋ ነው እናም ያሳስበኛል ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ገለጸ፡፡
🕊🏳️የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት ከመገናኛ ብዙሀንና ከዘርፉ ባለሙያዎች ያሰባሰባቸውን የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።
📚📚የአማራ ክልል በገጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጭ መሆናቸው ሲገለጽ በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ መኾናቸውንም ተጠቆመ።
ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"
መልካም ቀን!
ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews