Ethiopian Educational Channel


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Ta’lim


እንኳን ደና መጣችሁ
Channel created by @BA1227
በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኙት
1. ትምህርታዊ መረጃ መስጠት
2.የሳይኮሎጂ አስተማሪ ምክሮችንና አነቃቂ ንግግሮች
3.መፃህፍቶች በpdf እና የእንግሊዝኛ ንግግር ይለቀቃሉ!!!
በዚህ ቻናል ሀይማኖታዊ እና ፓለቲካ ነክ አይለቀቅበትም !
የቴሌግራሙ ቻናል ሊንክ:👉https://t.me/EEC1227

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ለ ተማሪዎች መልካም ዜና

ጥያቄዎችን የምታገኙበትን ምርጥ ቻናሎች ልጋብዛቹ ትወዳላቹ


የመምህራንና የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!
===================-==
😁1ኛ= ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡
😁2ኛ= የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡
😁3ኛ= ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡
😁4ኛ= የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡
😁5= የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::
😁6ኛ= በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡
😁7ኛ= በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡
😁8ኛ= በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ፡፡
😁9ኛ= የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው
፡፡
😁10ኛ= ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
፫= የጡረታ መለያ ቁጥር
፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡


አዲሱ የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ!
====================


🎯 last section



111. Flower: The reproductive structure of flowering plants.
112. Pollination: Transfer of pollen to the female part of a flower.
113. Fruit: Mature ovary of a flowering plant containing seeds.
114. Seed: A plant embryo encased in a protective coating.
115. Germination: The process of a seed sprouting.
116. Root: The underground part of a plant.
117. Stem: The main body or stalk of a plant.
118. Leaf: The part of the plant where photosynthesis usually occurs.
119. Photosynthetic Pigment: A molecule that absorbs light for photosynthesis.
120. Chlorophyll: The main photosynthetic pigment.
121. Tropism: A plant's growth response to a stimulus.
122. Vertebrate: An animal with a backbone.
123. Invertebrate: An animal without a backbone.
124. Nervous System: The system of nerves that controls and coordinates bodily functions.
125. Neuron: A nerve cell.
126. Brain: The central control organ of the nervous system.
127. Spinal Cord: The part of the nervous system that connects the brain to the rest of the body.
128. Endocrine System: The system of glands that produce hormones.
129. Hormone: A chemical messenger produced by the endocrine system.
130. Circulatory System: The system that transports blood and nutrients.
131. Heart: The muscular organ that pumps blood.
132. Blood Vessel: A tube that carries blood.
133. Red Blood Cell: A blood cell that carries oxygen.
134. White Blood Cell: A blood cell involved in immune defense.
135. Respiratory System: The system responsible for gas exchange (oxygen and carbon dioxide).
136. Lung: The main organ of the respiratory system.
137. Digestive System: The system responsible for breaking down food.
138. Stomach: An organ in the digestive system where food is broken down.
139. Intestine: Part of the digestive system where nutrients are absorbed.
140. Excretory System: The system that removes waste from the body.
141. Kidney: The organ in the excretory system that filters blood.
142. Muscular System: The system of muscles that allows for movement.
143. Skeletal System: The system of bones that supports the body.
144. Immune System: The system that protects the body from pathogens.
145. Antibody: A protein produced by the immune system that binds to pathogens.
146. Antigen: A substance that triggers an immune response.
147. Pathogen: A disease-causing agent.
148. Taxonomy: The science of classifying organisms.
149. Kingdom: The highest level of taxonomic classification.
150. Phylum: A major grouping within a kingdom.
151. Class: A major grouping within a phylum.
152. Order: A major grouping within a class.
153. Family: A major grouping within an order.
154. Genus: A grouping of closely related species.
155. Scientific Name: The two-part name of a species (genus + species).
156. pH: A measure of acidity or alkalinity.
157. Buffer: A substance that resists changes in pH.
158. Isotope: Atoms of the same element with different numbers of neutrons.
159. Compound: A substance made of two or more different elements.
160. Element: A pure substance made of only one type of atom.
161. Molecule: Two or more atoms held together by chemical bonds.
162. Solvent: A substance that dissolves another substance.
163. Solute: A substance that is dissolved in a solvent.
164. Solution: A mixture of a solute dissolved in a solvent.
165. Control Group: A group in an experiment that does not receive the treatment.
166. Experimental Group: A group in an experiment that receives the treatment.
167. Independent Variable: The variable that is manipulated by the experimenter.
168. Dependent Variable: The variable that is measured in response to the independent variable.

        https://t.me/EEC1227


⚠️Warning!🔔 ሰዎች መከተልህን አቁም!

ጊዜህ በጣም የተገደበ እና አጭር ነው።ስለዚህ, የሌሎች ሰዎችን መርህ, የሌሎች ሰዎችን ህይወት እየኖርክ መባከንህን አቁም! በሌሎች ሰዎች አዕምሮ ከመኖር ወጥመድ ፈልቅቀህ ውጣ።

የሌሎችን ተራ ጩኸትና ጋጋታ ውስጥህ ያለውን ድምፅ እና እምነት በልጦ እንዲቆጣጠርህ
አትፍቀድ! ዋናውና ወሳኙ ነጥብ ደግሞ
''ልብህንና ምኞትህን የመከተል ድፍረት
ይኑርህ''


ኤርድሮፕ የምትሰሩ ልጆች
Paws ተዘጋ እንዴ ብላቹ የምጠይቁኝ Paws ከቴሌግራም Ban ስለተደረገ የነበረውን ሙሉ መረጃ ወይም Data እንደያዘ ቀጥታ ወደ Web ተጠቃሏል።
👉ከዚ በኋላ Paws ን የምታገኙት በብሮዘር ይሆናል ማለት ነው።
👉እባክህ Paws አታስጨንቃቸው ቶሎ ሊስት ሁንና ገላግላቸው...

ወደ Paws ለመግባት ሊንኩን ተጠቀሙ
https://paws.community




🙏🎉












ከ4-8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሂሳብ እና የእንግሊዝኛ ማጠናከሪያ ትምህርት በቴሌቪዥን መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመተባባር የማጠናከሪያ ትምህርቱን ከዛሬ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቴሌቪዥን ስርጭት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

የትምህርት ስርጭቱ በ AMN Plus ከሰኞ እስከ አርብ ከ11፡00 እስከ 2፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሑድ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በስርጭቱ የእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርቶች በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ትምህርቱ በ AMN Plus ቻናል እንዲሁም በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይተላለፋል ተብሏል።
#AAEB


#ለእርስዎ_ካልሆነ_ለሌሎች_ያጋሩ!
#Share


Natural or Social ናቹ?


ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ተገቢ ያልሆነ ይዘትን ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ሪፖርት እናድርግ፤

9. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

10. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ፤


ያለሁ ይመስለኛል ሰኞ
ከእሁድም የጀርባ ጓሮ

አርብ ላይ ሆኜ
ይርቀኛል ቅዳሜ

ቅዳሜም ደርሼ
ቀንሽንም ቀድሼ
እስክትደርስ ያንቺ ሰአት
ደቂቃዎች አመታት
ሰአታት ዘመናት
ሆነው ይገዝፋሉ
አልገፋ ይላሉ።

አግኝቼሽ በሰአት በቀኑ
ሰአታት ዘመናት
ደቂቃዎች አመታት እንዲሆኑ
ስጓተታቸው ይበጣጠሳሉ

አግኝቼሽ ሳልጠግብሽ

እነ እሁድ እነ ሰኞ እነ ማክሰኝት
እነ እሮብ እነ ሐሙሲት
እነ አርብ ይግተለተላሉ
ሳልጠራቸው ይገባሉ

በኔ እና ባንቺ መሐል
በናፍቆቴ ና በናፍቆትሽ መሐል
በቅዳሜ እና በቅዳሚት መሐል
ጠላትና ምቀኛ ይበዛል

ናፍቆቴስ ጠላቶቹን ሁሉ ረታልሽ
ይኸው ላንቺ
'
እስክትመጪ
'
ስድስት ቀኖች ገደለልሽ።


ጤና መረጃ ቻናልን መቀላቀል የጤንነት የሚጠቅሙ መረጃ ያግኙ👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Tenamereja1227


እንኳን ደስ አለን አላችሁ!
ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻናል ተከፈተ
⏰26/06/2017ዓ.ም ተከፈተ


🪐ዉጤታማ የአጠናን ዘዴዎች
          

⭐️ለነገ ዝግጁ ሁኑ!!!...ሁልጊዜም ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገ ለምትሰሩት ዕቅድ በማዉጣት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል!

⭐️በየቀኑ የተማራችሁትን ማንበብ  ፤ከስር ከስር ማጥናት!

⭐️የተመጠነ የንባብ ጊዜ መመደብ ፤መሠላቸት ሳይኖር በተነቃቃ መንፈስ ዉጤታማ ጥናት ለማካሄድ በቂ ሰዓት መጠቀም!

⭐️የምናጠናቸዉን የት/ት አይነቶች በጊዜ መከፋፈልና ቅደም ተከተል ማስያዝ! በጥናት ወቅት ከጨዋታና ማህበራዊ ሚዲያ ራስን ማራቅ!

⭐️ምቹ እና ትኩረት ለማድረግ የሚረዳ የጥናት ቦታ መምረጥ እንዲሁም ለጥናት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በቅድሚያ ማዘጋጀት!

⭐️ማስታወሻ በአጭር በአጭሩ መያዝ እና አይገባኝም ከሚል አስተሳሰብ መዉጣት!

⭐️በት/ቤት የጥናት ቡድን መፍጠር ፤ከትምህርት አቻ ጓደኞቻችን ጋር እዉቀትና ልምዶችን መጋራት!

⭐️በየጊዜው የሚሰጡ የክፍል ፈተና ጥያቄዎችን ደጋግሞ መስራትና ከስህተት መማር!

⭐️ስናነብ ግልጽ ያልሆኑልን ነጥቦች ካሉ ማስታወሻ ይዞ ከመምህራን ጋር መወያየት! ወይም ደግሞ ከገባቸው ልጆች መረዳት

⭐️መፅሐፍትን በpdf የማንበብ ልምዳቺን ይሁን! በፈለግንበተ ቦታና ሰዓት ማንበብ ያስችለናል፣

🌌  መልካም  የጥናት ጊዜ!.

 

📌Join and share 👇👇👇
        @eec1227

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.