የሂርና ከተማ የመካከለኛ መስመሮች መልሶ ግንባታ እየተከናወነ ነው
በሒርና ከተማ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የመካከለኛ መስመሮች የእንጨት ምሰሶዎች ሙሉ በሙሉ በኮንክሪት ምሶሶ የመቀየር ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በከተማዋ የሚገኙት የእንጨት ምሰሶዎች ከ40 ዓመት በላይ ያገለገሉና ያረጁ በመሆናቸው ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ ሲሆኑ ቆይቷል፡፡
በመልሶ ግንባታው ከጭሮ ሰብስቴሽን እስከ ሂርና የተዘረጉት 600 የእንጨት ምሰሶዎች ወደ ኮንክሪት ምሰሶ ይቀየራሉ፤ ከጭሮ እስከ ሂርና 46 ኪ.ሜ፣ እስከ ዱባ ወረዳ ደግሞ 18 ኪ.ሜ በአጠቃላይ 64 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመሮች መልሶ ግንባታ ይከናወናል፡፡
የመልሶ ግንባታው ከሂርና ፊደር አገልግሎት የሚያገኙት ጡሎ ወረዳ፣ ሂርና ከተማ፣ ዱባ ወረዳ እና ግማሽ መስላ ወረዳ የኃይል አቅርቦት ያልተቆራረጠና ጥራት ያለው እንዲሆን ያስችላል፡፡
በአሁኑ ወቅት የኮንክሪት ምሰሶ ግዢ ተፈፅሞ የቁፋሮ ሥራ የተጀመረ ሲሆን በሁለት ወራት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል፡፡
በተመሳሳይ ለረዥም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውን የገለምሶ ከተማ የእንጨት ምሶሶ ወደ ኮንክሪት ለመቀየር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
መልሶ ግንባታው 37 ኪ.ሜ የሚያካልል እና ገለምሶ ከተማን፣ የኦዳቡልቱም ወረዳ ገጠር ቀበሌዎችን፣ የበአብሮ ወረዳ ገጠር ሳተላይቶች፣ የተሰወኑ የዳሮ ለቡ ቀበሌዎች ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ የሚያግዝ ነው፡፡
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
[Facebook]
http://www.facebook.com/EEUOfficial[Telegram]
https://t.me/eeuethiopia[Website]
http://www.eeu.gov.et