🚧አንብቡት
⓵ የስራ ሰአታችን ከጠዋቱ 3:30 እስከምሽቱ 11:30 ነው። ከዛ ውጪ ማታ እንዲሁም እኩለሌሊት ላይ የምትጽፉና የምትደውሉ ሰዎች እባካችሁ እረፉ! ቴሌግራም ላይም አትፃፉ ከተጠቀሰው ሰአት ውጪ🙏
⓶ የሰራተኞቹን ደሞዝ ይገባኛል ብለው የሚናገሩት ሰራተኞቹ ናቸው።ደውላችሁ እንድታወሩ ስናረግ እንድትደራደሩ እንዲሁም የቤታችሁን መስፈርት ማሟላት አለማሟላላታቸውን እንድታወሩ ነው። በደሞዙ የተነሳ እኔን እንዲሁም ሌሎች አብረው የሚሠሩትን ደላሎች ከመቆጣት አልፎ አልባሌ ቃላት የምትጠቀሙ አንዳንድ ሰዎች ይሄ የስራ ቤት ነው እንደየአቅማችሁ ሰራተኛ አለ እኛን አትቆጡን
⓷ የቤተሰብ ብዛት የትኛውም ደላላ ቢሮ የሚጠየቅ ጥያቄ ነው።ያ የሚሆነው የልጆቹን የመስራት አቅም እንዲሁም ከልጆች ጋ ያላቸውን ትስስር ለመለየትም ጭምር ነው። የቤተሰብ ብዛት ለሰራኞቹ በስልክ ነግራችኋቸው ተስማምተው ከሄዱ በኋላ ከተጠቀሰው ሰው በላይ አጋጥሟቸው አልሰራም ብለው ቢወጡ ጥፋቱ የቀጣሪው ነው። እኛ ነገሮችን አስተካክለን ስንልክ እናንተም በታማኝነት ከኛጋ መረጃ ተለዋወጡ🙏
አቤቱታ አበዛሁ አ? ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስለገጠሙን ነው እነዚህ ነገሮች መጻፌም።
ይሄ ቤት እንደቤተሰብ ነው የተለያዩ የማህበረሰቡ አካላል አሉበት። እንደሁልጊዜው ለቅን አስተያየታችሁ ለእርማት እንዲሁም ለአስተያየት ክፍት ነው።
መልካም የስራ ቀን ይሁንልን🥰
https://t.me/efuyegellamarket