Postlar filtri


አድዋ!

እንዴትም ተደርጎ ቢፋቅ የማይጠፋ የጥቁር ህዝቦች ድል!

@EliasMeseret


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ገቢው ለመቄዶኒያ መርጃ የሚውል!

“ጀስቲሲያ” ፊልም በአሜሪካ፣ ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ፣ AFI ሲኒማ ቤት። ይሄን ምርጥ ስራ አጣጥማችሁ ለሜቄዶኒያም የበኩላችሁን ድጋፍ አድርጉ።

📍ቦታ፡ AFI Movie Theatre, 8633 Colesville Rd, Silver Spring, MD 20910
🎟 የመግብያ ዋጋ፡ $25
📞 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወይም ትኬት ለመቁረጥ በ 703-855-9422 ይደውሉልን

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው።


#FakeNewsAlert አልጀዚራ እንደዚህ ብሎ አልዘገበም፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የአቶ ሙላቱ ተሾመን አስተያየት ግን ዛሬ አቅርቧል

ሊንክ: https://www.aljazeera.com/opinions/2025/2/17/to-avoid-another-conflict-in-the-horn-of-africa-now-is-the-time-to-act

- 'እርቅ' የተባለው ነገር ሲመጣ ኤርትራ ሀገሯ እንዳልገባ ከዛ ሁሉ ሚድያ ለይታ አገደችኝ፣

- የእኛው መንግስት ደግሞ ኤርትራን ጋብዞ የትግራይን ህዝብ ሲያስፈጅ እና ዜና ስሰራ 'ውሸት ነው፣ የኤርትራ ሀይል አልሀገባም፣ ሀገር ለማተራመስ የባንዳ ስራ ነው' ብሎ ፈረጀኝ

Now this!

@EliasMeseret


እስከዛሬ የሚፅፉት እና የሚናገሩት ስለኢትዮጵያ መስሎኝ የሰጠሁት አስተያየት ቆጨኝ

ለካ ስለሌላ ሀገር ነው 🤔

@EliasMeseret


መቼም በአጥር ሾልካ ገብታ ወይም በፓራሹት ወርዳ አይሆንም፣

ይህ እንደ አንድ ተራ ክስተት ብቻ ሊወሰድ አይገባም፣ አመራሩ ሳያውቅ እንዲህ አይነት ድርጊት በሀላል የሚፈፀም ከሆነ የኤርፖርቱ ግቢ ደህንነት ምን ያህል አስተማማኝ ነው የሚል ጥያቄንም ያጭራል።

@EliasMeseret


ክፉ ግዜ!

ነፍስ ይማር!

@EliasMeseret


የጉልበት ስራ ሰርቼ ይቺን ቀን ሳይርበኝ ባሳልፍ ብሎ በየመንገዱ የሚንከራተት የሀገሬ ወጣት እየታፈሰ የሚደርስበት የግፍ ፅዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው

@EliasMeseret


500 ሺህ የፌስቡክ ወዳጅ 🙏🏽

@EliasMeseret


የተፈጠረ ብዥታ የለም፣ ህዝቡ ሊደረግ የታሰበው ገብቶት ነው

እንደ አንድ የመንግስት የመረጃ ምንጭ፣ በሚቀጥሉት 5 አመታት ብቻ ይህን ህግ በመጠቀም እስከ 60 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ (ለመዝረፍ) ታቅዷል።

@EliasMeseret


ከሁለት ኢትዮጵያዊ አንዱ፣ ወይም 60 ሚልዮን ገደማው ኤሌክትሪክ አያገኝም

መንግስት 13 ሀገራትን በኤሌክትሪክ ለማስተሳሰር እየሰራ ነው።

@EliasMeseret


#FactCheck የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በርካታ ታዳጊዎች ከመንገድ እየታፈሱ ወደ እርሻ ጣቢዎች በግድ እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፁ ይታወቃል

"እርሻዎቹ የት ይሆኑ?" ብላችሁ ለጠየቃችሁ እና ማጣራት ለምትፈልጉ፣ ዋና መዳረሻው በሚድሮክ ሆራይዘን ፕላንቴሽን ስር የሚተዳደረው የበበቃ ቡና እርሻ ልማት ነው። "ሚድሮክ ፈቅዶ ነው ወይ ተገዶ ነው?" ለሚለው ምላሽ ቢሰጥበት ጥሩ ነው።

ሚድሮክ በዚህ ዙርያ አስተያየት እንዲሰጥ ደጋግሜ ብጠይቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል፣ ህዝብ ግን ልጆቹ የት እየተወሰዱ እንደሆነ የማወቅ መብት አለው።

በነገራችን ላይ ታፍሰው እየተወሰዱ ያሉት የጎዳና ላይ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ እንደ ሊስትሮ፣ ፍራፍሬ መሸጥ፣ የጉልበት ስራ በመስራት፣ መኪና በማጠብ ወዘተ የሚተዳደሩ እና ቤተሰብ ያላቸው ልጆች ጭምር ናቸው።

@EliasMeseret


በጅማ ከተማ በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን እና  ህዝቡ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ “እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት፤ ልየው ነው’ ያለው” በማለት ጠ/ሚሩ ያሰፈሩትን ሀሳብ አየሁ።

የጅማ ህዝብ ደግሞ ባለፈት ሶስት ወራት በግሌም፣ በመሠረት ሚድያ በኩልም ሲያሰማ የነበረውን ጩኸት ከታች በምስሉ ላይ ተመልከቱ ⤵️

መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ የሰራቸው ዜናዎች:

1. https://t.me/meseretmedia/282

2. https://t.me/meseretmedia/516

@EliasMeseret


ተደጋግሞ ሲነገር ውሸት እንደሆነ ያሳብቅ ካልሆነ ህዝቡ በቀን ተቀን ህይወቱ ምን ያህል ፍዳውን እየበላ እንደሆነ ያውቃል።

@EliasMeseret


#መሠረትሚድያ

በጀት= 0 ብር

የሰራተኛ ብዛት= 1

በጎ ፈቃደኞች= 3

ተፅእኖ= 100 ፐርሰንት

ሁሌ እኮራለሁ!

@EliasMeseret

@MeseretMedia


የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር ያስከተለው ምስቅልቅል እና ምሬት

(መሠረት ሚድያ)- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በተለይ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻ ከተደረገ ወዲህ የኑሮ ውድነት ተባብሶ ቀጥሏል።

የመገበያያ ዋጋቸው እጅግ እየጨመሩ ከመጡ ምርቶች አንዱ ነዳጅ ነው። የዛሬ ሁለት አመት በዚህ ወቅት ቤንዚን በሊትር 61 ብር ነበር፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ይሸጥ ነበር፣ ኬሮሲንም በሊትር 67 ብር ነበር።

አሁን ላይ ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል፣ ናፍጣ ደግሞ በሊትር 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፣ በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል።

ታድያ የዚህ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ የህዝብ ትራንስፖርቱ ዋጋም በእጅጉ እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል። በተለይ በተለይ በአዲስ አበባ ዳርቻ አካባቢዎች በሰፈሮችና በኮንዶሚኒየምዎች የሚኖሩ ዜጎች ለትራንስፖርት የሚያወጡት ወጪ እጅግ በጣም ጨምሮ ኑሮን እንዳከበደባቸው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

ለምሳሌ በኮዬ ፈጬ፣ በአራብሳ፣ በቂሊንጦ፣ በቱሉዲምቱ ወዘተ... የሚኖሩ ዜጎች ከነዚህ መኖሪያ መንደሮች እስከ መገናኛ እንኳን ለመድረስ በአውቶብስ 20 ብር፣ በታክሲ ደግሞ 50 ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

"ወቅታዊ ታሪፉ ደርሶ መልስ በአውቶቡስ 40 ብር፣ በታክሲ 100 ብር ነው መገናኛ ድረስ ብቻ። እኛ ግን አልፈን ሄደን መሀል ከተማ ነው የምንሰራው፣ ለትራንስፖርት ብቻ በቀን እስከ 130 ብር በትሹ እናወጣለን" በሚል አስተያየት የሰጡት እነዚህ ዜጎች ይህንንም ለማግኘት ብዙ ተሰልፈው እና ተንገላተው እንደሆነ ያስረዳሉ።

"ይሄ እጅግ በጣም ኑሮአችንን አክብዶብናል፣ ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል። አቤቱታችንን በሚዲያችሁ አስተላልፉልን፣ የሚመለከተው አካል መፍትሔ ሊሰጠን ይገባል" የሚሉት እነዚህ ዜጎች የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ መነሳት ላልተጠበቀ እና እጅግ አቅምን ለሚፈታተን ከባድ ወጪ እንደዳረጋቸው በምሬት ይናገራሉ።

"በአንድ ቤት ውስጥ ብቻ ስራ ለመሄድ፣ ልጆችን ት/ቤት ለማድረስ እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን እንቅስቃሴ ሳይጨምር ለአንድ ሰው  ይሄን ያህል ወጪ በቀን እያወጡ እንዴት መኖር ይቻላል?" በማለት አስተያየታቸውን በጥያቄ ቋጭተዋል።

መረጃን ከመሠረት!

@MeseretMedia




ከእዳ ወደ ምንዳ ወይስ ከእዳ ወደ እዳ?

የተቃርኖ ዘመን!

@EliasMeseret


የትብብር ጥያቄ!

አቶ ገብረማርያም መለስ እድሜያቸው 85 ሲሆን ጥር 9/2017 ዓ/ም ከሰአት ላይ ጠፍተዋል፣ መጨረሻ የታዩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው። በሰአቱ ለብሰውት የነበረ ልብስ ጥቁር ጃኬት ነው፣ ከዘራም ይዘው ነበር።

አቶ ገብረማርያምን ያየ ሰው በዚህ ስልክ ቁጥር ቢጠቁመን ብለው ቤተሰብ ተማፅኖ አቅርበዋል:

0920581054


እንኳን ለደማቁ የጥምቀት በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

መልካም በዓል!

@EliasMeseret


ኦሮሚያ ውስጥ ወታደሮች አንድ የሲቪል ልብስ የለበሰ ወጣትን እጁን ወደኋላ አስረው በጭካኔ ሲረሽኑ የሚያሳይ ቪድዮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ተለቋል

ቆይ፣ ይህ በቪድዮ የተቀረፀ ነው። እንዲህ ተቀርፆ ለህዝብ ያልደረሰ ምን ያህል ግፍ በየቀኑ ይፈፀማል?

ነፍስ ይማር ወንድሜ!

@EliasMeseret

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.