ትዝብት _ሰርግ ❗️
በዘመናችን የሚደረገው ሰርግ ለፎቶ ሆኗል።
በሚያሳዝን ሆኔታ የሰርጓ ቀን ፎቶ ካልተነሳች ካንተጋ አልሄድም ከቤቴ ነው መቆየት የምፈልገው የሚሉ እንሰቶች እንዳሉ እየሰማን ነው ሱብሃነሏህ።
ያሳዝናል ጋብቻን የመሰለ ትልቅ ተግባር የተንዘላዘለ እና በዛዛታ የታጨቀ መጥፎ ተግባር የሞላበት አድርገውት ቁጭ ካሉ እየሰነበተ መጥቷል።
… ሴቶች ❗️❗️
በተለይም ሴቶች ጋብቻ ሲያስቡ ቀድመው ፎርም የሚያስሞሉት የፎቶ ቦታ እና ለፎቶ የሚሆን ምቹ ልብስ ነው ለነርሱም ለሚዜዎችም የሚሆን ።
እረ እባካችሁ ጋብቻው ትኒሽ እንኳ ሱና ይምሰል።
ፎቶ እኮ ሀራም ነው የሚሉ ዑለማዎችም አሉ
ምን አይነት መንዘላዘል ነው።
ዲናቸውን ትምረዋል የሚባሉትማ እየባሰባቸው መጥተዋል።
ወደየት ነው የምትወስዱን ❓።
እኔ ፎቶ መነሳት አልፍልግም ቬሎ ልብስም አልከራይም የሚል ባል እማ ~ ምነው አቅም አጠህ ነው?
ደሃ ሆነህ ነው? እእ ንገረኝ ምን ጨነቀህ እያሉ ጭንቅላቱን ሲያናጉት እረ እዛው ደስ ያለሽን አድርጊ ላለቀ ነገር ብሎ ያደርጋል ።
ወሏሂ ወዳጆቼ ይህንን አይነት የተንዘላዘለ ጋብቻ በማስቀረት ትብብር ማድረግ ይኖርብናል።
በተለይ ሴቶች የአስተሳሰብ እጥረት በአብዛኞቻችሁ ላይ ስለሚንፀባረቅ ልብ በሉ ወንዶች እንዳያገቡ አታድርጉ።
አይ አይ ኡስታዝ ❗️❗️
እናንተ ይህን ትላላችሁ እንጅ ከናንተ ታላለቅ ኡስታዞች አድርገውት የለ እእ… ?
የሚሉም በዛ እያሉ ነው~ እነዛ ተላላቅ ኡስታዞች ወደው ያደረጉ መሰለሽ ?
በስንት ጭቅጭቅ እና ንትርክ ነው በስንት ጉትጎታ እና ንዝነዛ ነው ይህን እንኳ ማስታወስ ተሳነሽ ? ወይስ ማሰብ እያቆምሽ ነው ?
ስለዚህ ላላገባችሁ ውድ እህቶቼ ወንድሞቼ ይህችን አጭር ጥቆማ ተግባራዊ በማድረግ እንተባበር።
~~~~
ሸሪዐዊ እውቀት ተምራለች ብለህ
ካልተማሩት የተለየ ነጥብ ይኖረዋል ብለህ ከማሰብ ጋብ ማለት ይኖርብሃል ።
___
ክፍል ① ~ ሀቢብ ኑሩ
እለተ ቅዳሜ ካቲት 26 /6 /2014
ማርች 5/3/2022
https://t.me/elmudinIslamicstudio/12571