የኢ.ኤም.ኤስ የእለተ እሁድ አጫጭር መረጃዎች
1. በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር የኢትዮጵያ ሰብዓው መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰቧል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል” ዳግም እየተካረረ የመጣው የጦርነት ስጋት እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።
ከ19 ወራት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ለተለያዩ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ ያወሳው ኢሰመኮ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት ለመግባት እያደገ የመጣው መካረር ሊቆም እንደሚገባ ገልጿል።
2. ሕንድ በግዛቷ የሚመረት ስንዴ ወደ ውጭ ሀገራት እንዳይወጣ እገዳ መጣሏን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል።ሆኖም አዲሱ የስንዴ የውጭ ሀገራት እግድ ከዚህ በፊት በሂደት ላይ የነበሩ የስንዴ ግብይቶችን እንደማይመለከት አስታውቃለች። የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው የሕንድን ውሳኔ የኮነኑ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲሉ አክለዋል። ሕንድ በስንዴ ሽያጭ ላይ እገዳ መጣሏ በተለይም በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት የተቋረጠባቸው የአፍሪካ እና እስያ ሀገራት ሕንድን እንደ አማራጭ ለመጠቀም አስበው ነበር። በሕንድ አንድ ቶን ስንዴ በ25 ሺህ ሩፒ ወይም በ320 ዶላር የሚሸጥ ሲሆን፤ ወደ ውጪ ሀገራት አዲስ የሚደረጉ የስንዴ ግብይቶችን በሀገር ውስጥ የምግብ እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ ምርት ከሀገር እንዳይወጣ እገዳ ጥላለች።
3. የፊንላንድ መንግስት አሜሪካ መራሹን የኔቶ ጥምር ጦር መቀላቀል እንደሚፈልግ በይፋ አስታውቋል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ከካቢኔያቸው ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ፊንላንድ የኔቶ አባል ለመሆን በምታቀርበው የአባልነት ጥያቄ ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል። ይህ የካቤኒው ስምምነት ለመጽደቅ የፓርላማ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል ተብሏል።
4. ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ስታካሂድ ውላለች፡፡ ከማለዳ ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እየተካሄደ ይገኛል። ይህ የዛሬው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ነበር። ቀጥተኛ ባልሆነው በዚህ ምርጫ ላይ 30 በላይ እጩዎች እየተወዳደሩ ይገኛሉ።
https://t.me/esat_television_official