Once again ሁላችንንም ያገባናልና ወደኢትዮጵያ የማይኒንግ ጉዳይ ልመልሳችሁ ተገደድኩ። እንደምታውቁት በተለይ በፕሮጀክት ማኖ እና ቃል ካሳ በተባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ መሀከል በነበረው እሰጥ አገባ እንደአንድ የክሪፕቶ ኮሚዩኒቲ መሀል ገብተን አስታራቂ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ሞክረን ነበር። ይሁንና ጉዳዩ ወደባሰ ሁነት በመጓዝ ላይ በመሆኑም አንድ ሰፋ ያለ የመወያያ መድረክ እንደሚያስፈልገንና ህብዝም በይፋ መስማት ያለበትን ሰምቶ እንዲፈርድ የመወያያ መድረክ ለማዘጋጀትና ሀሳቦቻቸውንም ይገልፁልን ዘንድ የግል ሀሳቤን ማንሳቴም የሚታወስ ነው።
በዚህም ፕሮጀክት ማኖ ቡድን ለጥያቄው አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት በመድረኩ ለመገኘት ሙሉ ፍቃዳቸው አሳይተው የነበረ ሲሆን ቃል ካሳ በበኩሉ መልእክታችን የደረሰውና ያየው እንደሆነ ቢያመላክትም ምንም አይነት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። ይህን ሁነት በመመልከት ዝም ብዬ መቀመጥ አልቻልኩምና ምናልባትም በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ በቢትኮይን ማይኒንጉ እንቅስቃሴ ጉምቱ ስም ያካበተውን እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ የቢትኮይን ማይንኒግ ኩባንያ መስራች የሆነውን
ዶ/ር ኔሞ ስምረትን ይህንኑ ጉዳይ ለህዝብ በሚገባው መልኩ እና ሁላችንም ጥቅሙንም ጉዳቱንም በምንለይበት መንገድ ያስረዳልን ዘንድ፤ በጠረጴዛ ዙሪያም ፕሮጀክት ማኖዎች ያነሱትን ሀሳብ በተማረ እና ስነ አመንክዮ ላይ በተመሰረተ መንገድ ለመወያየት ጥያቄ አቅርቤለት ነበር።
ያለምንም ማቅማማትም በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝቶ ሀሳቡን ሊያካፍለን ፍቃደኝነቱን ሊያሳየን ችሏል። የተማረ ይግደለኝ አይደል የሚባለው . . . እናማ my people አሁንም የታፕ ታፕ እርዳታችሁን ልጠይቅና ከዚህ በታች ያለችዋን ዶ/ሩን ያመሰገንበትን እና በይፋ ጥያቄያችንን መቀበሉን የገለፅንበትን የትዊተር ፖስት አንድ ላይክ እና ሼር በማድረግ ቤተሰብነታችሁን ታሳዩኝ ዘንድ ለመጠየቅ ወደድኩ። በእርግጥ ጉዳዩ በጣም የሰፋና ጠንካራ የሆነ አገራዊ መሰረት ያለው በመሆኑም በዚህ ዝግጅት ዙሪያ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሁሉ የትውልድ ሀላፊነት እንዳለብንም ለማስታወስ ወደድኩ። Lets go family...show some love. ❤️🙏🏾
https://fxtwitter.com/CryptotalkEt/status/1897262005154660539