ሰበር ዜና ET🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot

የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ፓስፖርት‼️
አዲሱ ፖስፖርት ዛሬ ይፋ ተደረገ‼️
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ዘርጋሁት ባለው የኢ-ፓስፖርት ሲስተም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚስጥራዊ ህትመትና ቴክኖሎጂ ልምድ አለው ከተባለው የጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አ.ማ አማካይነት ዘመኑ በደረሰበት የሚስጥራዊ ህትመት የታተመ አዲስ ፖስፖርት ዛሬ የካቲ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ይፋ እያደረገ ነው፡፡
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ የትግራይ ፀጥታ ኃይል አባላት በደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ሰሓርቲ ወረዳ አዲስ ዓለም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በነዋሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በማለት ትናንት ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን አውግዟል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የተወሰኑ የክልሉ ፀጥታ ኃይል አመራሮች የጊዚያዊ አስተዳደሩን መዋቅሮች ለማፍረስ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው በማለት ከስሷል።

የፀጥታ ኃይሉ የአንድ ቡድን የሥልጣን መወጣጫ መሳሪያ ሊኾን እንደማይችል የገለጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ኹኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ክልሉ ከባድ ቀውስ ውስጥ ሊገባ ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ ትናንት የተወሰኑ የፀጥታ ኃይል አባላት የቀበሌ አስተዳደሩ ማኅተሙን እንዲያስረክብ ባስገደዱበትና፣ በዚሁ ወቅት ድርጊቱን በተቃወሙ ነዋሪዎች ላይ የኃይል ርምጃ በወሰዱበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


በውጭ ሀገር ላላችሁ ባላችሁበት የፈለጋችሁን ነገር ማሰራት ይቻላል መምህር ይትባረክ  ባህላዊ
መድህኒት ቀማሚ ትክክለኛዉን እና የቀደምት የሊቃዉንት የአባቶቻችን ጥበባቶች ይሻሉ ወይንም ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ ፈውስ እና ጥበብ ከፈለጉ ደዉለዉ ያናግሩ 🇪🇹
  @merrgetaa                   
በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 🌿🌿ለመፍትሄ ሀብት
2 🌿🌿ለህማም
3 🌿🌿ለመስተፋቅር
4 🌿🌿ቡዳ ለበላው
5 🌿🌿ለገበያ
6 🌿🌿የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 🌿🌿ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 🌿🌿ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 🌿🌿ለዓቃቤ ርዕስ
10🌿🌿ለመክስት
11🌿🌿 ለቀለም(ለትምህርት)
12🌿🌿 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🌿🌿 ለመፍትሔ ስራይ
14🌿🌿 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🌿🌿 ለሁሉ ሠናይ
16🌿🌿 ለቁራኛ
17🌿🌿 ለአምፅኦ
23🌿🌿 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24🌿🌿 ለግርማ ሞገስ
25🌿🌿 መርበቡተ ሰለሞን
26🌿🌿 ለዓይነ ጥላ
27🌿🌿 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28🌿🌿 ለሁሉ መስተፋቅር
29🌿🌿 ጸሎተ ዕለታት
30🌿🌿 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31🌿🌿 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32🌿🌿 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33🌿🌿 ለድምፅ
34🌿🌿 ለብልት
35🌿🌿 በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ
  @merrgetaa
   @merrgetaa
               ☎️.  09 17 46 89 18
   🇮🇴🇧🇮🇧🇫🇨🇲🇨🇱   ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ
1🌿🌿የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
2.🌿🌿 ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
3. 🌿🌿ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
4.🌿🌿 ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
5🌿🌿. ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
6.🌿🌿 ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
7🌿🌿. ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8🌿🌿. ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
9.🌿🌿 ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
10🌿🌿. መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
11.🌿🌿 ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን

ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር እኛ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልኝ ወይም በቴሌግራም መምህር ይትባረክ  ብላችሁ ታገኙናላችሁ
ወይም በስልክ ቁጥር
ለጥያቄዎ      #0917468918
ይደውሉልን    #0917468918

09 17 46 89 18
🌿🌿🌿🌿🌿🍀🍀🍀
  🍀 በዋሳፖ   በኢሞ ይደውሉልን
   👇👇👇👇
@merrgetaa
@merrgetaa
@merrgetaa


የኤርትራ መንግሥት የክተት አዋጅ‼️
የኤርትራ መንግስት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በታች የሆኑ ዜጎችን የውትድርና ስልጠና እንዲሰጥ እና እንዲለማመዱ ለሁሉም ክልሎች አስተዳደር መመሪያ ማውጣቱን ምንጮች ገልጸዋል‼️
ይህ እርምጃ ከግዳጅ የተበተኑ፣ተጠባባቂ የነበሩ እና ቀደም ሲል በማገልገል ላይ የነበሩትን ያካትታል።
በተጨማሪም ያገቡ ሴት ወታደሮች እና ልጆች ያሏቸው ወደ ወታደራዊ ክፍላቸው እንዲመለሱ ታዘዋል።
በመመሪያው መሰረት እድሜያቸው ከ50 በታች የሆኑ ግለሰቦች ከሀገር እንዳይወጡ የተከለከሉ ሲሆን ይህ የግዳጅ ምልመላ እና በእንቅስቃሴ ላይ የተጣለው እገዳ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። የክልል አስተዳደሮች የሚመለከታቸውን ዜጎች የማሳወቅ፣ የመመዝገብ እና የማሰባሰብ ስራ መጀመራቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።
ጦርነቱ ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለሚገመት ይህ ድንገተኛ እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ቅስቀሳ በኤርትራ ማህበረሰብ ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ "የኤርትራ መንግሥት የፕርቶሪያ ስምምነትን ያልተቀበሉ ሰዎችን በማሳተፍ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው" የሚል ሀሳብ ለአልጀዚራ እንግሊዘኛው ክፍል በኩል ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።
ይህን መረጃ የወሰደው በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ከሚሰራ ከአንድ ትልቅ አለም አቀፍ ግበረሰናይ ድርጅት/ ከኤርትራ ቅርንጫፍ ነው።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ሰበር መረጃ‼️
በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ የእስራኤል አምባሳደር ተናገሩ‼️
በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ግብፅ የሰላም ስምምነቱን በእጅጉ እየጣሰች ነው ብለዋል።  በቅርቡ በግብፅ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ በዛሬው እለት ዝተዋል።

አክለው የተናገሩት በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር ግብፅ ኢንተርኔቱን እና ሶሻል ሚዲያውን በግብፅ ጦር ምስሎች አጥለቅልቃው እየተመለከትን ነው ሲሉ ከሰዋል።
በግብፅ በኩል ያልተለመደ የተባለለት ሰሞንኛ ክስተት የተስተዋለው በተለይም የግብፅ ፓራትሮፐር ብርጌዶች በኦክቶበር 7 ሐማስ ጥቅም ላይ ያዋለውን  አይነት የአውሮፕላን ዝላዮች እና ኦፕሬሽኖችን ጨምሮ የተቀናጀ ነው የተባለለትን የወታደራዊ ስልጠና ልምምዶችን የሚያካሂዱበት ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መዳረሱን ተከትሎ ነው።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ሳፋሪኮም‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በጥቂት አከባቢዎች ተቋርጦ የነበረው አገልግሎታችን ወደነበረበት ተመልሷል ሲል ሳፋሪኮም አስታወቀ። ስለተፈጠረው ሁኔታ ይቅርታ ጠይቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ታገደ‼️
የደቡብ ኮሪያ መንግሥት በ AI technology ዘርፍ ብዙዎችን ያስደመመውን Deep seek የተባለውን መተግበሪያ ቁልፍ አድራሻዎችን፣የግለሰብ መረጃዎችን በመስረቅ እና አሳልፎ በመስጠት ጠርጥሬዋለሁ ያለች ሲሆን የወንጀል ምርመራ እስኪደረግ ድረስ DeepSeek የተባለው መተግበሪያ በሀገሪቱ እንዳይሰራ ማገዷን አስታውቃለች።
====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ትራምፕ vs ዘለንስኪ‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን በጆ ባይደን አስተዳደር ወቀት ከአሜሪካ የወሰደችውን 300 ቢሊዮን ዶላር መመለስ አለባት ብለው ያምናሉ።
ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንት በፊት ዩክሬን ለአሜሪካ ውድ የተባሉ የመሬት ማዕድናትን ለመውሰድ በይፋ ትዕዛዝ ያስቀመጠች ሲሆን የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አሜሪካ የ 500 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያላቸውን የከበሩ ማዕድናትን ለመውሰድ ባቀረበችሁ ትዕዛዝ ላይ የሀገሪቱ የማዕድን ሚኒስቴር እንዳይፈርም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል።
የዘለንስኪ አማካሪ በበኩሉ አሜሪካ የዩክሬንን የከበሩ ማዕድናትን ለመውሰድ ያስተላለፈችው ትዕዛዝ "በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አውሮፓዊያን አፍሪካን መቀራመት" በሚል ካስተላለፉት አምባገነናዊ ትዕዛዝ ጋር ተመሳሳይ ነው ሲሉ ተችተዋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ተገደለ‼️
የዓለማችን የመጀመሪያው የግብረ ሰዶማዊ  ኢማም ነው ተብሎ የሚታመነው ሙህሲን ሄንድሪክስ በደቡብ አፍሪካ ግቤርሃ ከተማ አቅራቢያ በጥይት ተመቶ መገደሉ ተነገረ ‼️

ትላንት ቅዳሜ ቀን ላይ  ሙህሲን ሄንድሪክስ ከሌላ ሰው ጋር በመኪና እየተጓዙ ሳለ መኪናው ላይ ያልታወቀ ሰው ሰዎች የጥይት እሩምታ እንዳወረዱ ፖሊስ ተናግሯል።

ፖሊስ በሰጠው መግለጫ "ሁለት ፊታቸው ያልታወቁ ተጠርጣሪዎች ከተሽከርካሪው ወርደው በተሽከርካሪው ላይ ብዙ ጥይቶችን መተኮስ ጀመሩ" ብሏል።  "ከዚያ በኋላ፣ ከቦታው ሸሹ። ከኋላ የተቀመጠው ሄንድሪክስ በጥይት ተመትቶ እንደተገደለ አውቀናል ።" ሲል ፖሊስ ተናግሯል።

ገዳዮችን ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነውም ሲል ሲቲዝን የተባለ የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የህወሓት ምላሽ‼️
ምርጫ ቦርድ ቢሰርዝም/ባይሰርዝም ፋይዳ የለውም:-ህወሃት‼️
በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ ከአሸባሪነት ተሰርዞ ወደ ህጋዊ ማንነቱ እንዲመለስ እንጂ እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ጠይቆ አያውቅም። ስለዚህ ህወሓት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ያልጠየቀውን፣ያልተቀበለውን እና በህግ ላይ ያልተመሰረተ ዕውቅና ቢሰርዝም ባይሰርዝም ህጋዊ ፋይዳ የለውም። በፍትህ ሚኒስቴር ተፃፈ የተባለው ደብዳቤም ያልተጠየቀ እና ህወሓት የማያውቀው ነው ብሏል። እንዲሁም በይዘቱ በፍጹም አንስማማም ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት በሚመለከተው ህግ መሰረት የወያኔን ህጋዊ አቋም ማስመለሱ ከባድ አልነበረም። የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያን መንፈስ እና ፅሁፍ በትክክል በመተግበር የትግራይን ህዝብ ችግር ለማቃለል ግዳጁን መወጣት አልቻለም ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሓት በህወሀት ህጋዊ ሰውነት መመለስ ዙሪያ ያለውን አላስፈላጊ ጥፋት ለኢትዮጵያ መንግስት ለማስረዳትና በውይይት ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። የኢትዮጵያ መንግስትም ጉዳዩን በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት ገልጿል። መፍትሄዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ቀጣይ ውይይቶች እየተደረጉ ነው። ይህ አበረታች ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርቡ ይጠናቀቃል ብለን እናምናለን።
ፕሪቶሪያ ፖለቲካ ነው ማንም ሰው በቴክኒክ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ እንዲበላሽ ካደረገ ተጠያቂው እራሱ ነው እንጂ ወያኔ አይደለም ብሏል።
በተጨማሪም የፕሪቶሪያ ስምምነት በአስቸኳይ እንዲተገበር እንጠይቃለን"ሲል በመግለጫው አስታውቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


በዉስጥ መስመር የደረሰን እንደወረደ
👇👇
እረ በናታችሁ ሰበር ዜናወች አንድ ጥቆማ  ልስጥ ይሄውም  ከወልዲያ-ጋሸና ያለውን መንገድ ጩሁልን ወላድ ረፈር ሲባል በስቃይ ነው ወልዲያ የሚደርስ እንዲሁም ትልልቅ ትራከሮች,ሎቤዶች,ቦቲዎች በመንገዱ ሲሄዱ በጣም ነው ሲቃዩ  በቃ መንገድ ነው ብሎ ለመጥራት ያሳፍራል/  መንገዱን ለመግለጽ ቃላት የለኝም ዋና መንገድ ነው ከጂቡቲ ባህርዳረ እንዲሁም ወርታ ደርቅ ወደብ ለመድርስ ያለ ስቃይ  በናታችሁ አሰሙልን ከስጋ አልፎ ለነፍስ ይበጃል ይህ ጉዳይ የእናቶች ስቃይ  የህብረተሰቡ እንግልት ቤት ይቁጠረው።

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ትራምፕ እና ፑቲን ተስማሙ‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው አቻቸው ጋር ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ከፈጀ የስልክ ውይይት በኋላ በዩክሬይን ጦርነት ዙሪያ ድርድር እንዲደረግ መስማማታቸው ተገልጿል።

ትሩዝ በተሰኘው የማህበራዊ ገጻቸው "ከፑቲን ጋር ረዘም ያለ እና በጣም ውጤታማ የሚባል ውይይት አድርገናል ብለዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ በበኩሉ "ትራምፕ እና ፑቲን ለአንድ ሰዓት ተኩል ያክል በስልክ ከተወያዩ በኋላ ለመገናኘት ተስማምተዋል" ሲል ገልጿል።
ዜሌንስኪ ሰላም እንፈልጋለን ብሏል።
እ.ኤ.አ 2020 ላይ በጆ ባይደን ተሸንፈው ከነጩ ቤተመንግሥት ከተሰናበቱ ወዲህ ዳግም ካማላ ሀሪስን አሸንፈው የተመለሱት ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የሩሲያን እና ዩክሬይንን ጦርነት ሥልጣን ላይ በወጣሁ በመጀመሪያው ቀን አስቆመዋለሁ ሲሉ እንደነበር አይዘነጋም።
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


200መቶ የሽንት ሀይላንዶች በተከራየበት ቤት ውስጥ ተገኘ‼️
በምዕራብ አባያ ወረዳ ገጠር መሬት ለሆነ ፕሮጀክት ስራ ከሌላ አከባቢ የመጣ ግለሰብ ነበር፣ከሶስት ወራት ቆይታ በኋላ  ተከራይቶ በሚኖረው ቤት ውስጥ ከ200መቶ በላይ ሁለት ሊትር ሀይላንዶችን በሽንት ሞልቶ  ተገኘ።
ግልሰቡ ቤቱን ተከራይቶ የሚኖር ብፐቢሆንም የቤት ክራይ አይከፍልም፣ የመጣበት ስራ ስላልተሳካ አከራዮቹም ለመጠየቅ ፈሩተከራዩ ከቤት ብዙ ጊዜ አይወጣም ነበር።
አንድ ቀን ግን የቤት ኪራይ ክፈል የሚል እና ሌላ ጫና ሲያሳድሩበት ቤቱን ጥሎ በወጣበት ይቀራል። ባለበቶቹ ቤቱን በህግ አካል ሰብረው በሚገቡበት ጊዜ ነበር ቤቱ በሽንት የተሞላ ሀይላንድ ያገኙት ሲሉ ምንጮች መረጃውን በውስጥ መስመር አጋርተዋል።
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


መቆም ክልል ነው‼️
ከነገ የካቲት 05/2017 ዓ.ም ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰሩ አሸከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ መቁም አይቻልም ተብሏል‼️
በኮሪደር ልማት በለሙና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት ተሽከርካሪ በመንገድ ዳር ማቆም እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ፥ ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከተለያዩ የአፍሪካ ብሎም የዓለም ሀገራት እንግዶች አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን አንስቷል።

ስለሆነም ከዛሬ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ማታ 12:00 ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር ማቆም እንደማይቻል አስታውቋል።

በኤሌክትሮኒክ ክፍያ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ፣ የሜትር ታክሲ፣ የላዳ፣ የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች መልዕክቱን እንዲተገብሩም ቢሮው አሳስቧል።
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


#የቦንብ ጥቃት‼️
በትግራይ ክልልጰሽሬ ከተማ በተወረወረ ቦንብ ንፁሃን ላይ ጉዳት አደረሰ‼️
ትናንት ምሽት በሽሬ ከተማ በተለምዶ ሀረግ ፓርክ በተባለ ሰፈር ቦንብ ተወርውሮ 10 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በተወረወረው የቦንቦ ፍንዳታ ጉዳት የደረሰባቸው የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል። በተጨማሪ መረጃ በዚሁ አካባቢ በጥር ወር ተመሳሳይ ቦምብ ተጥሎ ሳይፈንዳና ጉዳት ሳያደርስ እንደቀረ ታውቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ መሪዎች ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለሁ አሉ‼️

👉🏿 ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?


👉🏿በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ቢሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?

👉🏿በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን  ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

👉🏿የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር  ትጠብቃላችው?

👉🏿በራሳችው  አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን  ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችው?
ትራምፕ ይሄን የተናገሩት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የትራምፕ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ጣሉ‼️
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ መጣላቸው ተሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚኒ ኔታንያሁ በጋዛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል የእስር ትዕዛዝ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ ነው የማዕቀብ ሰለባ የተደረገዉ።

ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መሠረት አልባና ሕጋዊ ያልሆነ ፍርድ በአሜሪካና በወዳጆቿ ላይ ሲያስተላልፍ ነበር ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።

ማዕቀቡ በICC ውስጥ የሚሠሩ ግለሰቦችና ቤተሰቦች ላይ የገንዘብና የቪዛ ክልከላን እንደሚያጠቃልል ተነግሯል።
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ተገደለ‼️
በአማራ ክልል በሸዋሮቢት በአራት ግለሰቦች ላይ  ጉዳት ያደረሰው ነብር ተገደለ‼️
በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ በሮቢ የትንባሆ እርሻ ልማት ድርጅት ውስጥ በስራ ላይ የነበሩ አራት ግለሰቦች ላይ ነብር ጉዳት ማድረሱን የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አስታውቋል ።

ነብሩ ጉዳቱን ካደረሰ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በጥይት ተገድሏል።

ጉዳት የደረሰባቸው አራቱ ሰዎች በሸዋሮቢት  የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA

18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.