ETHIO-MEREJA®


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


💸💰አፍሮስፖርትን ይቀላቀሉ! ማለቂያ የሌላቸውን የማሸነፍ ዕድሎችን ይጠቀሙ!💰⏳

አሁኑኑ ድህረ ገጻችንን https://bit.ly/3XbY3o7 ይጎብኙ!

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት ቀረበ


አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጿል።

ፖሊስ እስካሁን አሻራ ማንሳቱን፣ አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመላክ፣ የአስከሬን ምርመራ ማድረጉን ገልጾ የሰው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

"አሁን ፎቶግራፎችን ከመዝገቡ ጋር ለማያያዝ፣ የሰዎች ምስክርነት ለመስጠት እና የአስከሬን ምርመራው እስኪመጣ ድረስ ለማጣራት 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል።

የአንዱአለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይሰጥ ብሎ ቢጠይቅም ፍርድ ቤት የአስክሬን ምርመራ እንስኪደርስ በማለት 13 ቀናት ድምፃዊው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ወስኗል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


በኢትዮጵያ ቴሌግራም ተቋርጧል።

የቴሌግራም መተግበሪያ ላለፉት ደቂቃዎች አገልግሎቱ ተቋርጧል። እዚህ ሀገር ውስጥ ብቻ ወይስ ሌሎችም ሀገራት የሚለውን በማጣራት መረጃ የምንልክላችሁ ይሆናል።

እስከዛው አገልግሎቱን በVPN መጠቀም ይቻላል።


በዳታ ሙሉ በሙሉ ያለ VPN የማይሰራ ሲሆን አንዳንዶች በWiFi ያለ VPN እየሰራላቸው ይገኛል። አንዳንዶች በWiFiም ሆኖ ያለ VPN እየሰራላቸው አይደለም።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


❗️ጥንቃቄ ❗️

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን "ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክ" ሕገ-ወጥ ነዉ ሲል አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን "ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክ" በሚል ስም የሚንቀሳቀስ አካል ያለ ምንም ህጋዊ ፈቃድ የኢንቨስትመንት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ ይህ አካል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ ነኝ ብሎ ድረ-ገጽ ከፍቶ ማስተዋወቁን ገልጿል።

ባለስልጣኑ ባወጣው መግለጫ መሰረት ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክ በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016 መሰረት ፈቃድ ሳያገኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው። በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የካፒታል ገበያ አገልግሎት እንዲሰጥ ያልተፈቀደለት አካል መሆኑን አሳስቧል።

በተጨማሪም ባለስልጣኑ የካፒታል ገበያ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡና ፈቃድ ያላቸው አካላት ብቻ መሆናቸውን አስገንዝቧል።

ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከዚህ አካል ወይም ከሌሎች ፈቃድ ከሌላቸው "የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች" ጋር ማንኛውም አይነት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አሳስቧል።


    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


ተፈፀመ!!

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አርቲስት አንዱዓለም ጎሳ፣ ቤተሰቦቿ እና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት ተፈጽሟል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


በአፍሮ ስፖርት አኪዩሙሌተር የፈለጉትን ጨዋታዎች እንደፈለጉ ከስተማይዝ አድርገው የማሸነፍ እድሎን ያሳድጉ!

አሁኑኑ ድህረ ገጻችን ወይንም https://bit.ly/4dxEaNt ላይ ይግቡና ጨዋታዎን ከስተማይዝ ያድርጉ!

ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


ጀርመንኛ ቋንቋ ስልጠና በመራህያን

A1, A2, B1 and B2 and C1 Level

•አዲስ ቋንቋ መማር ለምትፈልጉ
•የጋብቻ ፕሮስስ ጀርመን ኤምባሲ መጀመር ላሰባችሁ
•የስራ ፕሮስስ ለመጀመር ያሰባችሁ

    •Online or Inperson

To register:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan


በሟች ወጣት ቀነኒ አዱኛ አሟሟት ዙሪያ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ!!

"ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ አልፏል " - ፖሊስ

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰንሻይን ቤቶች ፊት ለፊት ከሚገኘው ውዳሴ ህንፃ ላይ ነዋሪ የነበረችው ሟች ቀነኒ አዱኛ መጋቢት 01 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ እንዳለፈ ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃው ከደረሰው በኋላ የምርመራ ቡድን በማዋቀርና ቦታው ድረስ በመሄድ ተገቢውን የቴክኒክና የታክቲክ መረጃዎችን ያሰባሰበ መሆኑንና የሟችንም አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለተጨማሪ ለምርመራ እንዲሄድ ማድረጉን አመልክቷል።

ሟች ቀነኒ በወቅቱ ከበረዳ ላይ በወደቀችበት ሰዓት ፖሊስ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለም ጎሳን በቁጥጥር ስር በማዋልም ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

በቀጣይ የመጨረሻውን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ከፖሊስ የወንጀል ምርመራ ውጤት በፊት የሚናፈሱ መረጃዎች ተገቢነት የሌላቸው ናቸው ብሏል።

ከዚህ ባሻገር የሚናፈሱት መረጃዎች በምርምራ ሒደቱ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅህኖ በመገንዘብ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ እና የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡


    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


አርቲስት አንዷለም ጎሳ ከዕጮኛው ሞት ጋር በተያያዘ ለጥያቄ በፖሊስ መጠራቱ ተነገረ

በኦሮምኛ ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አንዷለም ጎሳ ከዕጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዝ በፖሊስ ጥያቄ እንደተደረገለት ተሰምቷል።

በማኅበራዊ ሚደያ በርካታ ተከታዮቿ ያሏት ቀነኒ አዱኛ ማክሰኞ ጥዋት መሞቷን ተከትሎ በርካቶች ሐዘናቸውን ከመግለፅ ባሻገር የሞቷ ምክንያት እንዲጣራ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

የአርቲስት አንዷለም ማኔጀር ሌሊሳ ኢንድሪስ የአስከሬን ምርመራው በሚኒሊክ ሆስፒታል እንደሚደረግ እና የሟች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ረቡዕ እንደሚከናወን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግሯል።

ቀነኒ ከሚኖሩበት ሕንጻ መውደቋን እና "ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ መሞቷን" ሌሊሳ ተናግሮ አንዷለም እና ቤተሰቦቹ ወድቃ እንዳገኟት አስታውቀዋል።

ሌሊሳ ንጋት 11 ሰዓት ሰዓት ስልክ ተደውሎ "ቀነኒ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደገባች" እንደተናገረው ገልጾ፣ "እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከአምስተኛ ፎቅ ወድቃ ነው የሞተችው። ሁኔታውን ለማጣራት ምርመራ ተጀምሯል" ብለዋል።

ሌሊሳ እንደሚለው አርቲስት አንዱአለም በአሁኑ ወቅት ለምርመራ በፖሊስ ጣቢያ ነው የሚገኘው።(ቢቢሲ)

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በሶሪያ ደቡባዊ ዴራ ግዛት ወታደራዊ ጣቢያዎችን አጠቁ

የእስራኤል ወታደራዊ አውሮፕላኖች በሶሪያ ደቡባዊ ግዛት ዴራ ላይ ጥቃቶችን እንደፈጸሙ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች እና የክትትል ቡድን ያሳወቁ ሲሆን በቀድሞው የበሽር አል አሳድ መንግስት ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ፈጽመዋል።በመንግስት የሚተዳደረው የሶሪያ አረብ የዜና አገልግሎት (SANA) ሰኞ ማምሻውን የተፈጸመው ጥቃት ከዋና ከተማይቱ ደማስቆ በስተደቡብ 103 ኪሜ ርቃ በምትገኘው በዴራ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኙ ሁለት ከተሞች ላይ ደርሷል።

“የእስራኤል ወታደራዊ አውሮፕላኖች በዴራ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኙ የጃባብ እና ኢዝራ ከተሞች አካባቢ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽመዋል” ሲል ሳና ዘግቧል።መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብት ታዛቢ ቡድን በእስራኤል ተዋጊ ጄቶች 17 ጥቃቶች በከተሞች ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወታደራዊ ቦታዎች ላይ መምታቱን ገልጿል::እስካሁን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ታዛቢው ቡድን አስታዉቋል፡፡

የእስራኤል ሚዲያ ቻናል 14 የአየር ጥቃቱ ያነጣጠረው በአል አሳድ መንግስት ጦር ሰፈር፣ የጦር መሳሪያ መጋዘኖች፣ ራዳሮች፣ ታንኮች እና መድፍ ላይ ነዉ ያለ ሲሆን በሶሪያ የሚገኙ አማፂ ቡድኖች “መሳሪያዎቹን ሊወስዱ እየሞከሩ ነበር” ብሏል።በታህሳስ ወር የሶሪያው ፕሬዝዳንት አል አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ እስራኤል በሶሪያ ኢላማዎች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአየር ድብደባዎችን ፈጽማለች።


    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


በተመረጡ የቨርቹዋል ጨዋታዎቻችን ጊዜና ቦታ ሳይገድብዎ ባሉበት ሆነው በአፍሮ ስፖርት ይወራረዱ!

እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ወደ👉https://bit.ly/3M9qBIw ይግቡና ይወራረዱ!

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


አሳዛኝ ዜና🕯🕯

የድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሚስት ቀነኒ አዱኛ በድገንት ህይወቷ አልፏል፤ ስለአሟሟቷ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል።

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ

19.1k 0 30 16 188

የአሜሪካ እና ዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት በሳኡዲ አረቢያ ተገናኝተው ሊመክሩ ነው

የአሜሪካ እና የዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑካን ቡድን ጦርነቱን ለማስቆም አላማውን ያረገ ውይይት በነገው ዕለት በሳኡዲአረብያ ያካሄዳል፡፡

ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለዲሚር ዘለንስኪ መካከል የተደረገው ውይይት ወደ ውዝግብ ከተቀየረ በኋላ ዩክሬናውያን ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ምልክቶችን የአሜሪካ ልዑካን እንደሚከታተሉ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩብዮ ፣ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ማይክ ዋልትዝ እና የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ለጉባኤው ወደ ጂዳ አቅንተዋል፡፡ሮይተርስ ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ስማቸውን ያልጠቀሳቸው አንድ ባለስልጣን ዩክሬናውን ከ2014 እና 2022 ድንበር ጥያቄ ባለፈ ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት መመልከት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር ኪቭ ከሞስኮ ጋር ሰላም መፍጠር የምትፈልግ ከሆነ አንዳንድ የግዛት ጥያቄዎችን መተው እንደሚኖርባት ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትላንትናው ዕለት ለጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር ከነገው የከፍተኛ ባለስልጣንት ውይይት ፍሬያማ ውጤት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡በዛሬው ዕለት ወደ ሳዑዲ ያቀኑት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው “ሰላምን ለማስፈን የማደርገውን ጥረት ለመቀጠል ወደ ሳኡዲ እጓዛለሁ” ብለዋል፡፡

ዘለንስኪ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሰላምን እንደማይፈልጉ እና ሩሲያ በዩክሬን ላይ በጀመረችው ጦርነት ግልፅ የሆነ ሽንፈት ካላስተናገደች ሌሎች የአውሮፓ ሀገራትን ታጠቃለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡አውሮፓውን የዩክሬን አጋሮች ደግሞ ኪቭ ከሩስያ ጋር ለመደራደር ጠንካራ ቁመና ላይ መሆን እንደሚገባት እና ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትገባ ግፊት ሊደረግባት እንደማይገባ ያነሳሉ፡፡ ትራምፕ በበኩላቸው ምስራቃዊ አውሮፓዊቷ ሀገር የሰው ሀይል እና ሃብት እየመነመነ እንደሚገኝ አሳስበው ከሩሲያ ጋር ለመስማማት በፍጥነት ወደ ጠረጴዛው መምጣት እንደሚኖርባት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

    T.me/ethio_mereja
         ኢትዮ-መረጃ


ጀርመንኛ ቋንቋ ስልጠና በመራህያን

A1, A2, B1 and B2 and C1 Level

•አዲስ ቋንቋ መማር ለምትፈልጉ
•የጋብቻ ፕሮስስ ጀርመን ኤምባሲ መጀመር ላሰባችሁ
•የስራ ፕሮስስ ለመጀመር ያሰባችሁ

    •Online or Inperson

To register:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan



15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.