የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ፡፡
------------------------------------------------
የካቲት 25 /2017 ዓ.ም 10ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በሐረሪ ብሔራዊ ክልል በሐረር ከተማ በሚገኘው ሞዴል አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከብሯል።
በክብረበዓሉ ላይ የተገኙት የሐረሪ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
አቶ ኦርዲን መርሃ-ግብሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግና የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራትን ከማሳደግ ባለፈ የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።
አቶ ኦርዲን ጨምረውም የትምህርት ቤት ምገባ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንጻር ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መርሃ-ግብር መሆኑን ጠቅሰው የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የመማር ማስተማር ትኩረትን በማይቀንስ መልኩ ራሱን የቻለ አደረጃጀት ተፈጥሮለት ሊመራ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ከመርሃ-ግብሩ አንጻር በክልሉ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር በለውጡ መንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝና ውጤት እያስመዘገበ ያለ መርሃ-ግብር መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1B9oAaubEK/