ሲግማው ስለ ስፖርት የተወሰነ ነገር ልበልህ ዝግጁ🔥🔥🔥
በሳምንት ውስጥ ከ3 እስከ 5 ቀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማከናወን:
- ጤናማና በቂ የሆነ እንቅልፍ መተኛት
- ጭንቀትና ድብርት ማስወገድ
- ከእድሜ ጋር የተያያዙ የመርሳት ችግሮች መቅረፍ
- የአዕምሮ መነቃቃት መጎናፀፍ
- ሰዎችን መውደድና ደስተኛ መሆን(የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስናከናውን በአዕምሮ ውስጥ ዶፖሚን የተባለ ሆርሞን ይመነጫል።የዚህ ሆርሞን ጠቀሜታ ሰዎች ደስተኛ እንዲሆኑና የፍቅር ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው)።
ሌላው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ኢንዶርፊን የተባለ ጠቃሚ ሆርሞንም እንዲመነጭ ያደርጋል።ይህም ሆርሞን የህመም ስሜት እንዲቀንስና የደስታ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ነው።
እጅግ ወሳኙ ነገር ደግሞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለወሲባዊ ህይወት እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ነው።በእንቅስቃሴ ወቅት የደም ዝውውራችን ጤናማ ሰለሚሆንና በቂ oxygen ስለምናገኝ ሴሎቻችን ተግባራቸው በአግባቡ እንዲያከናውኑ ይረዳል።በመሆኑም ጤናማ የሆነ የወሲብ ስሜት እንዲኖረን ይረዳል።
በወሲብ ምክንያት የሚፈጠሩ የግንኙነት መሻከሮችም የመቅረፍ ጠቀሜታ አለው ማለት ነው።እነዚህንና ዘረፈ ብዙ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታዎች በተከታታይነት ሳቀርብላችሁ በደስታ ነው።የትኞቹም ማወቅ የምትፈልጉት ጉዳይ በዚህ ዘርፍ ካለ የማውቀውን በደስታ ለማጋራት ዝግጁ ነኝ።
ከላይ የተጠቀሱትን የስፖርት ጠቀሜታዎች በአንድ ጀምበር ሳይሆን በቋሚነት ስንተገብር የምንጎናፀፋቸው መሆኑን ልብ ይበሉ!!!
JOIN
@Ethio_Sigmaa@Ethio_Sigmaa