ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


#𝑞𝑢𝑜𝑡𝑒
#𝑚𝑜𝑡𝑖𝑣𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛
#𝑖𝑛𝑠𝑝𝑖𝑟𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Which Unlocks The World Secrets?¿😐


"ፈጣሪ የት ነው..?"
       (ሩሚ)


የክርስቲያን መስቀል ላይ ልፈልገው ሞከርኩኝ ነገር ግን ከዛ የለም! የሒንዱስ ጥንታዊ ቤተ-መቅደስ ፓጎዳ ጎራ አልኩኝ ቢሆንም ዱካውን የትም ላገኘው አልቻልኩኝም!

ከተራራው እና ከሸለቆው አሰስኩት ግን በከፍታም፣ በዝቅታም ለማግኘት አልተቻለኝም! መካ ውስጥ ካዕባም ተጓዝኩኝ በተመሳሳይ እዛም ቢሆን የለም!

ጠበብቶች እና ፈላስፎችን ጠየኩኝ ዳሩ ግን እሱ (ፈጣሪ) ከመረዳታቸው በላይ ነው!

በመጨረሻ ከልቤ ስፍራ ማተርኩኝ፣ ማረፊያውን ያፀናው እዛ ነው፤ አየሁትም! እናም ሊገኝ ሚችልበት ሌላ ቦታ የለም!


Philosopy gora

SHARE||@ethio_tksa_tks


አሳ አጥማጆች ሁልጊዜ ላይቀናቸው ይችላል አይደል?

👇🏾

አሳ አጥማጆች ማእበል ሲያስቸግራቸው: አሳዎች የሚፈልግ ቦታ ላይ ሳይመጡላቸው: ንፋስ ሆኖ በቂ የሆነ ቀዘፋ ማድረግ ሳይችሉ ሌሎች ተግባራቶች አሏቸው

ከማእበል እና ንፋስ ጋር ታግለው ለማጥመድ አይጋጋጡም
.
ሁኔታውን እያወቁት "አሳ ካልያዝኩኝ ሞቼ እገኛለሁ" ብለው መረባቸውን አይጥሉም
.
አሳ መያዝ አልቻልኩም ብለው አይቆዝሙም

👇🏾

ባህሩ እስኪሰክን እና ንፋሱ ገለል እስኪል ድረስ ሌሎች ስራዎችን ይከውናሉ

መረባቸውን ያጠናክራሉ: ይጠግናሉ: ይሰፋሉ
.
ጀልባቸውን ያጠባብቃሉ: ቀዳዳዎችን ይደፍናሉ
.
ማእበሉ ሲበርድ እና አሳዎች ሲገኙ ለማጥመድ ይዘጋጃሉ

……………….

አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል?🤔

👇🏾

ቁጭ ማለት የሚገባን: ነገሮች የማይሆኑበት
.
ያሰብነው የማይሳካበት: ብንታገልም ድካም የሆነበት

አሳ አጥማጁን መሆን !!!

❤️🙌🏼


አንዳንድ ሰዎች ከእኛ ጋር ነበሩ እንጂ የእኛ አልነበሩም።


ትናንሽ ነገሮች ትንሽ ናቸው ብለህ አትዘናጋ ትኩር ብለህ ተመልከት። ትልቅ መርከብ እንዲሰምጥ የሚያደርገው ትንሽ ቀዳዳ ነውና።


©Benjamin Franklin

SHARE||@ethio_tksa_tks


#repost
🤔እረስቼዋለሁ

#አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት ....

"እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት!

ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡

እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት።

ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው።

አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡

ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት።

ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች።

አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው።

አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤

"አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ...

"እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ...

"የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡

እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!

እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

ሰው እንጂ ፈጣሪ ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል።

ፈጣሪ ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ!

ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪ እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ!

 "ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!"
አሜን!🙏


#LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት


❤መልካም ምሽት🙏

SHARE|


ታሪካችሁ ሲነገር እንዲህ እንዲባል አድርጉ እንዳቃታቸው እንዳልተሳካላቸው እንደወደቁ እንዳለቀሱ ሰዎች እንደተሳለቁባችው አልቀሩም ሁሉንም በድል አሸንፈዋል!💪👏👏👏

SHARE||@ethio_tksa_tks


በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው

አህያው ዛፍ ስር ታስሮ ነበር። በአጋጣሚ ሰይጣን መጣና አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ለቀቀው። አህያውም ወደ ማሳው እየሮጠ ገብቶ ሰብሉን ማውደም ጀመረ።

ይህን ያየችው የገበሬው ሚስት አህያውን በጥይት መታችው። የአህያው ባልተቤት ተበሳጨና የገበሬውን ሚስት ገደላት። ገበሬው መጣና ሲያይ ሚስቱ ሙታለች። ወዲያው አጸፋውን መለሰና የአህያው*ን ባለቤት ተኩሶ ገደለ*ው።

የአህያው ባልተቤት ሚስት ልጆቿን ጠራችና የገበሬውን ቤት እንዲያቃጥሉ አዘዘቻቸው። ልጆቹም አመሻሹ ላይ እናታቸው ያዘዘቻቸውን ለመፈጸም ገበሬውም በውስጥ ሲቃጠል እያሰቡ በደስታ ሄዱ። ወዲያውም ቤቱን አቃጥለው ተመለሱ። እንዳጋጣሚ በሚያሳዝን ሁኔታ ገበሬው እቤት አልነበረምና ተመልሶ መጥቶ የአህያ*ውን ባልተቤት ሚስትና ልጆቹን ገድሎ ተመለሰ።

ሲመለስ ግን ሰይጣንን መንገድ ላይ ያገኘዋል። ገበሬው ትንሺ ሰከን ሲል የሆነውን አስታውሶ ነበርና ሰይጣንን ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቀዋል? ሰይጣንም እንዲህ አለ፦ እኔ ምንም አልሰራሁም። አህያው*ን ብቻ ነው የፈታሁት። ግን ሁላችሁም የውስጣችሁን ሰይጣን ፈታችሁት። ሁሉንም ነገር ያደረጋችሁት እራሳችሁ ናችሁ።

ሌላ ጊዜ ለምንም ነገር ምላሺ ከመስጠታችን ፣ ውሳኔወችን ከማሳለፋችን በፊት ለአፍታ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል። ብዙጊዜ ሰይጣን የሚያደርገው ውስጣችን ያለውን አህያ መልቀቅ ነው። "በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው!"


SHARE||@ethio_tksa_tks


ሊያስጨንቅህ የሚገባው ከፊትህ ያለው ተራራ ሳይሆን ፤ ጫማህ ውስጥ ያለው ጠጠር ነው።

©Mohammad Ali🗣

@ethio_tksa_tks


“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
  — ሉቃስ 2፥11


እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሰን

🙏በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን🙏

መልካም በዓል❤️

@ethio_tksa_tks


እውነት የሚያስከትለው ህመም ቶሎ ያልፋል አዝጋሚ እና እያደር የሚበላው የውሸት ስቃይ ግን መቋጫ የለውም!
©John Steinbeck

SHARE||@ethiotksa_tks


ለአንድ ሰው ስትል ሁሉን ነገር
ትተዋለህ; ያ ሰው ግን ለአንድ
ነገር ሲል አንተን ይተውሀል::


SHARE ||@ethio_tksa_tks


.........አንዳንድ ሞቶች ከሟች ነፍስ በላይ ቋሚን ይገላሉ። አንዳንድ ስብራቶች ካለመኖር በበለጠ መኖርን ያስፈራሉ።ካለፈ ይልቅ መጪውን ከሟች ይልቅ ቀባሪን ያስፈራሉ። ለሚወዱት ምንም አለማድረግ የቋሚ ሌላ ሞቱ ነው።........


ምርጡ ፊልም አይተህ የወደድከው ነው እንጂ ኦስካር የወሰደው አይደለም...


ምርጡ ሙዚቃ የልብህን ያ ዜመው ነው እንጂግራሚ ያሸነፈው አይደለም...


ምርጡ ምግብ ተርበህ ያገኘኸው ነው እንጂ ጣፍጦህ የበላኸው አይደለም... 





ምርጡ ስጦታ ድንገት የመጣው ነው እንጂ ውድ ያወጣው አይደለም... 


ምርጡ ጓደኛህ ያልነገርከውን የሚሰማው ነው እንጂ እስክትነግረው የሚጠብቀው አይደለም... 

ምርጡ ጊዜ አሁን ነው እንጂ የሚመጣው አይደለም... 


ምርጡ ሃብት ፍቅር ነው እንጂ ገንዘብህ አይደለም... 


ምርጡ መንገድ የማትጋፋበት ነው እንጂ አስፓልት አይደለም... 


ምርጡ ስልጣን ራስን መግራት ነው እንጂ ሌላውን መግዛት አይደለም... 


ምርጡ እውቀት ራስን ማወቅ ነው እንጂያጠኑትን ማስታወስ አይደለም... 


ምርጡ ሰው ራሱን የሆነው ነው እንጂ መንጋው የከበበው አይደለም...


ምርጡ ባለውለታህ አቅምህን ያሳየህ ነው እንጂ ጥሪት ያኖረልህ አይደለም...

~

እና ደግሞ...

__

ምርጥነት ለሌሎች እንደሚታየው አይደለም... ለራስ እንደሚሰማው እንጂ...

SHARE ||@ethio_tksa_tks


የሰውን ትክክለኛ ባህሪ ለማወቅ ከፈለክ ስልጣን ስጠው


©Abrham Lincoln

SHARE ||@ethio_tksa_tks


በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡
ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡
እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን።
ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡ መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሰብ ዐይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ኃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ሆነ...
መብረቁ ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነበር። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም ለመጨረሻዉ ተሣፋሪ ንጽህና ነበር፡፡

SHARE ||@ethio_tksa_tks


እስቲ 2024 ለመጨረሻ ጊዜ በ Reaction እንሰናበተው 😊

Happy New Year 🥳🥳


እንዲህ አይነት ሰዎች ያስፈልጉናል
👇🏾
በቃኝ ስንል - ዛሬን ብታልፈው ያልፋል የሚሉን
.
ደክሞኛል ስንል - ጀርባችንን ደግፈው እንዳንወድቅ የሚደግፉን
.
ሰው የለንም ስንል - ሰው ማለት እኔ ነኝ የሚሉን
እስኪ ይሄን ፎቶ እዩት ! ሁልጊዜ አዲስ የሚሆንብኝ ፎቶ
ከድልድይ ላይ ወድቆ ራሱን ለማጥፋት የነበረ ሰው "አለንልህ" የሚሉ ሰዎች ህይወቱን አድነውት 🙌🏼
ለሁለት ሰአታት ያህል ከእርሱ ጋር ቆመዋል
.
ሰውነቱ እንዳይዝል ደግፈው ይዘውታል
.
ሰው ነን! አለንልህ! ብለውት አቁመውታል
ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነውና !!

SHARE||@ethio_tksa_tks


last day of 2024


የውሸት ጓደኛና ጥላ አንድ ናቸው ሁለቱም ፀሃይ ስትወጣ ነው የሚከሰቱት



በቅንነት SHARE & React እያደረጋችሁ

@ethio_tksa_tks

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.