Postlar filtri


አንድ ሰው የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ቢሆንም ንብረቱን ይዞ እስካልተጠቀመ ድረስ የውርስ ንብረቱን በያዘው ሰው ላይ የሚያቀርበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000/1/ መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ ቀሪ ነው።
የወራሽነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ የለውም በሚል ከዚህ በፊት የተሰጡ የሰበር ውሳኔዎችን በመለወጥ በ7 ዳኞች የተሰጠ አዲስ የህግ ትርጉም። የሰ/መ/ቁ 243973 ጥቅምት 06/ 2017 ዓ.ም

የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በማንኛውም ጊዜ የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት ይችላል በማለት ከአሁን በፊት በሰ/መ/ቁ 205248 44237 ቅፅ(10) 38533 ቅፅ(10) ወዘተ.. የተሰጡ የሰበር ውሳኔዎች በዚህ የሰበር ውሳኔ ተለውጠዋል።
https://t.me/ethiolawtips
ጠበቃ👇
+251911954039


ክስ ቀርቦብኝ ከዚህ ቀደም ጉዳዩ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ተዘግቶ ነበር የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በፍሬ ነገር ክርክር ላይ በእርቅ ስምምነት መዝገቡ ስለመዘጋቱ መከራከሪያ እስከተነሳ ድረስ ፍ/ቤቱ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ወስዶ በቅድሚያ እልባት ሊሰጠው የሚገባ እና ፍ/ቤቱ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አስቀድሞ ሊመለከተው የሚገባ ስለመሆኑ የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 222041 ጥቅምት 15 ቀን 2015 የተሰጠ አስገዳጅ የህግ ትርጉም👇
https://t.me/ethiolawtips


የሰበር ችሎት በ ሰ/መ/ቁ. 213123 በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም፡
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 መሰረት ተከራካሪዎች ካቀረቧቸው ማስረጃዎች በተጨማሪ ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ የማስቀረብ ስልጣን እና ኃላፊነት እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡ ሕጉ ኮመን ሎው (common law) እና ኮንቲኔንታል ሎው (continental law) የሕግ ሥርዓት የሚከተሉ ሀገሮችን አጣምሮ የያዘ እና ከኮመን ሎው የህግ ሥርዓት ከሚከተሉ ሀገሮች በተለየ ለዳኛው ጉዳዩንና ግራቀኙ የሚያቀርቡትን ማስረጃ ከማዳመጥ ያለፈ ተግባር እንደሰጠው ያሳያል፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት #በአደራ መስጠትን በተመለከተ #በጽሑፍ_መሆን_አለበት የሚል ህጉ #ግዴታ_የማይጥል ስለመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 240242 በቀን 29/09/2016 ዓ/ም አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ውሳኔ👇
https://t.me/ethiolawtips




ኑዛዜ በውል አዋዋይ ፊት የተደረገ ቢሆንም ኑዛዜው ላይ " ኑዛዜው #እንደተነበበ" ካልገለፀ ፈራሽ ነው

"ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰው ፊት ቢደረግም ስለ መነበቡ በኑዛዜው ላይ ካልተገለጸ ወይም ስለ መነበቡ አመላካች ቃል ወይም ሐረግ ከሌለ ህጋዊ ውጤት የለውም።
ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰዉ ሥራዉን በሚያካሄድበት ክፍል ዉስጥ መደረጉ ኑዛዜዉ በተናዛዡና በምስክሮች ፊት መነበብና ይህም ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ላይ መገለጽ እንዳለበት በአስገዳጅነት የተደነገገዉን ሊሟላ እንደሚገባዉ እንጂ የኑዛዜዉ መነበብ ጉዳይ ቀሪ የሚያደርገዉ አይሆንም፡፡ሲል የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ. 210987 መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ነው።
እንዲሁም በሰ/መ/ቁ. 70057 (ቅጽ 13) ላይ ባሳለፈዉ አስገዳጅ ዉሳኔ ኑዛዜዉ ላይ #እንደተነበበ ካልገለጸ አልያም ኑዛዜዉ #እንደተነበበ አመላካች ቃል ካልተቀመጠ ኑዛዜዉ ፈራሽ መሆኑን መወሰኑን ይታወሳል።
Join👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips



7 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.