ሠላም ሠላም ...
ከሁሉ አስቀድሜ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ ... ከረጅም ጊዜ በኋላ በመምጣታችን ...
በዚህ ቻናል ፈጣንና ትክክለኛ የስራ ማስታወቂያዎችን ስንለቅ እንደነበር ይታወሳል ...
ነገር ግን ለረጅም ጊዜ የስራ ማስታወቂያ ሳናወጣ ቆየን ... ማስታወቂያም ማውጣት ያልቻልነው እኔ ባጋጠመኝ ህመምና ሌሎች ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ነበር ... ለዚህም በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ ።
አንተ ማነህ ካላችሁም .. እኔ ግሩም እባላለሁ ... የኢትዮፔጅ መስራችና አድሚን በመሆን ሳገለግል ነበር ...
አሁን እግዚአብሄር ይመስገን ጤናዬ ተመልሷል አንዳንድ ነገሮችም በጥቂቱም ቢሆን እየተስተካከሉ ነው ... በዚህ ጊዜ ሁሉ ከእኛ ጋር ለነበራችሁ ምስጋናችን ትልቅ ነው ::
ጠፍተን በነበረ ጊዜ ውስጥ ግን ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል ..
በፊት እንደምናደርገው በጋዜጣና የተለያዩ ቦታዎች የሚወጡ የስራ ማስታወቂያዎች ላይ በመሳተፍ ብቻ "የተሻለ" ኑሮ መኖር እየተቻለ አይደለም።
ለዚህም ጊዜው የሚጠይቀውን አገልግሎት ለመስጠት እያሰብን ነው ። ከነዚህም ውስጥ
1. የተለያዩ part time የስራ እድሎች,
2. ትክክለኛነታቸው የተረጋገጡ የኦላይን የስራ እድሎች (ይሄ 1000 ብር አስገቡ 2000 ብር ይሆንላችኋል አይነት የማጭበርበር ሥራዎችን ማጋለጥ) ,
3. የተለያዩ ሙያ ያላቸው አባላት ከሌሎች ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ የሚችሉበትን ግንኙነቶችን ማመቻቸት ፣
4. ሌሎች የስልጠና ፣ ለስራ የሚሆኑ የብደር ወይም ሌላ የፋይናንስ እድሎች ፣ ዝግጅቶች .. የመሳስሉትን ከእናንተ ጋር በመሆን መረጃዎችን ማጋራት ...
5. ......
እነዚህንና ሌሎች ... እኛ ብቻ ሣንሆን እናንተም ሁላችን በጋራ የምንሰራበትና የምንለወጥበት መረጃንና እድሎችን ማመቻቸት አስበናል .. ፈጣሪ ይርዳን ።
እናንተስ ምን ታሰባላችሁ ? ... ሀሳብ አስተያየታችሁን
@ethiopage_admin ላይ ላኩልን
ባለፈዉ በታመምኩ ጊዜ ... አንድ ነገር ተማርኩ ... ነገሮችን በጋራ መስራት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ... በዚህም መሠረት እዚህ ቻናል ዉስጥ ያላችሁ ሁላችሁን አንድ ነገር በትህትና እጠይቃለሁ ...
ከዚህ በኋላ ባለን ጊዜ አብራችሁን እንድትሆኑ ... መረጃ በማጋራት ይሁን በሌሎች መንገዶች... እንዲሁም ከሌሎች አባላት ጋር አብሮ በመስራት ለተሻለ ህይወት አብረን እንድንሰራ እጠይቃለሁ ።
መልካም ምሸት
ግሩም