Ethiopia Check


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




#FakeAccountAlert Akkaawuntii X (Tiwiitaraa) sobaa maqaa Obbo Jawaar Mahaammadiin baname irraa of yaa eegnu!

Akkaawuntiin X (Tiwiitaraa) sobaa maqaa Obbo Jawaariin baname odeeffannoowwan garagaraa qoodaa akka jiru hubanneerra.

Akkaawuntiin maqaa ‘Jawar Muhammad’ jedhufi hordoftoota 380 ol qabu kun ji’oota darban keessa odeeffannoowwan heddu maxxanseera.

Odeeffannoowwan akkaawuntichi tibbana qoode keessaa tokko immoo ergaa baga gammaddanii mootummaan Itoophiyaa dhiyeenya kana Pirezidaantii Somaalilaand ta’anii kan filaman Abdiraahmaan Mohammad Abdullaahiif dabarse ni argama.

Maxxansa kana keessatti akkaawuntichi bifa safuun ala ta’een Pirezidaantii Somaaliyaa kan ta’an Hasan Sheek Mohaammud qeeqee jira.

Obbo Jawaar gama isaaniitin akkaawuntiin kun kan isaanii akka hintaane akkaawuntii Tiwiitaraa isaanii sirrummaan isaa mirkanaa’e fi hordoftoota kuma 349 ol qaburratti beeksisaniiru.

Odeeffannoon akkaawuntii sobaa irratti qoodames akkaawuntii isaanii isa sirriirra akka hinjirre mirkaneessineerra. Akkaawuntiin X Obbo Jawaar Mahaammad inni sirriin geessituu kanaan argama: https://x.com/jawar_mohammed?s=21&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

Gama biraatiin akkaawuntiin X sobaa maqaa nama siyaasaa kanaan ALI Waxabajjii 2016 baname ji’oota muraasa darban keessatti odeeffannoowwan 390 ol qooduu isaa ilaallee jirra.

Akkaawuntiiwwan fi fuulawwan miidiyaalee hawaasaa sobaa maqaa namoota fi dhaabbilee beekamootiin banaman odeeffannoowwan sobaa fi dogongoraaf nusaaxiluu waan danda’aniif ofeeggannoo yaa taasifnu.

@EthiopiaCheck




#FactCheck የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የመኪና መገጣጠሚያ ሲያስመርቁ ያሳያል ተብሎ የተጋራው ቪዲዮ የተሳሳተ ነው

ከ7 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘UNO’ የሚል ስያሜን የሚጠቀም የቲክቶክ አካውንት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የመኪና መገጣጠሚያ ሲያስመርቁ ያሳያል ያለውን ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ቪዲዮውም በድምሩ ከ12,000 በላይ ግብረ-መልሶችን ያገኘ ሲሆን በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰው ፕሬዝደንት መንግስቱ ናቸው ብለው ያመኑ በርካታ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡም ተመልክተናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰው ፕሬዝደንት መንግስቱ አለመሆናቸውን አረጋግጧል። በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ሰው በጋና የሚገኝ አሳንቲ ብሔር ባህላዊ ንጉስ ሲሆኑ የንግስና ስማቸውም ዳግማዊ ኦቶሙፉ ናና ኦሲ ቱቱ (Otumfuo Nana Osei Tutu II) ነው።

ንጉሱ ከንግስናቸው በተጨማሪ የኩዋሜ ኑኩሩማህ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር በመሆንም ያገለግላሉ።

ከላይ የተጋራው ቪዲዮ የተቀረጸውም ዳግማዊ ኦቶሙፉ ናና ኦሲ ቱቱ ከሶስት ቀናት በፊት ዞንዳ የተባለን በጋና የሚገኝ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በጎበኙበት ወቅት ነበር። ትክክለኛውን ቪዲዮ ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:
https://vm.tiktok.com/ZMhnCy44V/

ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#FactCheck የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከሰሞኑ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” እንዳሉ ተደርጎ የተጋራው መረጃ አዲስ አይደለም

‘Somali Soldier’ የሚል ስም ያለው የኤክስ (ትዊተር) አካውንት የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ብለዋል ሲል ከሰሞኑ በተደጋጋሚ መረጃ አጋርቷል።

መረጃው የዋና ጸሃፊውን ምስል እና ንግግራቸው ያረፈበት የስክሪን ቅጂም በውስጡ ይዟል።

‘Somali Soldier’ የኤክስ አካውንት ጉቴሬዝ ይህን ንግግር መች እንደተናገሩ ወይም በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው እንዳጋሩ ምንም አልጠቀሰም።

ኢትዮጵያ ቼክ በመረጃው ዙሪያ ባደረገው ማጣራት መረጃው ንግግሩ የተደረገበትን ቀን ሳይጠቅስ አሳሳች በሆነ መልኩ መጋራቱን ተመልክቷል።

ጉቴሬዝ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ያሉት ከሰሞኑ ሳይሆን ከሁለት ዓመታት በፊት እኤአ ጥቅምት 17፤ 2022 ሲሆን ይህን ያሉትም በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ጦርነት በማስመልከት ነበር።

ዋና ጸሃፊው በወቅቱ ያጋሩት የኤክስ (ትዊተር) መልዕክትም መዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://x.com/antonioguterres/status/1582082186337202176?s=46&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

ስለዚህም ‘Somali Soldier’ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ዋና ጸሃፊው አሁን እንደተናገሩ በማስመሰል ያቀረበው መረጃ አሳሳች እና ያልተሟላ ነው።

የተሟላ መረጃ ሳያካትቱ እና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ መረጃዎች ለሀሰተኝ እና የተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ።

@EthiopiaCheck


#MondayMessage ዘረባ ፅልኣትን ናይ ሓሶት ሓበሬታን ኣብ ምቁፅፃር ግዳ ትካላት ማሕበራዊ ሚዲያ እንታይ ክመስል ይግባእ?

ኣብዚ እዋን ኣብ ማሕበራዊ ሚዲያታት ዝርአ ዝርግሐ ናይ ሓሶት ሓበሬታን ዘረባ ፅልኣትን ኣዝዩ ከም ዝወሰኸ ይፍለጥ።

ይኹን’ምበር ነዞም ነገራት ባይታ ዝህቡ ዘለው ኵባኒያታት ማሕበራዊ ሚዲያታት እኹል ናይ ምቁፅፃር ስራሕቲ ብዘይምስራሕ ይንቀፉ። እዚ ብፍላይ ኣብ ኢትዮጵያ ብሰፊሑ ይርኣይ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/the-roles-and-responsibilities-of-social-media-companies-in-countering-hate-speech-and-disinformation-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab/


የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ቲክቶክ በፈረንጆች ሁለተኛ ሩብ ዓመት በኬንያውያን ተጠቃሚዎች የተጫኑ 360,000 ይዘቶችን ማንሳቱን አስታውቋል። በተመሳሳይ 60,000 አካውንቶችንም መሰረዙን ገልጿል። ቲክቶክ ባስነበበው የሩብ ዓመት ሪፖርቱ ከተነሱት ይዘቶች አብዛኞቹ ሀሠተኛ መረጃንና ልቅ ወሲብን ያሰራጩ ናቸው ብሏል። ከተሰረዙት አካውንቶች መካከል ደግሞ 90% ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የሚጠቀሙባቸው ሆነው በመገኘታቸው መሆኑን ገልጿል። ኬኒያ ከወራት በፊት ቲክቶክ የየሩብ ዓመቱን ሪፖርት እንዲያቀርብ መጠየቋ ይታወሳል።

2. አንጋፋው የብሪቲሽ ዕለታዊ ጋዜጣ ዘ-ጋርዲያን ኤክስ የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም ማቆሙን አስታውቋል። ጋዜጣው በድረገጹ ባስነበበው መግለጫ ኤክስን አሉታዊ ይዘቶች የበረከቱበት “መርዛም” ፕላትፎርም ሲል ገልጾታል። ከጋርዲያን በተጨማሪም የስፔኑ ላ ቫንጋርዲያ ጋዜጣም ኤክስ የሀሠተኛ መረጃ አሰራጮችና የሴራ ተንታኞች የገደል ማሚቶ (echo chamber) ሆኗል የሚል ምክንያት ከሰጠ በኃላ ፕላትፎርሙን መጠቀም እንደሚያቆም ገልጿል።

3. በተመሳሳይ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን (Reporters Without Borders) ኤክስ የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ ሀሠተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል መክሰሱን አስታውቋል። ቡድኑ በፈረንሳይ ሀገር በሚገኝ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ኤክስ ከተቋሙ አንጻር የተሰራጨን ሀሠተኛ መረጃ ተደጋጋሚ ሪፖርት ቢቀርብለትም አለማንሳቱን ያትታል። ቡድኑ ክሱን ያቀረበው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ኩባንያዎች ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው ለማሳየት መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስነብቧል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-የማህበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች በጥላቻ ንግግር እና በሃሰተኛ መረጃ መቆጣጠር ላይ ያላቸው ሚና ምን መምሰል አለበት በሚለው ጉዳይ መልዕክት አስተላልፈናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2502

-ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑን ወታደራዊ ኮንቮዮች ያሳያል ተብሎ የተጋራን ፎቶ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2503

-‘’የድሮ ፎቶ’’ እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስልንም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2504

-ቴክኖሎጂን በመጠቀም ‘በሰአታትእ ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ መረጃንም ተመልክተናል: https://t.me/ethiopiacheck/2505

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck




#HealthCheck ቴክኖሎጂን በመጠቀም ‘በሰአታት' ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ አሳሳች ነው

“በሦስት ሰአታት ውስጥ የስኳር ህመምን ከነዘርማንዘሩ ማጥፋት ተችሏል” የሚል መረጃ በቲክቶክና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

እነዚህ ‘ET Smart Care’ በሚል የቲክቶክ አካውንት እየተሰራጩ የሚገኙ የህክምና መረጃዎች “የክሩስፐር ጂን ኤዲቲንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሦስት ሰአት ውስጥ የስኳር ህመምን ከነዘር ማንዘራቸው ማጥፋት ተችሏል። እውነት ነው ከነዘር ማንዘራቸው ማጥፋት ችሏል” ሲል ይደመጣል።

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/health-professionals-advised-against-misleading-information-about-diabetes-treatments-circulating-on-social-media-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%83/


#FactCheck "የድሮ ፎቶ" እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስል

'አበበ ቶላ ፈይሳ' የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ158 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ "የድሮ ፎቶ እያወጣህ እንደ አዲስ የምትለጥፍ ከሆነ..." በሚል ያሰራጨው ምስል እንዳለ ተመልክተናል።

ግለሰቡ በዚህ ልጥፉ ላይ ከትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲንሸራሸር የነበረው የፋኖ ሀይሎች አመራር የሆነው የዘመነ ካሴ ምስል "ዓመት የሞላው" መሆኑን ገልጿል።

ይህን ያሳያሉ ያላቸውን እና የፋኖ አመራሩን ፎቶ አምና፣ ማለትም እአአ በ2023 የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አጋርተውት ነበር ያላቸውን ምስሎች አያይዟል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እኛም በዚህ ዙርያ ፍተሻ አርገናል።

በዚህ ዙርያ ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የድሮ እንዲመስሉ '2023' የሚል ዓመት በፎቶሾፕ ቅንብር እንደገባባቸው ተመልክተናል። ቅንብሩ ሲሰራም የፌስቡክን ዲዛይን በማይመስል መልኩ ተጣሞ እና ከዲዛይን ውጪ ክፍተት ኖሮበት ሆኖ እንደተሰራ መመልከት ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ መረጃውን አጋርተዋል ወደተባሉት የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በመሄድ ምርመራ ያደረግን ሲሆን "የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት" ከሚለው ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ የነበረው ሌላ የፋኖ አመራሩ ምስል መሆኑን ለማየት ችለናል።

በዚህም ምክንያት 'አበበ ቶላ ፈይሳ' በተባለው ግለሰብ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና በቅንብር የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ከአውድ ውጪ ከሚቀርቡ፣ በቅንብር ከሚሰሩ እና ተጋነው ከሚሰራጩ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

7.2k 0 14 5 127

ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑን ወታደራዊ ኮንቮዮች ያሳያል ተብሎ የተጋራው ፎቶ ከሌላ ቦታ የተወሰደ ነው

ከ15,700 በላይ ተከታዮች ያሉትና ‘Demekech’ የሚል ስያሜ የሚጠቀም የኤክስ/ትዊተር አካውንት ብዛት ያላቸው ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን የሚያሳይ ፎቶ ማጋራቱን ተመልክተናል።

በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ከባህር ዳር ከተማ ተነስተው ወደ ጎንደር ያቀኑ መሆናቸውን ገልጿል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ የጎግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች መገልገያን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ፎቶ ከሩዋንዳ የተወሰደ መሆኑን አረጋግጧል።

በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ሲሆን እአአ በታህሳስ ወር 2021 ዓ.ም በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተፈጠረን ውጥረት ተከትሎ ሩዋንዳውያንና ዩጋንዳውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስፋት ሲያጋሩት ነበር።

ይህንንም የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመከተል መመልከት ይቻላል:

https://web.facebook.com/share/p/15VXLLitQP/

https://web.facebook.com/share/p/15m5CFiBCd/

በተጨማሪም በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚነበበውን የሰሌዳ ቁጥር ያነጻጸርን ሲሆን የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት የሚጠቀምበት መሆኑን አይተናል።

ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ፎቶዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#EthiopiaCheck የሰኞ መልዕክት

የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ድርጅቶች በጥላቻ ንግግር እና በሃሰተኛ መረጃ መቆጣጠር ላይ ያላቸው ሚና ምን መምሰል አለበት?

የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበዛ መቷል፡፡ ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች የሚወጡባቸው የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች በቂ የሚባል የመቆጣጠር (moderating) ስራ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰሩ አይታዩም።

እነዚህ ድርጅቶች በመጀመሪያ የተመሰረቱ ጊዜ በሚዲያቸው ላይ ለሚወጡ ጽሁፎችም ሆነ ማንኛውም አይነት ነገሮች ተጠያቂነታቸውን ከራሳቸው ላይ አንስተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰዎች ማንኛውንም አይነት መረጃዎችንም ሆነ ዜና የሚያገኙት በነዚህ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ ብቻ እየሆነ መቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ድርጅቶችም ከብዙ ጫናዎች በኋላ በተወሰነ መልኩ በሚዲያዎቻቸው ላይ የሚወጡትን መረጃዎች አርተፊሻል ኢንተለጀንስን እና የሰው ሀይልን በመጠቀም መቆጣጠር ጀምረዋል፡፡

ሆኖም ግን የሃሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች የመብዛታቸውን ያክል እነዚህ ድርጅቶች ሃላፊነት ወስደው ሲሰሩ አይታዩም፣ በተለይ የፖለቲካ ይዘት ባላቸው ጽሁፎች ላይ፡፡ የሚያንማር መንግስት በሮህንጊያ ሙስሊሞች ላይ ያሰራጨው የሃሰተኛ መረጃ ያስነሳውን ከፍተኛ እልቂት እንደ ምሳሌነት መመልከት እንችላለን፡፡

በሃገራችንም ደግሞ በተለይ ከ2015 አ.ም ጀምሮ በሚታዩት የተለያዩ አለመግባባቶች እና ግጭቶች ጀርባ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ የሚወጡት የሃሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች ግጭቶቹን ከሚያባብሱት ውስጥ ናቸው።

የእነዚህ ሚዲያዎችን ቸልተኝነትን አስከትሎ በአለማችን ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡትን መረጃዎች በተለይም የፖለቲካ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች የሚቆጣጠሩበት መመሪያዎችን አውጥተዋል። እነዚህ መመሪያዎችን ካወጡ ሃገራት መካከል አውስትራሊያ እና ሲንጋፖር ይገኙበታል።

ኢትዮጵያም በቅርቡ ያጸደቀችው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ውስጥ ለተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ኃላፊነቶችን አስቀምጣለች።

ህጉ “ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠርና ለመግታት ጥረት ማድረግ አለበት። ድርጅቱ የጥላቻ ንግግርን ወይም የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰው በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ይህን መሰል መልዕክቶችን ወይም ንግግሮችን ከአግልግሎት አውታሩ ሊያስወግድ ይገባል” ይላል።

ነገር ግን መንግስት እንደዚህ አይነት ህጎችን/መመሪያዎችን አውጥቶ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚወጡትን መረጃዎች በሚቆጣጠሩበት ጊዜ የሰዎችን የመናገር መብትን ሲጋፉ እናያለን።

እንደ መፍትሄ ልናያቸው ከሚገቡ አስተያየቶች መካከል:

1. በእነዚህ ድርጅቶች ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡትን እያንዳንዱን መረጃዎች የሚከታተሉ ሰዎች (content moderators) በብዛት መቅጠር ያስፈልጋቸዋል። አሁን ከሚጠቀሟቸው ከነሱ ውጪ ያሉ ድርጅቶች (outsourced companies) ይልቅ በየሃገሩ ሰዎችን መቅጠር አለባችው። እነዚህም የሚቀጠሩት ሰዎች የሃገሩን ባህል እና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች መሆን ይኖርባቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ከ7 ሚሊየን ሰዎች በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚ ባለባት ሀገር እና በብዙ ቋንቋዎች በሚጻፍባት ሃገር ላይ በብዛት መረጃዎችን የሚከታተሉ ሰዎች (content moderators) መቀጠር አለባቸው።

2.  እነዚህ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ደግሞ ቢያንስ በመረጃ የተረጋገጡ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከአውታራቸው ማውረድ ይኖርባቸዋል።

3. እንዲሁም ትክክለኛ ገፆችን ማረጋገጥ (verify ማድረግ) እና ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን የመዝጋት ሀላፊነታቸውንም ሊወጡ ይገባል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck




የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባነት በተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ትልቅ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል። የቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ከከተማው ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተማሪዎች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ለውጤት ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያት በመሆኑን አስታወቀዋል። ሃላፊው “በተለይም ቲክቶክ ቶታሊ ልጆችን ቀምቶናል” በማለት የተናገሩ ሲሆን “እነዚህን ሶሻል ሚዲያዎችን ባን ካላደረግን (ካልዘጋን ተማሪዎችን) አስተምረን ዳር እናደርሳልን ከባድ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

2. ዋትስአፕ የሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች (reverse image search) አገልግሎትን በሙከራ ደረጃ መጀመሩን የቴክኖሎጅ ዘገባዎችን የሚሰራው ቴክራዳር በሳምንቱ አጋማሽ አስነብቧል። የሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በዋትስአፕ የሚመለከቱትን ፎቶ ትክክለኛነት በቀላሉ ለማወቅ ይረዳቸዋል ተብሏል። አገልግሎቱን ለማግኘት ፎቶውን መከፈት ቀጥሎም ቁልቁል የተደረደሩትን ሶስት ነጥቦችን መንካት ከዚያም ሰርች ኦን ዌብ (search on web) የሚለውን አማራጭ ብቻ መንካት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

3. ካናዳ የቲክቶክ ቢሮዎችን መዝጋቷን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይሁን እንጅ ካናዳዊያን የቲክቶክ መተግበሪያን መጠቀም መቀጠል ይችላሉ ተብሏል። ካናዳ እርምጃውን የወሰደችው ከብሔራዊ ደህነንት ስጋት ጋር በተገናኘ መሆኑ ተገጿል። ቲክቶክ ውሳኔውን የተቃወመ ሲሆን ወደ ፍርድ ቤት ሂጀ እሟገታለሁ ብሏል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች ሊንኮች:

- አልጎሪዝሞች እንዴት የመረጃ አጠቃቀማችንን መልክ እንደሚያስይዙ በሰኞ መልእክታችን በትግርኛ ቋንቋ አቅርበናል: https://tig.ethiopiacheck.org/home/tackling-echo-chambers-and-filter-bubbles-how-algorithms-shape-our-social-media-news-feeds-%e1%88%93%e1%89%a0%e1%88%ac%e1%89%b3/

-ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ መወሰኑን በመግለጽ የተሰራጨን ‘ደብዳቤ’ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2497

-በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የሚዲያ ዳሰሳ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2498

- ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው የተባለ ግለሰብ ያሰራጫውን ምስልም ፈትሸናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2499

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#FactCheck ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው የተባለ ግለሰብ ያሰራጨው ሀሰተኛ ምስል

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ዛሬ የሰራውን ዘገባ በማንሳት "ስትዋሹም እየተናበባችሁ" በማለት ግለሰቡ መረጃ ማጋራቱን ተመልክተናል።

ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዜናው የተጠቀመበት ምስል በትግራይ ጦርነት ወቅት ትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመበት መሆኑን በመጥቀስ ይህን ያሳያል ያለውን ምስል ከቢቢሲ ዘገባ ጋር በማመሳከር አቅርቧል።

"ውሸትን እንደትግል መሳሪያ መጠቀም የነበረ፣ ያለና የሚኖር ሃቅ ነው። ነገርግን ፕሮፓጋንዳ ሳይንስ እና የላቀ ጥበብ የሚሻ እንጂ  ተዘርፍጠ'ው የሚሰሩት ቀላል ስራ አይደለም" ያለው ረዳት ፕሮፌሰሩ አክሎም "በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ከሁለት ዓመት በፊት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የዋለን ምስል ተጠቅሞ ፕሮፓጋንዳ መስራት አንድም ፕሮፓጋንዳን መናቅ ሁለትም ጅላንፎ'ነት ስለሆነ ማስተካከያ ልታደርጉና ተናባችሁ ልትዋሹ ይገባል" በማለት 77 ሺህ ገደማ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፁ ላይ መረጃ አጋርቷል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ ማጣራት ያደረገ ሲሆን ግለሰቡ ያሰራጨው ምስል በቅንብር የቀረበ እና ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ችለናል።

ትግራይ ቴሌቭዥን በወቅቱ፣ ማለትም ኦክቶበር 24/2022 ባወጣው ዘገባው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት የተጠቀመውን ምስል ሳይሆን ሌላ የድሮን ጥቃትን ያሳያል የተባለ መሆኑን ማየት ችለናል (ምስሉ ላይ በስተቀኝ አያይዘነዋል)።

ስለዚህ ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዘገባው የቆየ የትግራይ ምስል እንደተጠቀመ አድርጎ ያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አረጋግጠናል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#MediaMonitoring ኣብ ትግራይ ዝርከቡ ተመዛበልቲ መሊኦም ናብ መረበቶም ተመሊሶም ድዮም?

ብቀዳም ቤት ፅሕፈት ኣመሪካ ብምኽንያት ካልኣይ ዓመት ኣብ መንጎ ህወሓትን መንግስቲ ኢትዮጵያን ኣብ ፕሪቶሪያ ዝተፈረመ ውዕሊ ዘላቒ ምቁራፅ ተፃብኦታት ኣብ ዘውፅኦ መግለፂ ክሳብ ሕዚ ንዝተርኣዩ ምዕባለታት ከም ዝንእድ ጠቒሱ ነይሩ።

ምስዚ ብዝተሓሓዝ ኣብ ትግራይ ተዅሲ ደው ምባሉ ዝያዳ ክንእድ ከሎ “ተመዛበልቲ ናብ ገዝኦም ተመሊሶምን መሰረታዊ ኣገልግሎታት ናብ ንቡር ተመሊሶምን’ዮም” ክብል እቲ መግለፂ ሓቢሩ።

ተወሳኺ ሓበሬታ ንምንባብ ነዚ መላግቦ ሰዓቡ: https://tig.ethiopiacheck.org/home/media-monitoring-about-the-recent-controversy-regarding-idps-in-tigray-region-%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad/


#FactCheck ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ መወሰኑን የሚገልጽ ‘ደብዳቤ’ ሀሰተኛ ነው

ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩ እንደተወሰነ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

በቀን 18/2/2017 እንደተጻፈ ተደርጎ እየተጋራ የሚገኘው ይህ ደብዳቤ የትምህርት ሚኒስቴር አርማ እና የሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) “ፊርማ” አርፎበታል።

ደብዳቤው በመንግስት ይሰጥ የነበረው አቅም ማሻሻያ ፕሮግራም በበጀት እጥረት ምክንያት መቋረጡን እና ለፕሮግራሙ ያለፉ ተማሪዎች በግል እንዲማሩና የመንግስት ከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ነጥብ ሲያመጡ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ያትታል።

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት እንዲያጣራ ከተከታዮቹ ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን ጉዳዩን በተመለከተ መረጃ አግኝቷል።

በዚሁ መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር እና የሚንስትሩን ስም እና “ፊርማ” ይዞ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ከት/ት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የትምህርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) “ሀሰተኛ መረጃ ነው” በማለት ደብዳቤው ትክክለኛ አለመሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በደብዳቤው ላይ አጠራጣሪ የሆኑ የአፃፃፍ ሁኔታዎችን የተመለከትን ሲሆን በፎቶፎረንሲክስ መስል መመርመሪያ መሳሪያ ባደረግነው ማጣራትም ደብዳቤው ተመሳስሎ የተሰራ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን ተመልክተናል።

ተመሳስለው የሚሰሩ ሀሰተኛ ደብዳቤዎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣ ሲሆን ታማኝ ባልሆኑ ምንጮች የሚሰራጩ መሰል ደብዳቤዎችን አምነን ከመቀበላችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#MediaMonitoring የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር እንደተከለከለ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነ አየር መንገዱ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናገረ

በርካታ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማልያ ኦንላይን ሚድያዎች ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሉን እየዘገቡ ይገኛሉ።

እንደ 'Eritrean Press' ያሉ እነዚህ ሚድያዎች ለዚህ ክስተት አስረጂ ነው ያሉትን ማስረጃ ባያቀርቡም ጉዳዩ አየር መንገዱ በቅርቡ ወደ ኤርትራ እንዳይበር ከመታገዱ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አመላክተዋል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራርያ ጠይቋል።

"አየር መንገዳችን አሁንም በኤርትራ አየር ክልል እየበረረ ነው፣ መረጃው የተሳሳተ ነው" ብለው አንድ ከፍተኛ የአየር መንገዱ ሀላፊ መረጃ ሰጥተውናል።

"በኤርትራ አየር ክልል ለመብረር አሁንም ፈቃድ አለን፣ ይህ ፍቃድ እንደተነሳ ምንም አይነት ከኤርትራ አልደረሰንም" ብለው ያስረዱት ሀላፊው ከበፊቱ የተቀየረ ነገር እንደሌለ ጠቁመዋል።

ይሁንና Flight Radar 24 የተባለው የበረራ መከታተያ ድረ-ገፅ እና መተግበርያ አንዳንድ አውሮፕላን የኤርትራን አየር ክልል በመተው በሱዳን በኩል እየበረሩ እንደሆነ በ X ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ይሁንና በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አየር መንገዱ አሁንም በረራውን በኤርትራ የአየር ክልል እያደረገ እንደሆነ የሚያሳዩ የስክሪን ቅጂዎችን እያጋሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


#FactCheck ጠ/ሚር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት መዳረሻነት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ስለመሆኗ ስላነሱት ሀሳብ ጥናቶች ምን ይላሉ?

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዛሬው የፓርላማ ውሏቸው ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መሀል ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ነበር።

"በአፍሪካ ውስጥ የፈለገው ያህል የሚድያ ፕሮፖጋንዳው ቢስፋፋም ኢትዮጵያን የሚያክል ለኢንቨስትመንት ምቹ የሚባል ሀገር እምብዛም የለም" በማለት የተናገሩት ይህም ከመሬት አጠቃቀም፣ የኢነርጂ አቅርቦት እንዲሁም ዝቅተኛ የብልሹ አሰራር/ጉቦኝነት መኖርን አንስተዋል።

በዚህ ዙርያ በአፍሪካ በየአመቱ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሆኑ መዳረሻዎችን በማውጣት የሚታወቀው ግዙፉ RMB ግሩፕ ያወጣውን ጥናት እንመልከት።

የዘንድሮው (እአአ የ2024) የተቋሙ ጥናት እንደሚያሳየው ሲሸልስ ቀዳሚዋ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር ስትሆን በምክንያትነት የተቀመጠው ሳቢ የኢንቨስትመንት አሰራር፣ የህዝብ እድገት እና የተረጋጋ ኢኮኖሚ ናቸው።

በሁለተኝነት የተቀመጠችው ሞሪሺየስ ስትሆን ሀገሪቱ ደግሞ በፈጠራ፣ በኢኖሚ ነፃነት፣ በጥሩ መልኩ በሚመራ የኢንቨስትመንት ሴክተር እና ከፍ ባለ የነፍስ ወከፍ ገቢ ተመራጭ ሆናለች።

ከሶስት እስከ አምስት ያለውን ቦታ የያዙት ደግሞ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ናቸው።

RMB የግዙፉ የደቡብ አፍሪካው ፈርስት ራንድ ግሩፕ የኮርፖሬት እና ኢንቨስትመንት ባንኪንግ (CIB) ቅርንጫፍ ሲሆን ሪፖርቱን በዚህ ሊንክ መመልከት ይቻላል: https://www.rmb.co.za/where-to-invest-in-africa-2024

በዚህ ዙርያ አለም አቀፍ ሚድያዎች ዘገባዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን የፋይናንስ ዜናዎችን በማውጣት የሚታወቀው ብሉምበርግ የሰራውን ዜናም መመልከት ይቻላል: https://www.bloomberg.com/news/articles/2024-08-06/island-nations-top-egypt-as-best-african-investment-destinations?embedded-checkout=true

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

6.8k 0 17 10 93


20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.