EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Tibbiyot


ETHIOPIAN FOOD AND DRUG AUTHORITY /EFDA/
This is EFDA'S official Telegram Channel
For more updates please visit
Free call 8482
join the Channel
t.me/ethiopianfoodanddrugauthority

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ሴቶችን ወደ አመራርነት የማምጣት አስፈላጊነት ዙሪያ የህይወት ልምድ ተሞክሮ ቀረበ፡፡

አዲስ አበባ፣መጋቢት 2017 ማርች8 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ለመጎብኘት ወደ ተቋሙ ለመጡ የፌዴራልና የክልል የጤና ቢሮ ሴት አመራሮች የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ የጤናው ሴክተር ከሴቶችና ወጣቶች ጋር የተያያዘ ብዙ ስራዎች እንዳሉት በመግለፅ በጤናው ሴክተር ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት እየተሰራ ያለውን ስራ አድንቀው በተለያየ ዘርፍ በአመራርነት ላይ ለሚገኙ ሴቶች የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
ተምረን ለሀገራችን ካልጠቀምን ዋጋ የለውም በሚል የህይወት ልምዳቸውን ማካፈል የጀመሩት ከጤና ባለሙያ ቤተሰብ የተገኙት ሔራን ገርባ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ የጀመረው ህይወታቸው እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፋርማሲ ትምህርት ቤት አለፍ ሲልም በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒት ጥራት ምርመራ ባለሙያ፣ የመድኃኒት ምዝገባና ፈቃድ ባለሙያ፣ የመድኃኒት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና አሁን እየሰሩበት እስከ ሚገኙበት የዋና ዳይሬክተርነት ስልጣን ድረስ ያለፉባቸውን የህይወት መንገዶች ለሌሎች ሴት አመራሮች ትምህርት በሚሆን መንገድ ቀርቧል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የተቋሙን መዋቅርና ራዕይ ከማስተካከል ጀምሮ አገልግሎት አሰጣጡ ዲጂታላይዝድ የተደረገ ሲሆን ጠንካራ የትንባሆ ህግ እንዲወጣ ከማረግ በተጨማሪ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ሁለት ዓለም አቀፋዊና አንድ በሀገር ውስጥ መሸለማቸው ይታወሳል፡፡የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር በአፍሪካ የልቀት መአከል ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ ሲሆን በቃሊቲ ክ/ከተማ እየተገነባ ያለው የልህቀት ማዕከል ጥሩ ማሳያ ነው፡፡


ከፌደራል እስከ ክልል ያለው የትምባሆ ቁጥጥር ሪፖርት ቅብብሎሽ እና እርምጃ አወሳሰድ ሊጠናከር እንደሚገባው ተገለፀ፡፡
መጋቢት 2/ 2017 ዓ.ም አዳማ በተካሄደው የፌደራልና የክልሎች የትምባሆ ቁጥጥር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሲከፍቱ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ምንም እንኳን እንደ አገር በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ አበረታች ውጤቶች ቢገኙም ከፌደራል እስከ ክልል ያለው የትምባሆ ቁጥጥር ሪፖርት ቅብብሎሽ እና እርምጃ የሚጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ መጠናከር አለበት፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የትምባሆ ቁጥጥርን የማስተባበርና የማስተዳደር ኃላፊነት በአዋጅ ለባለስልጣ መስሪያ ቤቱ መሰጠቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ የትምባሆ ክልከላ ሕጉን በመፈፀም ላይ ያሉት የክልል ተቆጣጣሪ አካላት በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የሚሠሯቸውን ስራዎች በሙሉ ለባለስልጣኑ ሪፖርት በማድረግ ረገድ ያለውን ክፍተት በመገንዘብ ወደ እያንዳንዱ ክልል ወርደው ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሙያዎች እንዲመደቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የሚያደርገው የሁለት ቀናት ግምግማ ዓላማ እስካሁ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የተገኙ ጠንካራ ልምዶችን በመቀመር ወደ ሌሎች ለማስፋትና ድክመቶችን ነቅሶ በማውጣት ለማረም እንዲሁም በቀጣይ ተጠናክረው ሊሰሩ የሚገባቸው የቁጥጥር ስራዎችን ለይቶ በማውጣት አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የተሠሩ ስራዎች የዕቅድ አፈፃጸም ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡


Here you can find the Ethiopian Essential Medicine List ,7th Edition

http://www.efda.gov.et/publication/ethiopian-essential-medicines-list-oct-2024/


የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን 7ኛውን መሰረታዊ የመድኃኒት መዘርዝር ይፋ አደረገ

መጋቢት 2/2017 አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን 7ኛውን የኢትዮጵያ መሰረታዊ መድሃኒቶች መዘርዝር ይፋ አድርጓል።

የመድኃኒት መዘርዝሩን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የመድኃኒት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ እንደተናገሩት የተሻሻለው የመድኃኒት መዘርዝር ከዓለም ጤና ድርጅት የቅርብ ጊዜ ሞዴል መዘርዝር ጋር የተጣጣመ መሆኑን  በመግለፅ የ7ተኛው የመሰረታዊ መድኃኒቶች መዘርዝር ይፋ መደረግ ህዝባችን የሚጠቀማቸው መድኃኒቶች ከፍተኛ ጥራት እንዲኖራቸው እና አግባባዊ የመድሃኒት አጠቃቀምን ለማስፈን ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል.

የአለም ጤና ድርጅትን በመወከል የተገኙት ዶ/ር ቤጆይ ናሚባር እንደተናገሩት ኢትዮጵያ መሰረታዊ የመድኃኒት መዘርዝሯን ለማሻሻል የምታደርገውን ተከታታይ ጥረት አድንቀው የዓለም ጤና ድርጅት የመድኃኒት አስተዳደርን ለማጠናከር፣ የመድኃኒት ተደራሽነትን ለማሻሻል እና እንደ AMR ያሉ የጤና ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ዶ/ር ሸምሱ ኡመር ከባለስልጣኑ በ7ኛው እትም ላይ የተደረጉ ለውጦችን በተመለከተ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኙት አቶ ግርማ ተክሌ በ6ኛው እትም ዙሪያ ባቀረቡት ጥናት በመዘርዝሩ ላይ የነበሩ ክፍተቶችና መሻሻል የሚሹ አካባቢዎችን ለይተው አስረድተዋል፡፡


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish










የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለቁጥጥር ስራው የሚያግዙ ግብዓቶች ተረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብ ቁጥጥሩን ሊያግዙ የሚችሉ ግብዓቶች ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት SNV Netherlands Development Organization ተረክቧል፡፡ ወተት ጥራቱና ደህንነቱ ተጠብቆ መመረቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉትን ላክቶስ ስካነሮችና ዲፕ ፍሪዘር ከልማት ድርጅቱ ፕሮጀክት ማኔጀር ሚስተር ማርኮ ስትሬንግ የተረከቡት የባለስልጣኑ የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንደተናገሩት የልማት ድርጅቱ ለባለስልጣን መስሪያ ቤታችን የሠጣቸው የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች የወተት ጥራትና ደህንነትን ለማስጠበቅ እየተሰራ ላለው ስራ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልፀው የልማት ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡













16 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.