EthioTube


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።
Follow us on other our social media networks:
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በአፍሪካ አህጉር ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ላይ አተኩሮ በጋና አክራ በተካሄደው አመታዊው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” ላይ አፍሪካን በአየር ትራንስፖርት በማገናኘት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተጫወተ ላለው ሚና ላሳዩት የላቀ የአመራርነት ሚና የ “Leadership in Connecting Africa through Transport Award” ተሸላሚ ሆነዋል።
ይህ ሽልማት አፍሪካን እርስ በርስ በማገናኘት ቁርጠኛ የአመራርነት አስተዋፅዖ ላበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና የሚሰጥበት ሲሆን የዘንድሮው የ “2025 የአፍሪካ ፕሮስፔሪቲ ዲያሎግ” የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የታላላቅ አህጉር ዓቀፍ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በተገኙበት በጋና አክራ ተካሂዷል።

ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ:
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-group-ceo-honored-with-prestigious-leadership-in-connecting-africa-through-transport-award?fbclid=IwY2xjawIT04hleHRuA2FlbQIxMAABHVCok0vNq89NsFuUO9Ta4Vq_pp8oCZYCexS4Wwdhd55Ki_GLNqLPxJTZtw_aem_zG3snWW8DerWNkjQ0F7XRA

#የኢትዮጵያአየርመንገድ


በኤፍኤ ዋንጫ ማንችስተር ዩናይትድ ደካማውን ሌስተር ሲቲ በሜዳው ኦልድ ተራፎርድ በስንት መከራ 2ለ1 በማሸነፍ ወደ ሚቀጥለው ዙር ማለፍ ችሏል።

በሌላ በኩል ከትናት ወዲያ አርሰናል በኒውካስትል ተሸንፎ ከውድድሩ መሰናበቱ ይታወሳል።

ዘንድሮ የኤፍኤ ዋንጫን ማን ያነሳዋል? 🤔

#PremierLeague #ManchesterUnited #LeicesterCity #Arsenal #Newcastle


ኢቢሲ ሰለ “ፍቅር እስከ መቃብር”

ለፍትሕ መከበር ሲባል በብዙ የጠበቃችሁን ተመልካቾቻችን፣ ሕግ አክብረን ፍትሕ ያገኘን በመሆኑ “ፍቅር እስከ መቃብር”ን በቅርቡ ይዘን እንመለሳለን!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) “ፍቅር እስከ መቃብር” የተሰኘውን ድርሰት ወደ ፊልም ቀይሮ ከመሥራት ጋር በተያያዘ በፍርድ ቤት የቀረበበትን ክስ በሕግ አግባብ ተከራክሮ ረትቷል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት "ፍቅር እስከ መቃብር"ን አስመልክቶ በኢቢሲ በኩል እንዲሁም በከሳሽ በኩል የቀረበውን የሰነድ ማስረጃ መርምሮ የከሳሽ ጥያቄን ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ማደረጉን እና ከዛሬ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተሰጥቶ የነበረው እግድ መነሣቱን በመጥቀስ ውሳኔ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት የሰጠው ውሳኔ ኢቢሲ ከመነሻውም የ“ፍቅር እስከ መቃብር” ባለቤትነት መብቱን የገዛው ሕጋዊ መንገዱን ተከትሎ መሆኑን እንዲሁም የመጽሐፉ ደራሲ ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ በሕይወት እያሉ መብቱን በሽያጭ ያስተላለፉት ስለመሆኑ እና ኢቢሲ የ“ፍቅር እስከ መቃብር” ድርሰትን ወደ ፊልም ለመቀየር ሕጋዊ መብት ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የሕግ ጉዳዩን የተከታተሉት በኢቢሲ የሕግ ነክ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ዳግማዊ ገልጸዋል።

ኢቢሲ በሕግ የተቋቋመ ሀገራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሲወጣ የኖረ እና ያለ፤ የደራሲውን ሥራ በወጋየሁ ንጋቱ ትረካ ከፍ ያደረገ እና በዚህም በይፋ ደራሲው ያመሰገኑት ተቋም ነው።

አሁንም የተደረገው ያንኑ ሌጋሲ የሚያስቀጥል፣ የደራሲውን ሕልም የሚፈታ እና በሕጋዊ እና እውቅና ባለው ይሁንታቸው የተላለፈውን መብት መነሻ በማድረግ የሠራን በመሆኑ ፊልሙን በቅርቡ ለዕይታ የምናበቃ መሆኑን እንገልጻለን።





5 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.