#ይነበብ ‼
#ExitExam#Important_Message የመውጫ ፈተና ነገ ሰኞ ጥር 26/2017 ዓ/ም ጀምሮ እነደሚሰጥ ይታወቃል። በዚህ ፈተና ወቅት
ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል?👉ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው። (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)
👉ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው
👉ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።
👉ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።
👉ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።
👉ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።
👉በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገርም ሆነ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።
👉ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።
👉ተፈታኞች በምንም አይነት ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።
👉ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ደንብና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ይሄንን መረጃው Exit ለሚፈተኑ ጓደኞቻችሁ (Department Telegram Group ላይ) Forward አድርጉላቸው!ለወቅታዊ መረጃ ይቀላቀሉን
👉ቴሌግራም ቻናላችን: @ExitExamPrep
👉ቴሌግራም ግሩፓችን: @ExitExamSquad