FBC (Fana Broadcasting Corporate)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ሊቨርፑል ቦርንማውዝን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊቨርፑል ወደ ቫይታሊቲ ስታዲየም በማቅናት ቦርንመዋዝን 2 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን ማጠናከር ችሏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ለሊቨርፑል ግቦቹን ሞሃመድ ሳላህ በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ማስቆጠር ችሏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ኤቨርተን ፉልሃም ኒውካስል ዩናይትድን 2 ለ 1 እንዲሁም ሳውዝአምፕተን ኢፕስዊች ታውንን 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡

ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት ከግማሽ ደርዘን በላይ ግብ በማስቆጠር ብራይተንን 7 ለ 0 አሸንፏል፡፡

መረሃ ግብሩ ሲቀጥል ምሽት 2 ከ30 ዎልቭስ ከአስቶንቪላ ይጫወታሉ፡፡


የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡ የወዳጅ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ተወካዮች የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚዬም ጉብኝት በምስል፡-


ሩሲያ በዩክሬን የሃይል መሰረተ ልማት ላይ የተሳካ የአየር ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ በዩክሬን የጋዝ መሰረተ ልማቶች ላይ የተሳካ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የአየር ላይ ጥቃቱ ለዩክሬን መከላከያ ሰራዊት ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትን ዒላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡ በተፈጸመው ጥቃት እስካሁን 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን÷በርካቶች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ግዛቶች…

https://www.fanabc.com/archives/281215


አየር ኃይል ለገነባው ከፍተኛ ወታደራዊ የዝግጁነት አቅም የሙያተኛው ሚና ጉልህ ነው – ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አየር ኃይል አሁን ለገነባው ከፍተኛ ወታደራዊ የዝግጁነት አቅም የሙያተኛው ድርሻ ጉልህ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ገለጹ። የኢፌዲሪ አየር ሃይል ሎጂስቲክስ የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር በአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ተካሂዷል፡፡ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የአየር ኃይል ሎጀስቲክስ…

https://www.fanabc.com/archives/281211


የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡ የወዳጅ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ተወካዮች የአንድነት ፓርክ ጉብኝት በምስል፡-


ማስታወቂያ


የዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ላዕላይ ም/ቤት አባል አንድሬይ ክሊሞቭ በብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ ያደረጉት ንግግር …

የሩሲያን ገዥ ፓርቲ የዩናይትድ ራሺያ ፕሬዚዳንት፣ የሩሲያ ፌደሬሽን የጸጥታ ም/ቤት ምክትል ሃላፊ ድሚትሪ ሜድቬዴቭን ደብዳቤ (መልዕክት) ሳቀርብላችሁ ከፍ ያለ ክብርና ኩራት ይሰማኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔን በማስመልከት ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ልገልጽልዎ እዎዳለሁ። በዚህ ጉባዔ በሚኖረው ውይይት ለኢትዮጵያ መጻኢ ዕድገት ፈጣንና ጠንካራ መሰረት እንደሚጥል እና…

https://www.fanabc.com/archives/281208


በኢትዮጵያ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የኢኮኖሚ ለውጥ አይቻለሁ – አምባሳደር ሰልማ መሊካ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የኢኮኖሚ ለውጥ እንቅስቃሴን አይቻለሁ ሲሉ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር ሰልማ መሊካ ሀዳዲ ገለጹ። አምባሳደሯ ከፋና ዲጂታል ጋር በነበራቸው ቀይታ÷በመሠረተ ልማት ረገድ በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ ላይ ትልቅና አዎንታዊ ለውጥ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሩም በተቋማት ሪፎርም፣ በባንኮች፣ በቱሪዝም፣ ኤክስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች ላይ…

https://www.fanabc.com/archives/281205


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
‘ከቃል እስከ ባህል’


456 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 456 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሊባኖስ ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን÷በሳምንቱ 157 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በተመሳሳይ 289 ወንዶች፣ 9 ሴቶች እና አንድ ጨቅላ ሕጻን በድምሩ 299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

10 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.