Postlar filtri


ቤተልሄም አዳሙ የወይዘሪት አገው የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ሆነች።

ወይዘሪት አገው የቁንጅና ውድድር በ85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ዛሬ ተካሂዷል። 11 የአገው ቆነጃጅቶች ተወዳድረዋል።

የተደረገውን ብርቱ ፉክክር በማለፍም ቤተልሄም አዳሙ የዓመቱ የአገው ቆንጆ ኾና ተመርጣለች። ለቀጣዩ አንድ ዓመት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የባሕል አምባሳደር በመኾን ታገለግላለች።


አሁን በቦሌ ቡልቡላ የወረዳ 12 አስተዳደር አከባቢ የደረሰ የእሳት አደጋ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የፋስት መረጃ ተከታታዮች ከስፍራው ያደረሱን መረጃ ያሳያል።
#FastMereja


ግጭት እንዳይነሳ የሰጉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገንዘባቸው ከባንክ ማውጣት እና ሸቀጦች መግዛት ላይ ተጠምደዋል።

#FastMereja I የወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ ተከትሎ ደግሞ ግጭት እንዳይነሳ የሰጉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገንዘባቸው ከባንክ ማውጣት እና ሸቀጦች መግዛት ላይ ተጠምደዋል።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት ሰራተኞች እንደሰማነው በማለት ዶቼ ቬለ እንደዘገበው ከወታደራዊ አመራሮቹ ውሳኔ በኃላ በነበሩ ሶስት ቀናት ብቻ ከግማሽ ቢልዮን በላይ ብር ከባንኩ ቅርንጫፎች በደንበኞች ወጪ ተደርጓል።

በገበያዎች በተለይም የምግብ ነክ ሸቀጦች የሚገዛ በዝቷል፥ የተወሰነ የዋጋ ጭማሪም ይስተዋላል። በሌላ በኩል በበርካታ ነዳጅ ማደያዎች በተለይም ቤንዚን የሌለ ሲሆን በጥቁር ገበያ ከ270 እስከ 300 ብር አካባቢ ይሸጣል። ይህንኑ ተከትሎ የትራንስፖርት ዋጋም ተወዷል ሲል ዶቼ ቬለ አስነብቧል።




🚨 አሜሪካ ለሚኖሩ (ተጨማሪ) መረጃ፡ የእጮኛ ቪዛና የስደተኞች አፈሳና መመለስ 🚨
በጋዜጠኛ አበበ ፈለቀ

ትላንት ያጋራሁትን መረጃ ተከትሎ የእጮኛ (K-1 Fiancé(e) Visa ) ቪዛ ጋ ተያይዞ በውስጥ መስመር ተጨማሪ መረጃን የጠየቁኝ የተጨነቁ ኢትዮጵያውያን አሉ። ለነሱ የሰጠሁት መልስ ለሌሎችም ስለሚጠቅም እነሆ።

የእጮኛ ቪዛ አሜሪካ መጥታችሁ በ90 ቀን ውስጥ ጋብቻ እንድትፈጽሙ የሚያስገድድ ነው። በ90 ቀን ውስጥ ተፈራርማችሁ የስራ ፍቃድ (Work Permit) እና የመኖርያ ፍቃድ (Green Card) ማመልከት ይኖርባችኋል።

በዚህም መሰረት የሚከተለው ነጥቦች መሰረታዊ ናቸው።

✅ በ90 ቀን ውስጥ ተፈራርማችሁ፣  ለመኖርያ ፈቃድ(Green Card) እና የስራ ፈቃድ (Work Permit) ካመለከታችሁ፣ እንዲሁም ምንም አይነት የወንጀል ታሪክ ከሌላችሁ ቪዛው ጊዜው ቢያልፍም የዚህ ዘመቻ ኢላማ አይደላችሁም።
✅  ጉዳዩ በሂደት ላይ ቢሆንና መኖርያ ፈቃዱና የስራ ፈቃዱ ባይመጣም እንኳን የማመልከቻችሁን (I-485 እና I-765) ደረሰኝ እና የጋብቻ ማስረጃችሁን ቅጂ ይዛችሁ መንቀሳቀስ ትችላላችሁ።
**

🔴በ90 ቀናት ውስጥ ጋብቻውን ካልፈጸማችሁ፣ ጋብቻውን ፈጽማችሁም የመኖርያ ፈቃድ ወይም የስራ ፈቃድ ማስተካከያ ማመልከቻ ያላስገባችሁ፣ የወንጀል ክስ፣ መዝገብ ወይም ታሪክ ያላችሁ ወይም የቪዛው የጊዜ ገደብ ያለፈባችሁ የዚህ አዲስ ህግ ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ።
****

ትላንት በዝርዝር የቀረቡት መረጃወችም ከላይ ከተጠቀሱት በተለይ ከእጮኛ ቪዛ ጋ ከተያያዙት መረጃወች ጋ በጋራ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። በድጋሚ ይሄ መረጃ እንደ ተጨማሪ መረጃ የሚጠቅም እንጂ ከጠበቆቻችሁ ጋ የምታደርጉትን በጉዳያችሁ ላይ ያተኮረ የምክር አገልግሎት የማይተካ መሆኑን አስታውሳለሁ።

#Ethiopia #Ethiopiandiaspora #immigration #USImmigration


የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልዑካን ቡድን ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታልን ጎበኙ

#FastMereja I ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ ሣልሳዊ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መልዕክተኛ የልዑካን ቡድን ሜትሮ ፖሊታን ማር ዩልዮስና ፋዘር ጆሲ ጃኮብ የኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታልን ዛሬ ጥር 22/2017 ዓ.ም ጎበኙ።

አቶ ብርሃን ተድላ ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ በጉብኝቱ መርሐግብር ወቅት ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ከሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር መቀራረቡ በተለይ ከፍተኛ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለማድረግ ሆስፒታሉ ያለውን ራዕይ ለማሳካት የሚረዳ ነው።

ሆስፒታሉ በቴክኖሎጂ በታገዙ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችና ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት ባለሙያዎች በመታገዝ ዜጎቻችንን ለህክምና ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪና እንግልት ለማስቀረት እና ውጭ አገር የሚያስኬዱ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት አላማው አድርጎ የተነሳ በዋናነት በአዋቂና በህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና ላይ የተሰማራ የሕክምና ተቋም ስለመኾኑ አብራርተዋል። በተጨማሪ የደረትና የሳንባ ቀዶ ጥገና ሕክምና፥ የጭንቅላትና ህብለሰረሰር ህክምና፥ የነርቭ ህክምና፥ የኩላሊት እጥበትና ህክምና፥ የአጥንት ቀዶ ሕክምና እና ጠቅላላ ህክምና ከመስጠቱ ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለልብ ሕሙማን ህፃናት ያለ ክፍያ የቀዶ ህክምና በመስጠት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ብርሃን ገልፀዋል።

በዚህም እስከአሁን ድረስ ከ60 በላይ ለሆኑ የልብ ህሙማን ሕፃናትና አዋቂ ያለክፍያ እና በእገዛ የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

የሕንድ ኦርቶዶክስ የፓትያርኩ ተወካይ በጉብኝቱ ወቅት ባዩት ኹሉ መደሰታቸውን ገልፀው በትብብር መሥራት የእነሱም ፍላጎት መሆኑን ተናግረዋል።

ህንድ አራት ሆስፒታሎች ላይ በቦርድ አባልነት እና ሊቀመንበርነት እንደሚያገለግሉ ገልፀው ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል  ከእነዚህ ተቋማት ጋር አብሮ እንዲሰራ ፣እዚህ የማይሰጡ ህክምናዎችን እሳቸው ከሚያስተባብራቿው ሆስፒታሎች ጋር አብሮ እንዲሰራ እና ድጋፍ እንዲያገኝ የበኩሌን አስተዎፇ አደርጋለሁ ብለዋል።




6 አመት የፈጀው «እንደ ጊዜው» የተሰኘው የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ አዲስ አልበም ሊወጣ ነው!!

#FastMereja I የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ «እንደ ጊዜው» የሙዚቃ አልበም የስድስት አመት ስራው ተጠናቆ የፊታችን ጥር 30/2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

አስራ ሶስት ትራኮችን ያለው “እንደ ግዜዉ" አልበም አንጋፋ እና ወጣት ባለሞያዎች ተሳትፈዉበታል በግጥምና ዜማ ይልማ ገ/አብ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አለማየሁ ደመቀ እንዲሁም ራሱ ድምፃዊ ማሚላ ሉቃስን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች አሻራቸዉን አሳርፈዉበታል፡፡

አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ፣ ካሙዙ ካሳ ፣ ሚኪ ጃኖ ፣ ስማገኘዉ ሳሙኤል ፣ ፋኑ ጊዳቦ ፣ ሱራፌል የሺጥላ እና ጊልዶ ካሳ በሙዚቃ ቅንብሩ ተሳትፈዉበታል፡፡

አልበሙ የፊታችን ጥር 30 ጀምሮ በሰዋሰዉ አፕ እና በሰዋሰዉ የዩቲዩብ ገፅ ላይ ይለቀቃል፡፡

📷 Focus Studio


የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ሊካሄድ ነው!

#FastMereja I የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከየካቲት 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል እንደሚያካሂድ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።

የዘንድሮው የአመታዊ የህክምና ኮንፈረንስ “በኢትዮጵያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ደህንነት አሁናዊ ሁኔታና አማራጭ መፍትሄዎች" በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን በኮንፈረንሱ ሐኪሞች ብቻ ሳይሆኑ እንደአጠቃላይ የጤና ባለሙያው እያጋጠመው ያለውን ማህበራዊ ጫና እና ይህ የሚያስከትለውን ሀገራዊ ቀውስ በሃገራችን ከሚገኙ እውቅ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ምክክር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 61ኛው ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከ400 በላይ የተከበሩ የህክምና ባለሙያዎችን እና ከውሳኔ ሰጪዎች በተጨማሪ ከሁሉም ክልል የሚመጡ የማህበሩ አባላት ተወካዮች፤ ከተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ማህበራት የተውጣጡ ተወካዮች የህክምና ኮሌጅ ኃላፊዎች እና የመንግስት አካላት ጨምሮ የሚያሳትፍ ጉባዔ ሲሆን ዓለም አቀፍ የጤና አዉደርእዩ ከ70 በላይ ድርጅቶች የሚሳተፉበት እንዲህ ከ12,000 በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ መድረክ ላይ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ እውቅ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት የምርምር ግኝቶችን እና የህክምና ልምዶችን በማቅረብ የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እና በየዓመቱ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የሽልማት መርሃግብር ይካሄዳል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ከተመሰረተ 1940ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፤ በታካሚዎች ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫወት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማህበር ነው።




5ኛው ፊንቴክስ የፈርኒቸር የቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ።

#FastMereja I «ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ» በሚል መሪ ቃል ፊንቴክስ FINTEX የፈርኒቸር፣ የቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጂዎች ዓለም አቀፍ አውደ-ርዕይ ከጥር 22 - ጥር 25 ቀን 2017 ዓ/ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለ5ኛ ጊዜ መካሄድ ጀመሯል፡፡

ፊንቴክስ አውድ-ርዕይ ላይ የአገር ውስጥ አምራቾችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰባሰብ ከመላ አገራችን ከሚመጡ ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከዲፕሎማቲከ ማህበረሰብ እና ከበጎ አድራጎት ተቋማት፣ በመገንባት ላይ ከሚገኙ ባንኮች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ማዕከላት፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ ከአነስተኛና ጥቃቅን በማደግ ላይ ለሚገኙ የፈርኒቸር አምራቾች እንዲሁም ወኪል ሆነው በከልል ከተሞች ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በፈርኒቸር፣ በቤተ-ውበት እና በግንባታ አጨራረስ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የሚተጉ ግዙፍ የአገር ውስጥ አምራቾች ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል መድረከ እንደሆነ ተነግሯል።

ከ4000 የሚበልጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት ከስመጥር የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር እንደሚያድርጉ ይጠበቃል።

ኤክስፖው ፕራና ኤቨንትስ እና አፍሪካን ትረስትድ ፓርትነርስ በጋራ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡


ቀሲስ በላይ መኮንን በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጡ

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወሰነ።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እንዲሁም የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን ጠቅሶ ዝርዝር ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በዚህም ተከሳሾቹ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ተከሳሾች በተለያየ መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

በዚህ መልኩ የቀረበውን ዝርዝር ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ብቻ ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ የሚጣራ መሆኑን ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።

ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የዕምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በአንደኛው ክስ ብቻ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቶ ነበር።

ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት በሐሰተኛ ሰነድ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑ በአንደኛውን ክስ ላይ መገለጹን ተከትሎ በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው በተደራራቢነት የቀረቡና ተጠቃልለው ሊያስቀጡ የሚችሉ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ፍርድ ቤቱ አብራርቶ ሁለተኛውን ክስ ውድቅ በማድረግ በአንደኛው ክስ ብቻ በከባድ አታላይነት ሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ሆኖም ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸው ተጠቅሷል።

በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።

የሀሳብ ልዩነት ያቀረቡት አንደኛው ዳኛ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የባንክ ሂሳባቸው በመገለጹ ብቻ የወንጀል ተግባሩ በስምምነት ተፈጽሟል ለማለት አያስችልም የሚል የሀሳብ ልዩነት እንዳላቸው ጠቅሰው ልዩነታቸውን አሳይተዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ ዐቃቤ ሕግ ወንጀሉ የተፈጸመው በትብብር መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ይዟል።

በዚህም1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን ያቀረቡትን አራት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 21 መሰረት በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ደግሞ እያንዳንዳቸው አራት፣ አራት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ በዕርከን 17 መሰረት በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

በፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የተወሰነውን የጽኑ እስራት ውሳኔን የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እጃቸው ከተያዘ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል።

ዘገባው የፋና ሚዲያ ነው




#በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ

መልአከ ብርሃናት፣ ለሚጠሩት ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት በስፋት ይገልጹታል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ይከበራል፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ዑራኤል፡፡ የስሙን ትርጓሜ ሊቃውተ ቤተክርስቲያን ሲያስቀምጡም “ዑራ” ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን “ኤል” አምላክ ማለት ነው፡፡ በዚህም ዑራኤል ማለት የአምላክ ብርሃን፣ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር በመባርቅትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመው ታላቅ መልአክም ነው ቅዱስ ዑራኤል፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6÷2 መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ይሰማራል።

ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለትም የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለነቢዩ ሄኖክ ነግሮታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፣ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ እርሱ ነው፡፡ ሊቀ መልአኩ የጌታችንን ደም የረጨበት ጽዋ በሀገራችን በኢትዮጵያ እመጓ ቅዱስ ኡራኤል እንደሚገኝ ስፍረዋን የጎበኙ ጸሐፍትና የስፍራው አገልጋዮች ይገልጻሉ፡፡

ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፣ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ በርካታ ቅዱሳን አባቶች ምስጢር እንዲገለጥላቸው የረዳቸው ቅዱስ ዑራኤል መሆኑ በበርካታ የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ሰፍሮ ይገኛል፡፡ አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል እንዲናገሩ፣ የሚጽፉበት ብዕር በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ለሕይወት ድህነት የሚሆን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ቅዱስ ዑራኤል አግዟቸዋል፡፡ ይህም ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ያሳየናል፡፡

ዛሬም በየገዳማቱ ያሉ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ዓለምን ንቀው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፤ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ተቋቁመው በጾምና በጸሎት ሲተጉ ይህ ቅዱስ መልአክ ዑራኤል ፈጽሞ ይራዳቸዋል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ 8÷4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።” እንዲል በገዳማውያኑ መካከል ተገኝቶ ጸሎታቸውን ያሳርጋል፤ ልመናቸውን በአምላክ ፊት ያቀርባል፡፡ ቅዱሳን መካናትን ስናግዝ፣ ገዳማትን ስንረዳ፣ በዓታቸውን ስናጸና የገዳማውያኑ ጸሎትና በረከት ይደርሰናል፡፡    

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444



15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.